2017-09-09 09:12:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሃያኛው ዓለም አቀፋዊ ሓዋርያዊ ጉብኝት በኮሎምቢያ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ወደ ኮሎምቢያ ለሐዋርያዊ ጉብኝት ከኢጣሊያ በመነሳት በዚህ ወደ ኮሎምቢያ በሚያደርጉት ጉዞ የአየር የበረራ ክልላቸውን ለሚያቋሩጡባቸው አገሮች የቴለግራም መልእክት አስተላፈዋል። ቅዱስነታቸው በዚህ ለኢጣሊያ ረፓብሊክ ርእሰ ብሔር ሰርጆ ማታረላ፡ ለፈረንሳይ ርእሰ ብሔር ኤምኑኤል ማክሮን ለስፐይን ንጉስ ፊሊፐ ስድስተኛ ለፖርቱጋል ርእሰ ብሔር ማርሰሎ ረበሎ ደ ሱሳ፡ ለተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ዶናልድ ትራምፕ፡ ለባርባዶስ ጠቅላይ አስተዳዳሪ ፊሊፕ ግረቨስ፡ ለግረናዳ ጠቅላይ አስተዳዳሪ ሰቺለ ላ ግረናዳ፡ ለቨነዝዋላ ርእሰ ብሔር ኒኮላስ ማዱሮ ባስተላለፉት የቴለግራም መልእክት፥ ለእያንዳንዱ የተጠቀሰው አገር ወቅታዊ ሁኔታ አማክለው፡ ሰላም ፍትህ ትብብር ሰብአዊ እድገት የሚሉትን እሴቶች በማስተጋባት ለአህጉራቱና ሕዝቦቻቸውንም ጭምር በጸሎታቸው እንደሚዘክሩዋቸው አረጋግጧል።

የተከበራችሁ አድማጮቻችን ከዚያች ቅዱስነታቸው ሓዋርያዊ ጉብኝት አያካሄዱባት ካለችው ከአገረ ኮሎምቢያ ርእሰ ከተማ ቦጎታ ጋር እናስተዋውቃችሁ፥

ቦጎታ ይፋዊ የመጸውዕ ስሟ ሳንታ ፈ ደ ቦጎታ የሚል ሲሆን። ለምና ቅድመ ኮሎምቢያ የሚባሉት የኢንዶስ ሙይስካ ባህል ይኖርባቸው በነበሩት ተራራዎች የተከበበች ከተማ ስትሆን። ይህች በቀደምት የአገሪቱ ተወላጆች ኢንዶስ ባካታ ተብላ ትጠራ እንደነበረችም ሲጠቀስ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 6 ቀን 1538 ዓ.ም. በአገሮች ዳሳሽ ወራሪው የስፐይን ተወላጅ ጎንዛሎ ኺመነዝ ደ ኵወሳዳ የተቆረቆረችና ከተማ መሆንዋ ይነገራል።

እ.ኤ.አ. ሐምሌ 27 ቀን 1540 ዓ.ም. በወንድም ድኮሚንጎ ደ ላስ ካሳስ ለመጀመሪያ ጊዜ መሥዋዕተ ቅዳሴ ባረገባት ቤተ ክርስቲያን ባማከሉት ለ12 ደቀ መዛሙርት ክብር በተገነቡት በ 12 ጎጆዎች የተከበበች እንደነበረችና ለስፐይኑ ልዑል ካርሎ አምስተኛ ክብርም ሳንታ ፈ የሚል ተቀጥያ ስም ተሰጥቷትና ይፋዊ የመጠሪያ ስሟም ሳንታ ፈ ደ ቦጎታ እንዲሆን መወሰኑም ይገለጣል።

