2017-08-30 16:51:00

ተስፋችንን ያነስራራ ዘንድ በቅድሚያ ከኢየሱስ ጋር በተገናኘንበት ወቅት የነበረንን ደስታ ማስታወስ ያስፈልጋል


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሳምንት አንድ ቀን ርዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኚዎች የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነ የዛሬው ቀን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮዋቸው ከዚህ ቀደም የክርስቲያን ተስፋ በሚል አርእስት ታደርጉት አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በተለይም ደግም ተስፋ እና ማስታወስ በሚሉት ቃላት መካከል ያለውን ግንኙነት በማጉላት በዩሐንስ ወንጌል 1 ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራት እና ክቡራን የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ቅዱስነታቸው በዛሬው ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደረጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ ኣንጋብዛለን።

 

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው እለት አስተምህሮ አንድ በጣም አስፈላጊ የሆነ አርእስት ላይ ለማትኮር እፈልጋለሁ፥ ጥሪያችንን ማስታወስ የሚለውን ከግንዛቤ በማስገባት ተስፋ እና ማስታወስ በሚሉት ቃላት መካከል ያለውን ግንኙነት ለመዳሰስ እሞክራለሁ። ለዚህም ማጣቀሻ ይሆነኝ ዘንድ በመጀመሪያ የተጠሩትን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በዋቢነት ማንሳት እፈልጋሉ። የማስታወስ ችሎታቸው በጣም የሚደነቅ ነበር ምክንያቱከቀትር ቡኃላ አሥር ሰዓት ያህል ነበረበማለት የተጠሩበትን ሰዓት እንኳን ሳይቀር መዝግበው ይዘውት ነበር። (ዩሐንስ 1:39) ወንጌላዊው ዩሐንስ ወጣት በነበረበት ጊዜ እንዴት እንደ ተጠራ በስተርጅናውም ወቅት ጠንቅቆ ያስታውሰው ነበር ማለት ነው።

ይህ ግንኙነት የተፈጸመው አጥማቂው ዩሐንስ ያጠምቅ በነበረበት በዮርዳኖስ ወንዝ አከባቢ ሲሆን በዚያን ወቅት እነዚያ ወጣቶች መንፈሳዊ መንገዳቸውን ለመጀመር ይጠመቁ ነበር። አንድ ቀን ኢየሱስ ወደ እዚያው መጥቶ ተጠመቀ። በሚቀጥለውም ቀን በዚያው አከባቢ በሚያልፍበት ወቅት አጥማቂው ዩሐንስ ለሁለቱ ደቀ መዛሙርት “እነሆ የእግዚኣብሔ በግ” በማለት ተናገረ (ዩሐንስ 1:36)።

ለእነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርት ይህ ቃል “ብልጭታን ፈነጠቀ”። የቀድሞ መምህራቸው የነበረውን አጥማቂው ዩሐንስን በመተው ኢየሱስን መከተል ጀመሩ። ኢየሱስም ወደ እነርሱ ዞር ብሎ በመመልከት “ምን ትፈልጋላችሁ?” በማለት አንድ ወሳኝ የሆነ ጥያቄ ያቀርብላቸዋል። ኢየሱስ የሰውን ልብ ጠንቅቆ የሚያውቅ ሊቅ ተደርጎ በወንጌል ውስጥ ተግልጹአል። በዚያን ጊዜ እርሱን በንጹህ ልብ ይፈልጉት የነበሩ ሁለት ወጣቶችን አግኝቱዋል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ምንም ዓይነት ትርጉም የሌለው ደስታ ያለው ወጣት ምን ዓይነት ወጣት ነው? ምንም ነገር ለመፈለግ የማይነሳሳ ወጣት ወጣት ሊባል አይችልም። ከእድሜያቸው ቀድመው እንዳረጁ ይቆጠራሉ። በአራቱ ወንጌላት ውስጥ እንደ ተጠቀሰው ኢየሱስ በየመንገዱ ላይ የሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ልብ ውስጥ እሳት ጭሮ የሚያልፍ ነው። ከእዚህ ነው እንግዲህ  የወጣት ልጆችን የሕይወትና የደስታ ፍላጎትን ለማምጣትና ለማነሳሳት የሚያስችል "ምን ትፈልጋለህ?" የሚለው ጥያቄ የሚነጨው እና የሚያስፈልገውም ለዚሁ ነው።

