2017-09-23 09:26:00

ቅድስት መንበርና ዓለም አቀፍ የምስልምና ሃይማኖት ጉባኤ በጸረ ጸንፈኞች ትግል በጋራ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አገረ ቫቲካ ለጉብኝት የገቡትን የዓለም አቀፍ የምስልምና ሃይማኖት ጉባኤ ጠቅላይ ዋና ጸሓፎ ዶክተር ሙሃማድ አል ኢሳን እ.ኤ.አ. መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የጋራ ግንኙነት ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሕንጻ ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቅ።

ዶክተር ሙሃማድ አል ኢሳ አገረ ቫቲካን እንደ ገቡ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የጋራ ግንኙነት ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራን ጋር መገናኘታቸውና በተካሄደው ግንኙነትም ሃይማኖትና አመጽ የማይጣጣሙ እና ወንድማማችነትና ሰላማዊ የጋራ ኑሮና ሰላም ለመገንባት የሚያስችል ግብረ ገባዊ ሃብቶች ያለው መሆኑበእጽንዖት በማመላከት በማያያዝም ጸንፈኝነት ወደ ደም ማፋሰስ የሚገፋፋው ግጭት ከሃይማኖት ጋር የሚጻረር ፈጽሞ ሃይማኖታዊ መሰረት የሌለው ተግባር መሆኑ እንደተሰመረበት የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍ መግለጫ አያይዞ፥ የሃይማኖት እና የሕሊና ነጻነት በስፋት በምንኖርበት ዓለም ለአደጋ መጋለጡና ትክክለኛ የሆነ ሃይማኖታዊ ባህል ማስፋፋት ለሰላማዊ የጋራ ኑሮ ዋስትና መሆኑ ያረጋገጠ ግኑኝነትም እንደነበር አስታውቆ ሁለቱ አካላት በቅርቡ አንድ የጋራ ኮሚቴ ማቋቋም በሚል መርሐ ግብር መስማማታቸው ያመልክታል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.