ከሦስት ዘመናት በኋላ በትክክል ከስፐይን ቅኝ ግዛት እጅ ነጻ ከወጣች በኋላ እ.ኤ.አ. በ 1819 ዓ.ም. ኮሎምቢያ በጥንታዊ የመጸውዕ ስሟ እርሱም ሙይስካ ቦጎታ ተብላ መጠራት ጀምራ ከ1717 ዓ.ም. ወዲህ የአዲስቷ ግራናዳ ርእሰ ከተማ ሆኖ ከቆየች በኋላ በ1830 ዓ.ም. የታላቋ ኮሎምቢያ ርእሰ ከተማ ሆና ቆይታለች። ታላቋ ኮሎምቢያ ኤኳዶር ቨነዝዋላ የአሁኗ ኮሎምቢያና በኋላም በ 1903 ዓ.ም. ከኮሎምቢያ ተገላ ነጻ አገር የሆነችው ፓናማን በተሰየመ አገሮች ተከፋፍላለች። የወቅታዊቷ ኮሎምቢያ የዚህ ክፍፍል ውጤትም መሆንዋም የኮሎምቢያ የታሪክ ማኅደር ያመለክታል።

መጋቢት 22 ቀን 1664 ዓ.ም. ሜጥሮፖሊ ለመሆን በቅታ በአሁኑ ወቅት በበጎታ ሰበካ 4.486.980 ነዋሪ ሕዝብ እንዳለና ከዚህም ውስጥ 3.866.879 ካቶሊክ ምእመን ነው፡ ሰበካው 279 ቁምስናዎች፡ 443 አቢያተ ክርስቲያን፡ 380 ካህናት፡ 481 የሰበካ ካህናት፡ 138 ቀዋሚ ዲያቆናት፡ 90 የዘርአ ክህነት ተማሪዎች፡ 1.011 ገዳማውያን፡ 1.497 የተለያዩ የደናግሎች መንፈሳዊ ማኅበር አባላት ደናግል፡ 546 የካቶሊክ አቢያት ትምህርት፡ 237 የግብረ ሠናይ ማእከሎች ያቀፈ ሰበክ ሲሆን። ባለፈው ዓመት 41.850 ዜጎች ሚሥጢረ ጥምቀት የተቀበሉበት በብፁዕ ካርዲናል ሩበን ሳላዛር ጎመዝ ሊቀ ጵጵስና ሥር የሚመራ መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል የዜና ምንጭ አስታወቀ።

በኮሎምቢያ የቅድስት መንበር ሓዋራዊ ልኡክ “ኑንዚያቱራ” አጭር ታሪክ

የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሕንፃ በቦጎታ በዚያ የካቶሊክ መንበረ ጥበብ፡ የአገሪቱ ዋናው የቴሊቭዥንና የረዲዮ ጣቢያ ማእከል፡ የተለያዩ የአገሪቱ መንግስት ሚኒስትራዊ ሕንፃዎች በሚገኙበት ብዙ ነዋሪ ሕዝብ ሰፋሪ ባደረገው በተኡሳኵይሎ ክፍለ ከተማ ይገኛል። የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ በጠቅላላ በበጎታ ከሚኙት ከ200 የተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት ውስጥ አንዱ ነው።

በኮሎምቢያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ የቪቶሪያና ሰበካ ስዩም ጳጳስ ተብለው እ.ኤ.አ. የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም. የተሾሙት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ኤቶረ ባለስትረሮ ሲሆኑ በቅድስት መንበር የአገረ ኮሎምቢያ ልኡከ መንግሥት ደግሞ ጉሌርሞ ሊዮነ ኤስኮባር ሄራን መሆናቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

 

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በኮሎምቢያ ርእሰ ብሔር አቀባበል ተድርጎላቸው አገሪቱ ቤተ መንግሥት በተደረጋልቸው የእንኳን ደህና መጡ ስነ ሥርዓት ርእሰ ብሔር ዅዋን ማኑኤል ሳንቶስ ካስደመጡት ንግግር በመቀጠል ባሰሙት ንግግር፥

ክቡር ርእሰ ብሔር

ክቡራትና ክቡራን የረፓብሊካዊት ኮሎምቢያ መንግሥት አካላት፡ ልኡካነ መንግሥታት

ክቡራትና ክቡራን

ለኮሎምቢያ ርእሰ ብሔር ዶክተር ኹዋን ማኑኤል ሳንቶስ በዚህ አገሪቱ ልዩ የታሪክ ምዕራፍ በምትገኝበት ወቅት ይፋዊ ጉብኝት እንዳደርግ ባቀረቡልኝ ጥሪ መሰረት ዛሬ እዚህ በመገኘቴ ምስጋናዮን አቀርባለሁ። እዚህ ለምትገኙት ለሁሉም አህጉራት ልኡካነ መንግሥታት ሰላምታዮን አቀርባለሁ። እዚህ ለምትገኙት ለሕዝባውያን ተቋም ወኪሎች በጠቅላላ ለመላው የኮሎምቢያ ሕዝብ ልባዊ ሰላምታዮን አቀርባለሁ።

