Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ሐዋርያዊ ጉዞዎችና ጉብኝቶች

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ በላቲን አመሪካ በምትገኘው አገረ ኮሎምቢያ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ በላቲን አመሪካ በምትገኘው አገረ ኮሎምቢያ - EPA

12/09/2017 16:03

እ.ኤ.አ. መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ከኮሎምቢያ ርእሰ ከተማ ቦጎታ ከሚገኘው ካታም ከተሰየመው አየር ማረፊያ በኮሎምቢያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 07፡20 ተነስተው ልክ 07፡50 ቪላቪሰንሲዮ በሚገኘው ልዊስ ጎመዝ ኒኞ አፒያ  ኣየር ማረፊያ እንደደረሱ በከተማይቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ኦስካር ኡርቢና ኦርተጋ በኮሎምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት ሊቀ መንበር በክልሉ አስተዳዳሪና የከተማይቱ ከንቲባ እንዲሁም በክልሉ የመከላከያ ኃይል የጸጥታ ኃይልና የአፒያ የአየር አይል አዛዦች አቀባበል ተደርጎላቸው በቀጥታ እ.ኤ.አ. በ1989 ዓ.ም. በታጣቂ ኃይሎች እጅ የተገደሉት የአሩአካ ሰበካ ጳጳስ ለነበሩት ለእግዚአብሔር አገልጋይ ብፁዕ አቡነ ኸሱስ ኤሊዮ ካራሚሎ ሞንሳልቨና እ.ኤ.አ. በ 1948 ዓ.ም. የተገደሉት የሰበካ ካህን የእግዚአብሔር አገልጋይ አባ ፐድሮ ማሪያ ራሚረዝ ራሞስን ብፁዕና ለማወጅ የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ለማቅረብ 1 ሚሊዮን ሕዝብ የማስተናገድ አቅም ወዳለው ካታማ ወደ ሚገኘው ሰፊ ክልል 09.15 ደቂቃ ደርሰው በቅዳሴው ስነ ሥርዓት ለመሳተፍ የተገኘነውን በብዙ ሺሕ የሚገመተውን ሕዝብ እየተዘዋወሩ ሰላምታን ካቅረቡ በኋላ በላቲን ስርዓትም ዕለቱ በዓለ ልደታ ለማርያም መሆኑ የዘከሩት ቅዱስነታቸው በብፁዓን ጳጳሳትና ካህናት ታጅበው መስዋዕተ ቅዳሴውን አሳርገው በዕለቱ  ከነቢይ ሚኪያስ ምዕ.1 ከቁጥ. 1-4 እንዲሁም ከማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 1 ከቁጥር 1-16፡ ከ 18-23 የተወሰዱትን ምንባባት አስደግፈው ባስደመጡት ስብከት፥ የአመጽ ሰለባ የሆኑት ሁሉ የቂም በቀል ፈተና ላይ ድል የሚነሳ ኃይል ምስክሮች ናቸው። የቂም በቀል ፈተናን የሚያሸንፉ ሁሉ የእርቅ ታማኝና አሳማኝ ምስክሮች ናቸው። በእርቅ ጎዳና የመጀመሪያው እርምጃ ከእኔ ይሁን የሚሉ ሁሉ የተጨባጭ ተስፋ ህያው ምስክሮች ናቸው። እርቅ ጽኑና ተጨባጭ የሚሆነው በሁሉም አስተዋጽኦ ነው። ስለዚህ ያለ ሁሉ ሱታፌ እርቅ ተሸናፊ መሆኑና እርቅ ከእግዚአብሔር ጋር እርቅ ከወድንምና እህት ጋራ እንዲሁም ከተፈጥሮ ጋር በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያማከለ ሰፊና ጥልቅ ስብከት መለገሳቸው የቫቲካን አዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ ኣኵይሊኖ አስታወቁ።

 

