2017-09-07 16:43:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለሐዋርያዊ ጉዞ ወደ ኮሎምቢያ


ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ወደ ኮሎምቢያ የሚያከናውኑት ዓለም ዓቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት ዋዜማ በኮሎምቢያ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፥ እንደ የሰላም መንፈሳዊ ነጋዴ ወደ እናንተ በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ የድምጸ ርእየት መልእክት አስተላልፈዋል።

እንደ የተስፋና የሰላም ነጋዲ ወደ እናንተ ፡ ከእናንተ ጋር አብሬ በጌታ ያለን እምነት ለመቀደስ  ከእናተ የፍቅር ሥራን በሰላምና በውህደትን ፈላጊነት ጽናታችሁ ለመማር ወደ እናንተው አቀናለሁ” በማለት ለኮሎምቢያ ሕዝብ መልእክታቸውን በማስተላለፍ፡ በዚህ እ.ኤ.አ. ከ መስከረም 6 ቀን እስከ መስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚያከናውኑት ሐዋርያዊ ዑደት መንፍሳዊ መርሆው በሰላም ጉዞ “የመጀመሪያው እርምጃ ከእኛ ይጀምር”  የሚል ሲሆን፡ ወድማማችነትን ለመገንባት እንዲቻል አገናኝ ድልድይ እናቁም፡  አዳዲስ የሰላም ተኪዶዎችን እንፍጠር ብለዋል።

እንደሚታወቀውም በኮሎምቢያ የነበረው የእርስ በእርሱ ግጭት አልባት እንዲያገኝ በግንባር ቀደም አቢይ አስተዋጽኦ ሰጥተዋል። ተስፋ ያደረገበት የሰላሙ ስምምነትም ተደርሷል። “ሰላም ካለ መታከት ኮሎምቢያ የምትሻውና ዘወትር የምትጓጓው ሁነት ነው። ዘወትር እንደ ጠላት በዓይነ ቁራኛ ካለ መተያየት በወንድማማችነት መንፈስ ለመኖርና ለመደጋገፍ ዘላቂነት ያለው ሰላም እንሻለን። ሰላም የዚያ የሚያፈቅረንና የሚያጽናናን የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን ያስታውሰናል።”

“ኮሎምቢያ የሰላምና ውህደታዊ ስምምነት የነገሰባት የወንድማማችነት አገር ትሆን ዘንድ ካለ መታከት አበክረው በቆራጥነትና በጽናት የተጉት የአገሪቱ ዜጎች ላሳዩት ጥረት ተገቢ እውቅና በመስጠት፡ ቤተ ክርስቲያን በበኩልዋም ሁሉም ከጌታ ጋር ለመስታረቅ ይኸንን ዕርቅ በማነቃቃት ብቻ ሳይሆን ከዚያ የሰው ልጅ ጭካኔ በተሞላው ተግባር ከሚበዘብዘው ተፈጥሮ ጋር እንዲታረቅም ታነቃቃለች።”

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ያንን ኮሎምቢያ ለ 50 ዓመት ያደማው 260 ሺሕ ዜጎች ለሞት ሌሎች ከ60 ሺህ በላይ የሚገመቱትም ለመበታተን 7 ሚሊዮን ለስደትና ለመፈናቃል አደጋ የዳረገው በመንግሥት ወታደሮችና ፋርክ በሚል አህጽሮተ ቃል የሚታወቀው የኮሎምቢያ አብዮታዊው ታጣቂው ኃይል መካከል የተካሄደው ጦርነት ባለፉት ቀናት በመንግሥትና በታጣቂው ኃይል መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት አማካኝነት እልባት አግኝቱል። ሆኖም ያንን በጦርነት የወደመው ሰብኣዊነትና ንብረት ለማነጽ ብዙ ጥረት ይጠይቃ። ይኽ ቅዱስ አባታችን በቀዳሚነት እንዲደረስ ብዙ አስተዋጽኦ የሰጡበት ሰላምና መረጋገት በኮሎምቢያ ለሚፈጽሙት ሐዋርያዊ ዑደት አቢይ ምክንያት ነው። በኮሎምቢያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤቶረ ባለስትረሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በቅርቡ አካሂደዉት በነበረው ቃለ ምልልስ፥ እውነትና ምሕረት ሚዛን ያደረገ ዘላቂነት ያለው አብሮነትና ውህደትን እንጂ ያንን ያለፈው ግጭትና ጦርነት ሚዛን ያደረገ እርቅ ለሰላም ምክንያት አይሆንም፡ ስለዚህ ይቅር ለማለት ለመታረቅና ሰላም ለማረጋገጥ ሌላው ሳይሆን ፈቃደኛነቱ ከእያንዳንዳችን መጀመር አለበት፡ ሌላው ይቅደም ሳይሆን በሰላም ጉዞ እኔ የመጀመሪያውን እርምጃ ፈጻሚ ሆኜ መገኘት አለብኝ፡ ስለዚህ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የኮሎምቢያው ሐዋርያዊ ዑደት አጠር ባለ አገላለጥ ይኽን ይመስላል ብለው እንደነበርም ይታወሳል።