እዚህ የምገኘው ከእኔ በፊት በሩቅ ዓመታት በኮሎምቢያ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ በቀዳሚነት የሚጠቀሱት የብፁዕ ጳውሎስ ስድስተኛና ሁለተኛ አገሪቱን የጎበኙት ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዱካ በመከተል፡ ልክ እንደ እነርሱ ከኰሎምቢያውያን ወንድሞቼ ጋር በመሆን እምነትን ለመቀደስ ነው፡ … በእምነት በተስፋ ብቻ  ነው በሕይወት ጉዞ የሚያጋጥመው ችግር ሁሉ የሚፈታው አገሪቱም ለሁሉም ዜጎችዋ የትውልድ አገር የምትሆነው።

ኮሎምቢያ በተለያዩ መስክ የተባረከች አገር ነች። በተፈጥሮ ሃብት በመልክዓ ምድራዊ ውበት የታደለች በዓለም በብዝኃ ሕይወታውያን ነገሮች ሃብታም ናቸው ተብለው ከሚገለጹት አገሮች ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠች፡ ይኸንን ሁሉ የታደለችውን ጸጋ በማድነቅም “በትፈጠረው ሁሉ ፈጣሪን ማመስገን” (መዝ. 33.9 ተመ.) ነው፡ … ሃገረ ኮሎምቢያ በእግዚአብሔር ጸጋዎች የታደለች ሃብታም በሕዝቧ ዓይነተኛው ሰብአዊነት ጽናትና ብርታት የታደለች አገር ነች።

… ይኽ የማካሂደው ጉብኝትና በዚህ ጉብኝትም በማከናውናቸው ግኑኝነቶች ያንን የዛሬ አስር ወር በአገሪቱ የነበረው ትጥቃዊ ዓመጽ ለማስወገድ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ዕርቅና ሰላም እውን ለማድረግ የተደረገው ጉዞ ቀርቤ አደንቅ ዘንድ ዕድል ሆኖልኛል። በጋራው ሰላምና ተስፋ በመሻት የተከናወኑ ጥረቶች ለዚያ በጋር መኖር ዘንድ ያለውን ተስፋ የሚያፈካ ነው። … ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ያንን የነበረው ያመለካከት ልዩነት እየጠበበ መጥቶ ወደ አንድ ስምምነት ለመደረስ ተበቅቷል። ሰላማዊ የጋራ ኑሮ ለማስጨበጥ ያስችላሉ የሚባሉት በተለያየ መልኩ ይገለጡ የነበሩት አመለካከቶች ዘንድ የነበረው ልዩነት ጭምር ጠቦና ተወግዶ የሚፈለገው ሰላም ተደራሽ ሆኗል። ይኽ ጥረት የግልና እሩቅ የማይመለከት ጥቅም ላይ ከማተኮር ያድነናል። በማንኛውም ፖለቲካዊ ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ ሂደት ሰብአዊነት ሊማከል ይገባዋል። … ወደ ሰላምና ስምምነት የሚያደርሰው ጎዞ አድካሚ እንደሆኑ መጠን ከእኛ ለተለየው እውቅና መስጠትና መቀበል ቁስሎችን መፈወስ አገናኝ ድልድይ መገንባት እርስ በእርስ መደጋገፍ እንዲኖር የሚደረገው ጥረት ምንኛ ጥልቅና ከባድ መሆኑ ግልጽ ነው (ወንጌላዊ ሐሴት፡ ቍ. 67 ተመ.)።