ቅዱስነታቸው ብፅዕና ያወጁበትን መስዋዕተ ቅዳሴ አጠናቀው ልክ 05 ሰዓት ሰኣት ተኩል ማሊካ ደ ኾሮቭ ወደ ተሰየመው የእንግድ መቀበያ በመሄድ እዛው ምሳ ተቋድሰውና አጭር እረፍት ካደረጉ በኋላ ከቀትር በኋላ ልክ 09.30 ላይ የእርቅ ስነ ሥርዓት ለመምራት ከስድስት ሺሕ በላይ ወደ ሚያስተናግደው አዳራሽ በመሄድ የዛሬ 10 ወር በፊት በሰላም ስምምነት በተቋጨው ለ 50 ዓመት በተካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ጉዳት በደረሰባቸው ንፁሓን ዜጎችና የቀድሞ ታጣቂ ኃይል አባላት በነበሩት ሰላምታ ተደርጎላቸው ወደ መድረኩ እንደ ወጡ፡ የቪላቪሰንስዮ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኦስካር ኡርቢና ኦርተጋ ያሰሙት የእንኳን ደህን መጡ ንግግር ተደምጦ እንዳበቃ መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 85 ተነቦና ዕርቅና ሰላም የሚያስተጋቡ መዝሙሮች ከተደመጡ በኋላ የጦርነቱ ጉዳተኞች ከሆኑት ውስጥ አራት ዜጎች የሰጡት ምስክርነት ተሰጥቶ እንዳበቃም ቅዱስ አብታችን በዚያ እ.ኤ.አ. በ 2002 ዓ.ም በቦኻያ ክልል ጥቃት ተፈጽሞ በዚያች ብዙዎች ሕይወታቸው ከሞት አደጋ ለማዳን ተደብቀዉባት በነበረቸው ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት ተጥሎ እዛው ውስጥ የነበርው የስቁል ኢየሱስ ምስል ሳይቀር ጉዳት ደርሶበት እስካሁን ድረስ ታቅቦ የሚገኘው አካለ ጉዳተኛው ኢየሱስ የተሰየመው መስቅል በተኖረበት መድርክ ሆነው፥ በሁሉም በማንኛውም ሰው ላይ የሚፈጸመው ዓመጽ የመላ ሰው ዘር ስቃይና ቁስል ነው …  ፍቅር ከሞት በላይ ያይላል። ይኽ አካለ ጉዳተኛው ኢየሱስ የተሰየመው መስቀል የዚያ የእርስ በእርስ ጦርነት ሞትና እልቂት ተጨባጭ ምስክርነት ነው … ዓመጽ ዓመጽን ይወልዳል በምሕረት ግን የጥላቻው ሰንሰለት ይበጣጠሳል። የመጨረሻው ቃል ዓመጽ ሳይሆን ድል ነው፡ ይኽ ደግሞ የጦርነት ሰለባ የሆኑት የሰጡት ምስክርነት የሚያረጋግጠው እውነት ነው ያሉት ቅዱስ አባታች ምስክርነታቸው ከሰጡት ውስጥ የአካል ጉዳት ከደረሰባት ዜጋ ገጸ በረከብት የሰጠቻቸው የምትደገፍበት ምርኩዝ እያሳዩ፥ ጉዳት የደረሰብሽ ብትሆኝም ይቅርታን በማድረጉ ተግባር እጅግ ፈጣን ነሽ። ይቅርታ በመስጠቱ ሂደት ክርስቲያን ፈጣን መሆን ይገባዋል። ብዙዎቻችን ያ የዓመጽና የሞት ምክንያት የሆነው ሰው ተለውጫለሁ ቢለን ለማመን ይሳነናል፡ ማመኑ እጅግ ከባድ ነው፡ ኢየሱስ ለህሙማን ነው የመጣው። ስለዚህ በይቅርታ ጎዳና የመጀመሪያው እርምጃ ከእነዚያ የአመጽና የሞት ምክንያት ከሆኑት ሰዎች ሊጀምር እንደሚችል ማመን ያስፈልጋል። በይቅርታ መንገድ የመጀመሪያው እርምጃ ክእኔ ይጀምር እንበል። … እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አያይዘው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የመስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም. መርሐ ግብራቸው ከቪላቪሰንሲያዮ ከሚገኘው ከእፒያ የአየር ኃይል አየር ማረፊያ ተነስተው ቦጎታ በሚገኘው ካታም ወታደራዊ ያየር ማረፊያ በመግባት እዛው ወደ ሚገኘው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሕንጻ በመመለስ እንደነበርም ያመልክታሉ።

 