 

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዛሬ ጧት ለሐዋርያዊ ዑደት ወደ ኮሎምቢያ ከመነሳታቸው በፊት ሁሌ ከሚፈጽሙት ሐዋርያዊ ዑደት ዋዜማ እንደሚያከናውኑት ይኸው እ.ኤ.አ. መስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ሮማ ወደ ሚገኘው ወደ ባዚሊካ ሳንታ ማሪያ ማጆረ (ወደ አቢዩ ባዚሊካ ቅድስተ ማርያም) በመሄድ Salus Populi Romani - የሮማውያን ደህንነት በሚል ስያሜ በሚታወቀ የቅድስት ማርያም ቅዱስ ምስል ፊት ተገኝተው በኮሎምቢያ የሚፈጽሙት ሐዋርያዊ ዑደትና መላ በዚህ ጉዞ የሚሸኙዋቸውን እንዲሁም መላውን የኮሎምቢያ ሕዝብ ለማርያም ማወከፋቸውንም የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል፡ የተላለፈው መግለጫ ከዚሁ ጋር በማያያዝም ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀትር በፊት ልክ ከጠዋቱ 5 ሰዓት ወደ ኮሎምቢያ ከመነሳታቸው ቀደም በማድረግ እንደ ተለመደው @Pontifex በተሰየመው ትዊተር ማኅበራዊ መረብት ባለው አድራሻቸው አማካኝነት ዕለታዊ የሚስተላልፉት መልእክታቸውን በመቀጠል “ውዶቼ አደራ ስለ እኔና ለዚያች ሰላም እና እርቅ ምልክታውን ያደረገው ሐዋርያዊ ዕደት ስለ ምፈጽምባ አገረ ኮሎምቢያ ጸልዩ” የሚል መልእክት መልቀቃቸው ያመልክታል።

 

አሁንም ከዚሁ ርእስ ሳንወጣ አጠር በማድረግ የአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት በኮሎምቢያ ታሪካዊ ሂደቱን እንመልከት፥ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመልክቶ እንደሚገኘው ኮሎምቢያን አገር የጎበኙት የመጀመሪያው ር.ሊ.ጳጳሳት ብፁዕ ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድተኛ ናቸው።

ጳውሎስ ስድስተኛ ይኸንን ሐዋርያዊ ንግደት እ.ኤኤ. ከነሐሴ 22 ቀን እስከ ነሐሴ 25 ቀን 1968 ዓ.ም. ያካሄዱት ሲሆን። በዚህ ጉብኝታቸውም ለ 200 የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ማዕርገ ክህነትና ማዕርገ ዱቁና የፈጸሙበት ለአርሶ አደር የአገሪቱ ማኅበረሰብ መሥዋዕተ ቅዳሴ የሠሩበት የመላ ላቲን አመሪካና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሁለተኛው ይፋዊ ሰብሰባውን በይፋ ያስጀመሩበት አዲሱን የዚሁ ጳጳሳዊ ጉባኤ ሕንፃ የመረቁበት ከተለያዩ አቢያተ ክርስቲያንና ከአይሁድ እምነት ተከታይ ማኅበረሰብ ጋር ግኑኝነት ያካሄዱበት በጠቅላላ የተለያዩ 20 ክንዋኔዎችን ፈጽመዋል።