የአገረ ኮሎምቢያ አህጉራዊ መርሆ ነጻነትና ስርዓት የሚል ነው፡ በእነዚሁ ሁለት ቃላቶች ውስጥ የአገረ ኮሎምቢያና ሕዝቧ ጥረትና ጉዞ እንዴትና ምን መሆኑና እምን ላይ ያቀና መሆን እንዳለበት ተመልክቶ ይገኛል። ስርዓት የሕግ አርቃቂያንና የኃያላን ሕግ ሳይሆን የአንድነት የውህደት የትብብርና የሰላም ኑሮ ዋስትና ሰጭ መሆን አለበት። … ኢፍትሃዊነት የሁሉም ክፋት መንስኤ ነው (ወንጌላዊ ሐሴት፡ ቍ. 202 ተመ.)፡ በዚህ እይታ መሠረትም ወደ ተናቁት ከህብረተሰብ ወደ ተገለሉት በዳርነት ወደ ሚገኙት ሕዝብ ቅርብ በመሆን ከእነርሱ ጋር ለመገናኘት እነዚህ ዜጎችን ትመለከቱም ዘንድ ምዕዳኔን አቀርባለሁ … ።

የሴቶች መሆናዊ ባህርይ ክብር እንሰጥ፡ ባላቸው በእናትነት ባህርይ አማካኝነትም እንመልከታቸው፡ ኮሎምቢያ መላ ሕዝቧ ያስፈልጋታል። ማንም አላስፈላጊ አይደለም። ሁሉም ዜጋ ለኮሎምቢያ አስፈላጊ ነው።

ቤተ ክርስቲያን ለተልእኮዋ ታማኝ ነች። ትልቁ ጥረቷም ሰላም ፍትህ የጋራ ጥቅም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ የሚውል ነው። ያንን የኮሎምቢያ ማኅበራዊነትን ልዩ ትርግሙ የሚሰጠው በዚያ በሕዝባዊ ማሕበራዊ ቅዋሜው ላይ በልዩ የሚታወቀው  ለአገሪቱ እድገትና ልማት አቢይ አስተዋጽኦ ወንጌላዊ መሰረት ያለው መለየዋ ነው። ይኽ ደግሞ የሕይወት ክቡርነት በተለይ ደግሞ የተቸገሩት እራሳቸውን ለመከላከል ብቃት የሌላቸው ዳር ያሉትን ሁሉ መከላከል የሚል ነው። የሕይወት ባህልም እርሱ ነው፡ የቤተሰብ ሕይወት የቃል ኪዳን ሕይወት ውጤት ነው (ወንጌላዊ ሐሴት፡ ቍ. 66 ተመ)።

ክቡራትና ክቡራን ያተሰጣችሁ ተልእኮ አቢይ ነው። በተመሳሳይ መልኩም የላቀ ጥረት የሚጠይቅ ኃላፊነት ነው። በማንኛው ዓይነት የሕይወት ውጣ ውረዶች የኮሎምቢያው ተወላጅ ጋብሬለ ጋርሲያ ማርከዝ እንደሚለው ሕይወት ላይ ማተኮር ያሰፈልጋል። ያለፈው ጦርነት ግጭት ያለውና ያለፈው ማእበል አውሎ ነፋስ ሁሉ በምንም ተአምር በሕይወት ላይ ድል አይነሳም። የሕይወት ክብር አደራ ይታቀብ፡ ሕይወትን በመቅጨት ደስታ አይገኝም።

በጥላቻና ቂም በቀል ብዙ ጊዜ ባክነዋል … ስለዚህ ማንኛውም ዓይነትም ይሁን ጸረ ሕይወት የሆነውን ተግባር ሁሉ እምቢ እንበል።

ለብቻችሁ እንዳልሆናችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። በምትገኙበት ጉዞ ሁሉ ከጎናችሁ ነን የምንል ብዙዎች ነን። ለብቻችሁ አይደላችሁም። የእኔ እዚህ መገኘት ለማበረታታት ያቀደ ነው። ወደ እርቅና ወደ ሰላም የሚደረገው ጎዞ የሚያጋጥመውን እንቅፋት ማሸነፍ የሚል ፍላጎት ያለው ነው።

በጸሎቴ ህልዋን ናችሁ ስለ እናንተና ስለ ኮሎምቢያ ህልውና መጻኢ አጸልያለሁ።

 

ቅዱስ አባታችን ለኮሎምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት፥ በነጻነት የእዕርቅን ቃል አውጁ