እ.ኤ.አ. መስከረም 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ልክ ከጠዋቱ 02፡20 ደቂቃ ቦጎታ ከሚገኘው ከካታማ የአየር ማረፊያ ተነሰተው ሓዋርያዊ ጉብኝታውን በዚያች ዘለዓለማዊት ጸደይ ተብላ በምትጠራው መደሊን ከተማ ለማከናወን ልክ ከጠዋቱ 03፡30 ደቂቃ ደርሰው አቀባበል ባደረጉላቸው በመዲሊን ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሪካርዶ ቶቦንና በከተማይቱ አስተዳዳሪና ከንቲባ አቀባበል ባደረጉላቸው አካላት ተሸኝተው መደሊን በሚገኘው በኤንሪከ አላያ ሀረራ አየር ማረፊያ ባለው አደባባይ ደርሰው እዛው ለተገኙት ምእመናን እየተዘዋወሩ ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው በዕለቱ ምንባብ ከቆላስይስ ምዕ. 1 ከቍ. 21-23 እንዲሁም ከሉቃስ ወንጌል ምዕ. 6 ከቍ. 1-5 አስደግፈው በኢየሱሳዊ ማኅበር አባል በወቅቱ የነበረውን የባርነት ስርዓት በመቃወም በዚያ ስርዓት ይሸጡና ይለወጡ ስለ ነበሩት ዜጎች በመጣበቅ ስለ ድኾች ስለ ሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ሕይወታቸውን የሰዉት ቅዱስ ፒየሮ ክላቨር በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የሚዘከሩበት ዕለት መሆኑ በማስታወስ፡ ያንን ሕግን ለመዘረዝ ሳይሆን ሕግን ወድ ሙላት ለማድረስ የመጣውን ኢየሱስ ክርስቶስ መከተል ያለው አስፈላጊነት ላይ በማተኮር የለገሱት ስብከት ሲያጠቃልሉ በእዚህ በእናንተ መካከል የምገኘው በእምነት በተስፋ ለማጽናናት ነጻ የሚያወጣው ክርስቶስ ነጻነታችን በመሆኑ ሁሉም በክርስቶስ ጹኑና ነጻ እንዲሆን አስተውል ለማለት ነው።እርሱ ትለወጡና ትፈቀሩም ዘንድ ፍቀዱለት ቅድስተ ማርያም ዘካንደላሪያ የሐዋርያዊ ጎዞአችሁ ትደግፍ፡ ዘወትር ለሁሉም ሕዝብ በሁሉም ሕዝብ መካከል ታማኝ ልኡካነ ወንጌል እንድንሆን ትደግፈን እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ልክ እኩለ ቀን መደሊን ወደ ሚገኘው የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት በመሄድ ምሳ ተቋድሰው በዘርአ ክህነት ትማሪዎች ቤተ ጸሎት ከዘርአ ክህነት ተማሪዎች ጋር ተገናኝተው ከተማሪዎች ጋር ለመታሰቢያ ፎት ግራፍ መነሳታቸው ያመለክታል።

ቅዱስነታቸው  ልክ ከቀትር በኋላ 08፡45 ደቂቃ መደሊን የሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ማደጎ ቤት ጎብኝተው እዛው ከሚረዱት ሕጻንትና የማእከሉ አስተዳዳሪዎች ጋር ተገናኝተው ቃለ ምዕዳን ለግሰው ልክ ከ09፡45 ደቂቃ ወደ ማካረና ትያትር ቤት በመሄድ እዛው ከካህናት ገዳማውያን ደናግልና የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ጋር ለመገናኘት እንደረሱ የመድሊን ሰበካ ተባባሪ ሊቀ ጳጳስና የጥሪ ጉዳይ የሚከታተለው ሓዋርያዊ ቢሮ ተጠሪ ብፁዕ ኣቡነ ኤልኪን ፈርናንዶ አልቫረስ የእንኳን ደህና መጡ መልእክት እሰምተው እንዳበም ቅዱስ አባታችን በማስከተል ከዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 15, 1-11 የተነበበውን ቃለ ወንጌል አማክለው ቃል መዕዳን ለግሰዋል ያለው የቅድስት መንበር ዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ይኽ የተካሄደው ግኑኝነት እንዳበቃም ቅዱስነታቸው 11፡30 ከኾሰ ኮርዶባ የአየር ማረፊያ ተነስተው ቦጎታ በሚገኘው ካታም አየር ማረፊያ ልክ 12፡25 ደቂቃ ደረሰው ወደሚያርፉበት ወደ ሐዋርያዊ ሕንጻ ማቅናታቸው ይጠቁማል።

