Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ፍትሕና ሰላም

ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጋላገር፥ ለውሁዳን ሃይማኖች የሃይማኖት ነጻነት ጥበቃና ክብር መቆም

ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጋላገር፥ ለውሁዳን ሃይማኖች የሃይማኖት ነጻነት ጥበቃና ክብር መቆም - AP

26/09/2017 08:58

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 72ኛው ዓለም አቀፍ የመሪዎች ጠቅላይ ስብሰባ ቅድስት መንበርን ወክለው የተሳተፉት የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሪቻርድ ጋላገር “ለአናሳ ሃይማኖት ምእመናን ጥበቃ” ማረጋገጥ አስቸኳይ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ኃላፊነት መሆን አለበት የሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያተኮረ ንግግር ማሰማታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

በዚህ ግጭት በሚካሄድባቸው ክልሎች የሚኖሩት የአናሳ ሃይማኖት ምእመናን ጥበቃ ትኩረት በማድረግ በተካሄደው ውይይት ብፁዕነታቸው እንዳመለከቱት፥ እ.ኤ.አ. 2016 ዓ.ም. በስፋት ጸረ አናሳ ሃይማኖቶች ምእመናን ጥቃት የተፈጸመበት ዓመት መሆኑ በማስታወስ፡ ብዙዎች ለስደት ለመፈናቀል ለአዲስ ባርነት አደጋ ለአካላዊና ለሥነ ልቦናዊ ጉዳት መጋለጣቸውንም ጠቅሰው ከዚህ በዘለለ  እስከ ዘር የማጥፋት ወንጀልም ተፈጽሞባቸዋል እንዳሉ ያመለከተው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስቲያን እንርዳ የተሰየመው የቤተ ክርስቲያን ማኅበር የሰጠው መግለጫ ጠቅሰው፥ በዓለማችን 38 አህጉራት በአናሳ ሃይማኖቶች ምእመናን የሃይማኖት ነጻነት ጥሰት እንደተፈጸመባቸው ለማረጋገጥ ተችሏል እንዳሉ ይጠቁማል።

የንኡሳን ሃይማኖቶች መብትና ክብር ለማስጠበቅ ያግዛሉ ያሉዋቸውን መሠረታውያን ነገሮች ብፁዕነታቸው ሲዘረዝሩ እንዳሳሰቡት፥ በቅድምያ የሕዝቦችን ነጻነት ሰብአዊ መብትና ክብር የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት ኃላፊነታቸውን መወጣት፡ የሁሉም ዜጋ አለ በየትኛውም ሀይማኖት እና ጎሣ አባል ይገኝ የዜግነት መሠረታዊ መብት ማረጋገጥ ተገቢና ግዴታም ነው። በዚያ የብዙሃን ሀይማኖት በመንግሥት ደረጃ እውቅና በሚሰጥበት አካባቢ የአናሳው ሀይማኖት መከበር አለበት በመሠረቱ የሀይማኖቶ ነጻነት መከበር ይኖርበታል።  ሁሉም ሀይማኖቶች እውቅ አግኝተው ለማንኛውም ዓይነት አመጽ ጥቃት እንዳይሆኑ መከላከል የሁሉም ኃላፊነት ነው። በሕግ ፊት ሁሉም ሀይማኖቶችና ሁሉም ዜጎች እኩል መሆናቸው መታወቅ አለበት። በመጨረሻም ጋራዊ ወይንም የጋራው ሉአላዊነት እና በሀይማኖት ማህበረሰቦች መካከል የጋራ መግባባት እና አዎንታዊ ትብብር ለሁሉም ሀይማኖቶች ነጻነት መከበር መሠረት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ግብጽ በሚገኘው በታላቁ የምስልምና ሃይማኖት መንበረ ጥበብ አል አዝሃር ተገኝተው  ባስደመጡት ንግግር እንዳሰመሩበት በማስታወስ ማብራራታቸው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ ያመልክታል።

ብፁዕ አቡነ ጋላገር በዚያ ባሰሙት ሰፊ ንግግር የሀይማኖት መሪዎች ያለባቸውን ኃላፊነት በማስታወስ፥ በቡድንም ይሁን መግልም የማንኛውም ሀይማኖት ተአምኖቶችን ተገን በማድረግ በሌሎች ወይንም በሀይማኖት ያንተ ወገን ባልሆኑት ላይ የሚፈጸመውን መደል አመጽና ግፍ ማውገዝ፡ በሃይማኖት ስም የሚፈጸመው ግብረ ሽበራ አለ ምንም ማመንታት ማውገዝ ይጠበቅባቸዋል። ቅዱስ አባታችን በእግዚአብሔር ስም የሚፈጸም ማንኛውም ዓይነት ዓመጽ ሁሉም ሀይማኖቶች ውጉዝ ብለው በሀይማኖቶች መካከል ሰላማዊ የጋራ ኑሮ መገንባት ምርጫ ሊጠመዱ ያስፈልጋል ያሉትን ሃሳብ ብፁዕ አቡነ ጋላገር ባሰሙት ንግግር ጠቅሰው ሀይማኖታዊ ግብረ ሽበራ ፈጽሞ ምክንያታዊ ሊሆን አይችልም። ምክንያታዊው በሀይማኖት ስም የሌላውን ሀይማኖት ማክበር ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል አስታወቀ።

የሁሉም የተለያዩ ሀይማኖቶች የጋራ ውይይት ለአሸባሪነት ፍቱን መድሃኒት ነው። ስለዚህ የዚህ ዓይነት የሁሉም ሀይማኖቶች የጋራው ውይይት ለተወሃደ ማኅበራዊ ኑሮ ትልቅ አብነት ነው ያሉት የቅድስት መንበር የውጭ ግንኙነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ጋላገር ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ፡ ሕንጸት ፅንፈኛነትን ለመከላከል ቁልፍ ነው ካሉ በኋላ፥ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ማንኛውም ንኡሳን ሀይማኖቶችና ምአምኖቻቸውን ለማጥፋት ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ ለመዳረግ ዓላማ ማስፈጸሚያ የገንዘብ ሃብትና የጦር መሣሪ ዝውወር እንዲቆም ጥላቻን የሚያነቃቃ ጥላቻው ወደ ዓመጽ ሊያሸጋግር የሚችል ተግባር ሁሉ እንዲወገድ መባድረጉ ረገድ ካለ መታከት ተግቶ መንቀሳቀስ ይኖርበታል እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አመለከተ።

26/09/2017 08:58