አገረ ኮሎምቢያ የጎበኙት ሁለተኛው ር.ሊ.ጳ. ደግሞ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ናቸው። ዮሓንስ ጳውሎ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 1 ቀን እስከ ሐምሌ 8 ቀን 1986 ዓ.ም. ርእሰ ከተማ ቦጎታን ያስቀደመ በጠቅላላ በአገሪቱ ከሚገኙት ሰበካዎች ውስጥ በአስራ ሁለቱ ጉብኝት አካሂደዋል። ኮሎምቢያ ለቅድስት ማርያም ጥበቃ ያወከፉበት በቅድስተ ማርያም ዘቺንኩይከራ መሥዋዕተ ቅዳሴ የሠሩበት በበጎታና በመደሊን ክፍለ ከተማ ከሚኖሩት እጅግ በድኽነት ከተጠቁት ጋር በመገናኘት የቤተ ክርስቲያን ቅርበትና ድጋፍ ያረጋገጡበት ከመላ በላቲን አመሪካ ከሚገኙት መንፈሳዊ ገዳማትና ወንጌላውያን ልኡካን ማኅበር አባላት ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር ከመላ የላቲን አመሪካና የካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ አገረኛው ቅዱስ ፐድሮ ክላቨር ቅዱስ አጽም ወዳረፈበት ስፍራ በመሄድ ጸሎት ያሳረጉበትና በአገሪቱ ለሚገኙት በመላይ የአገሪቱ የመገናኛብዙኃን በኩል የተሰራጨው ለእስረኞች ያስተላለፉት መልእክት ያጠቃለለ 30 ክንዋኔዎችን ፈጽሟል።

በመቀጠልም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ኮሎምቢያን የሚጎበኙ ሦስተኛ ብቻ ሳይሆኑ የመጀመሪያው የላቲን አመሪካ ተወላጅ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትም ናቸው። ቅዱስነታቸው በዚህ እ.ኤ.አ. ዛሬ መሰክረም 6 ቀን የጀመረውና መስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም. በኮሎምቢያ በሚፈጽሙት 20ኛው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት፥ ከኮሎምቢያ መንግሥት የመንግሥት አበይት አካላት ከኮሎምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፡ ከመላ ላቲን አመሪካና ካሪቢያን ብፁዓ ጳጳሳት ምክር ቤት አስፈፃሚ አካላት ጋር፡ አራት አበይት መሥዋዕተ ቅዳሴዎችን ለእግዚአብሔር አገልጋይ ኸሱስ ኤሚሊዮ ኻራሚሎን ሞንሳቨና ለፐድሮ ማሪያ ራሚረዝ ራሞስ ብፅዕና የሚያውጁበት መሥዋዕተ ቅዳሴ የተለያዩ የጸሎት መርሐ ግብሮች፡ ሆጋር ኾሴ የተሰየመው ማደጎ ቤተ ጉብኝት፡ በቅዱስ ፐድሮ ክላቨር ቅዱስ ሥፍራ ከኮሎምቢያ ውሉደ ክህነት አባላትና ገዳማውያን ካህናት ልኡካነ ወንጌል ጋር ግኑኝነት ያካተተ በጠቅላላ ከአሥር በላይ የተለያዩ ይፋዊ የግንኙነት መርሐ ግብሮች ይፈጽማሉ።

በኮሎምቢያ የዛሬ አሥር ወር በፊት የተደረሰው የሰላም ስምምነት መሠረት ያደረገ ብሔራዊ እርቅ እንዲጸና ለማድረግ ያቀዱ ምዕዳኖች ይለግሳሉ ተብሎም ይጠበቃል።

የተከበራችሁ አድማጮቻችን ቅዱስ አባታችን በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ አምስት ሰዓት ተኩል ቦጎታ በሚገኘው አየር ማረፊያ ይደርሳሉ ተብሎም ይጠበቃል።

መላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ አባታችን በዚህ በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት በጸሎት በመሸኘት አብራ ከሳቸው ጋር በመሆን ስለ እርቅና ሰላም ትጸልያለች።








All the contents on this site are copyrighted ©.