ኮሎምቢያ የእናንተ ትይታ ያስፈልጋታል። ያንን ለብዙ ስቃዮች ምክንያት የሆነውን መፍቻና መዋጣጫ ያጣው አቋራጩ ሃብት የማካበት መንገድ ለዘርፈ ብዙ ቀውስ ሥርወ መሰረት የሆነውን ሙስና ነቅሎ ለማስወገድ፡ አመጽ እንደ ስልት እምቢ ለማለት እኩልነት የለሽ ሁነትን ለማሸነፍ ኮሎምቢያ በምታደርገው ጽኑ ጉዞ እንዲሁም ወደ እርቅና ወሳኝ ወደ ሆነው ሰላም በምታደርገው ጉዞ የብፁዓን ጳጳሳት ታይታ ያስፈልጋታል።

… ኮሎምቢያ ያንን ማንኛውንም ለያይ ግንብ ዘለዓለማዊ ሊሆን እንደማይችል የሚያረጋግጠው ማንኛው ዓይነት ፍርሃት ፈራሽ መሆኑ የሚያሳምነው የማይድን ምንም ዓይነት ስቃይ እንደሌለ የሚያረጋግጠው ሞትን ያሸነፈው ክርስቶስን መካፈልን ትሻለች።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከሳቸው በፊት በዚህች አገር ሐዋርያዊ ጉብኝት የፈጸሙትን የመጀመሪያው ብፁዕ ጳውሎስ ስድስተኛ ሁለተኛውም ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊን እሳቤ በማድረግ በዚያ የዚህ የሳቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት መርሆ እርሱም የመጀመሪው እርምጃ ከእኛ ይሁን የሚለውን ጠቅሰው ቅዱስ መጽሓፍ እንደሚያወሳና  የአብርሃም የሙሴ ታሪክ እንደሚያወሳውም ሁሉ በመጨረሻም በኢየሱስ ትስብእት የተረጋገጠው ኢተቀልባሽ (የማይቀለበስ) የመጀመሪያው ወደ እኛ የማለቱ እርምጃው ከእግዚአብሔርና የዚያ የመጀመሪያው ወደ የማለት የመጀመርያ እርምጃ ለመፈጸም የሚያስችለው የሙሉ ነጻነትን ጸጋ በውስጡ ለማስተናገድ ለሚሻ ሁሉ የነጻነቱ ጸጋው ከኢየሱስ ነው። ፍጹም የእግዚአብሔር ወደ የሚለው የመጀመሪያው እርምጃ ኢየሱስ ነው። ይኸንን ነጻነት በምንም ተአምር እንዳታጡ አደራ። … ለዘመኑ አምባገነኖች ያጎበደዱ ሹመኞች እንድትሆኑ ከሚሻው ጋር እራሳችሁ እታመዛዝኑ፡ ዘወትር በኢየሱስ ዘንድ ያለው ውህደት በጸሎት ፈልጉ። እይታችሁ በዚያ ከዘለዓለማዊነት ጀምሮ በመረጣችሁ ላይ በማኖር ከእርሱ ልሳን የሚወጣውን ወሳኝ ምርጫ አስተናግዱ። ፍርድ ፍርዳችሁ ይሁን። እርሱ ለሚሻው ገዛ እራሳችሁን ስጡ።

… የኮሎምቢያ ምሉእ ሁነትና መሆንነትን ግምት የሚሰጥ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ያስፈልጋል። ያለፈውን ያለውን ታሪክ ግምት የሚሰጥ መጻኢ የሚመለከት ቤተ ክርስቲያናዊ ተመክሮ ያስፈልጋል። ለዚህች አገር ምስክርነትን ለማቅረብ የምትችል በጥቂቶቹ መዳፍ ውስጥ የማትቀር የኮሎምቢያ ጥቁር ኮሎምቢያዊ አናስር ልዩ ግምት የምትሰጥ ቤተ ክርስቲያን መገንባት ያስፈልጋል። … የሁሉም ለሁሉም የሆነች ቤተ ክርስቲያን የኮሎምቢያ ታሪክ በማገናዘብ ሓዋርያዊ ምስክርነት የምታቀርብ ቤተ ክርስቲያን።

በኮሎምቢያ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ያለው የሚገለጠው የክርስቶስ ቁስል የምትነኩ ሁኑ። ሙያተኞች ወይንም ፖለቲከኞች ሳትሆኑ መጋብያን እረኞችና በነጻነት የእርቅና የምህረት ቃል መስካሪያን ናችሁ።