 

እ.ኤ.አ. መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ከጠዋቱ 02፡00 ደቂቃ ከካታም የአየር ማረፊያ ተነስተው ወደ ካርታገና በሚገኘው በራፋኤል ኑኘዝ የአየር ማረፊያ ልክ 04፡00 እንደ ደረሱ በካርታገና ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኾርገ ኤንሪከ ኺመነዝ ካርቫያል በከተማይቱ የመንግሥት አካላትና ከንቲባ እንዲሁም የክልሉ የመከላከያ ኃይል አዛዥ የአቀባበል ስነ ስርዓትተድርጎላቸው እዛው ይጠባበቁዋቸው ለነበሩት 300 ወጣቶችን ቀርበው ሰላምታቸውን ካቀረቡ በኋላ ወደ ቅዱስ ፍራንቸስኮ አደባባይ ተዛውረው በቅዱስ ፍራንቸስኮ ቁምስና ቆሞስ አባ ኤልኪን አሰቨዶ አቀባበል ተደርጎላቸው ኣዛው ለሚገነባው የጎዳና ተዳዳሪ መጠለያ ማእከል የመሠረት ድንጋይ ባርከው ካኖሩ በኋላ ለምሳ ድኾች ወደ ሚረዱበት የግብረ ሰናይ ማእከል በመሄድም ማእከሉን መጎብኘታቸው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታች ልክ 11.30  እ.ኤ.አ. በ1604 ዓ.ም. ኢየሱሳውያን ማኅበር ወደ ተመሰረተው ቅዱስ ፔትሮ ክላቨር ገዳም በመሄድ እዛው የካራገና ኢየሱሳውያን ማኅበር ልኡካን አለቃ አቀባበል ተድርጎላቸው፡ ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ደግመው እስተንትኖ ለግሰው ካበቁ በኋላ  በኢየሱሳውያን ልኡካን ማኅበር ከሚረዱት ከ 300 ጥቁር ኮሎምቢያውያን ጋር ተገናኝተው በቅዱስ ፒየትሮ ክላቨር ቅዱስ ትሩፋት ፊት ተንበርክከው የግል ጸሎት አሳርገው አበባ አኑረው ከ65 የኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት ጋር ከተገናኙ በኋላ ወደ ቅዱስ ዶሚንጎ መናንያን ቤት በመሄድ እዛው መሳ ተቋድሰው ልክ 09፡55 ደቂቃ ወደ ክርታገና ቤተ ሊቀ ጳጳስ በመሄድ ከ 300 ህሙማን ጋር ተገናኝተው ቡራኬ ሰጥተው 09፡45 ደቂቃ ከካርታገና ተነስተው በካርታገና ወደባዊ ክልል ተገኝተው ልክ 10፡30 ብዙ ሕዝብ ያሳተፈ መስዋዕተ ቅዳሴ ኣሳርገው  እንዳበቁም ከዛው ተሰናብተው ካርታገና ወደ ሚገኘው ፋራኤል ኑኘዝ የአየር ማረፊያ እንደደረሱ በኮሎምቢያ ረፓብሊክ ርእሰ ብሔርና ክብርት ባለ ቤታቸው አቀባበል ተደርጎላቸው አጭር የግል ግኑኝነት ካካሄዱ በኋላ በመከላከያ ኃይል የሙዚቃ ጓድ የቅድስት መንበር ብሔራዊ መዝሙርና የኮሎምቢያ ብሔራዊ መዝሙር ተደምጦ ይፋዊ ሽኝት እንደተደረገላቸው ከኮሎምቢያን ተሰናብተው ልክ 01፡00 በአየር ተሳፍረው እ.ኤ.አ. ዛሬ መስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ልክ 06፡55 ደቂቃ ቻምፒኖ አየር ማረፊያ ደርሰው እንደ ወትሮው ሮማ ወደ ሚገኘው ቅድስተ ማሪያም አቢይ ባዚሊካ በመሄድ በየሮማውያን ድኅነት በተሰየመቸው በቅድስት ማርያም ቅዱስ ምስል ፊት ጸሎት አሳርገው አገረ ቫቲካን በሰላም ገብተዋል። 

12/09/2017 16:03