ወንድምህ የት ነው የሚለው የኦሪቱ ጥያቄ ዛሬም ቢሆን ዝም ሊባል የማይገባው መቅረብ ያለበት ጥያቄ ነው። ይኸንን ጥያቄ የሚሰማሁሉ እይታውን እጎንብሶ ሊያቀረቅር አይችልም። ለጥቂት ለአደንዛዥ እጽዋት መግዣ ወይንም ለተሳሳተ የመንግሥት ትርጉም ግንዛቤ ተገዥ በመሆን በሀፍረት ተከናንቦ ወይንም የሚጨበጠው ግብ፡ ግቡን ለመጨበጥ ለምትገለገልበት መሣሪያ ምክንያታዊ ያደርገዋል በሚል በተሳሳተ ርእየት ምክንያት ወንድሙን በመሸጡ በሃፍረት ለሚኖር ሁሉ የሚቀርብ ጥያቄ ነው።

ቅዱስ አባታችን አክለው የኮሎምቢያን ማኅበራዊ ፈርጆችን ካላቸው ውጣ ውረድም ይሁን ያላቸውንም ክህሎት አንጻር በማሰብም አደራ እናንተ እረኞች እይታችሁ በዚያ ተጨባጩ ሰው ላይ አድርጉ። ሙሉእ ሰባአዊነት ላይ እትኵሩ። እዚህ የተገኘሁት የፍቱን መድሃኒት ማዘዣ ወረቀብ ከናቅረብ ሃኪም ተመስየ ወይንም ደግሞ ልትፈጽሙት ይገባል ብየ የሥራ መርሐ ግብር በቅደም ተከተል ላቀርብላችሁ አይደለም።

በዚህ በአሁኑ ወቅት አመጽ የአልኮል መጠጥ ሱሰኝነት በመሳሰሉት በተለያዩ ምክንያቶች በቋፍ ላይ ያለው የጋብቻው ቃል ኪዳን የአልቦ አባት የሆኑት ቤተሰቦች ሁኔታ መረጋገት መጓደል የሚሰቃየው የጉዲ ፈቻነት ባህል እጅግ የሚሰቃየው ኅብረተስብ፡ በነፍሰ ባዶነት ስጋት ውስጥ የሚገኙትን እንደ መፍትሔ አደንዛዥ እጸዋት መምረጥ ለሚል የተሳሳተ አማራጭ ፊት ለፊት የተደቀነበትን ወጣቱን የኅብረተሰብ ክፍል በማሰብ ለዚህ ሕዝብ ቅርብ ብቻ ሳይሆን ወንድምህ የት ነው የሚለው የጌታ ጥያቄ ከህሊናችን ሳናወጥ ቅርብ መሆን ነው፡

ለካህናት ለገዳማውያን ሁሉ የተሟላ ሕንጸት በማሳሰብ ቅርበታቸውንም በማረጋገጥ ከዚያ ለወንጌላዊ ልኡክነት ምች ከሆነው ከማንኛውም ዓይነት ዓለማዊነት እንዲጠነቀቁ መክረው ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን ኮሎምቢያ ለዚያች ለአገሪቱ ጠባቂ ለሆነቸው ለቅድስተ ማርያም ዘሮዛሪየም ቺኵይንኵይራ በማወከፍ ከማጠቃለላቸው በፊት፥ በአማዞን ያለችውን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን በማሰብ ቁሳዊነትና እንደ ሁኔታው ለሚለው አመለካከት ተገዥ ለመሆን ፈተና የተጋለጠውን ኅብረተሰብ በነጻ ከእግዚአብሔር የተጸገወለትን ሁሉ ለመበዝበዝ ሳይሆን ፍርያማ ማድረግ በሚል ተግባር ተፈጥሮን ያክብር አደራ።

የአማዞናዊው ክልል አገሬዎች ቋንቋ ጓደኛ የሚለው ቃል ሁለተኛው እጄ በሚል ቃል ነው የይሚገልጡት ስለዚህ አደራ ለአማዞን ክልል ሁለተኛ እጅ እንድሁንለት። ኮሎምቢያ አማዛናዊው ክልልዋን ልትጎዳ አይገባትም። በማለት ያስደመጡት ቃል አጠቃሏል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.