የዩሐንስ እና የእንድሪያስ ጥሪ የመነጨውም ከዚሁ ነው፣ ወዳጅነት ከኢየሱስ ጋር ለመጀመር እና ከእርሱ ጋር ያለንን ሕብረት ለማጠናከር የሚበጅ ጠንካራ የሆነ ጅማሬ ነው። ሁለቱ ደቀ ማዛሙርት ከኢየሱስ ጋር መኖር ይጀምራሉ ኑሮዋቸውም ወደ ተልዕኮ በፍጥነት ሲቀየር እናያለን። የእነርሱ ወንድሞቹ የሆኑት ስምዖን እና ያዕቆብ በቅርብ ጊዜ እነርሱም መጥተው እንደ ሚቀላቀሉዋቸውም እርግጥ ነው። ይህ ከኢየሱስ ጋር አድርገውት የነበረው ግንኙነት ልብን የሚነካ፣ ደቀ መዛሙርቱ እስከ ዘለዓለም የማይረሱት ቀናቸውን ብሩህ ያደረገ እና የወጣትነት ስሜታችውን ያነሳሳ ግንኙነት ነበረ።

እንዴት ነው ታዲያ እኛ የየራሳችንን የግል ጥሪ በዚሁ መልክ ልናስታውስ የምንችለው? ይህንን በብዙ መንገድ ልናስታውሰው የምንችለው ጉዳይ ቢሆንም ቅሉ፣ ነገር ግን በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ እንደ ተጠቀሰው ይህንን በሚገባ ማስታወስ የምንችለው በቅድሚያ ከኢየሱስ ጋር በተገናኘንበት ወቅት የነበረንን ደስታ በማስታወስ ነው። በምስጢረ ተክሊል በተፈጸመ ጋብቻ፣ የተቀደሰ ሕይወት ወይም የክህነት ሕይወት ውስጥ ያለን ሰዎች ከሆንን እያንዳንዱ ጥሪ የሚጀምረው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በሚደርግ ግንኙነት በመሆኑ የተነሳ ደስታን እና አዲስ የሆነ ተስፋን ይሰጠናል። እንዲሁም በመከራ እና በፈተናዎች ውስጥ በምንገባባቸው ወቅቶች ሁሉ እነዚህን ተግዳሮቶች እንድንወጣ በማድረግ ከእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት ምልአት ያለው እንዲሆን በማድረግ የተሟላ ድስታ እንዲኖረን ያደርጋል።

ጌታ እርሱ ተከታይ የሆኑ ሰዎች ልባቸው በደስታ ሳይሞላ ወደ ኃላ እንዲመለሱ አፍልግም። ኢየሱስ ከእርሱ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ከእርሱ ጋር መኖራቸው ደስታ የሚሰጥ እና ሕይወትን የሚያድስ መሆኑን እንዲለማመዱ ይፈልጋል፣ አንድ የእግዚኣብሔር መንግሥት ደቀ መዝሙር የሆነ ሰው ደስታ የሌለው ከሆነ ዓለምን በፍጹም ሊቀይር አይችልም። ጥሩ ሰባኪ ሊሆን ይችል ይሆናል ነገር ግን በሰዎች ዓይን ውስጥ የደስታን ብርሃን መፈኝተቅ ካልቻለ ግን አስቸጋሪ ይሆናል።

በዚህ ምክንያት ክርስቲያን - ልክ እንደ ድንግል ማርያም - የእርሱን የፍቅር የእሳት ነበልባል ይጠብቃል። እርግጥ ነው በሕይወታችን ውስጥ ፈተናዎች ይኖራሉ፣ እርግጥ ነው በቅዝቃዜ እና በኃይለኛ አውሎ ንፋስ ውስጥ መጓዝ የግድ ሊለን ይችል ይሆናል። ነገር ግን ክርስቲያኖች ወደ ቅዱስ እሳቱ የሚያደርሰውንና አንድ ጊዜ ተከፍቶ ለዘለዓለም የሚቆየውን መንገድ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ያዘኑ እና ደስተኝ ኣያልሆኑ ሰዎች ጋር በቀጥታ አንሄድ ይሆናል፣ በተንኮታኮተ ሕይወት ውስጥ በመግባት ተስፋ ወደ ቆረጡ ሰዎችን አንሰማቸው ይሆናል፣ ማንኛውም ሰው የትኛውም የእድሜ ልክ የህይወት ዘመኑ ምንም ዋጋ እንደሌለው በሚናገሩበት ወቅት ምንም ዓይነት ቅንዓት አይሰማንም ይሆናል፣ የወጣትነት ዘመናቸውን ታሪክ ሊተነፍሱ የሚፈልጉትን “የእድሜ ባለጸጋዎች” አናዳምጣቸውም ይሆናል፣ ከእነዚህ ይልቅ ምናባዊ የሆኑ ነገሮችን እንፈልጋለን፣ ነገር ግን እግዚኣብሔር በጥንቃቄ ወደ እውነት በመጓዝ እንደ እርሱ እና ከእርሱ ጋር እንድናልም ይፈልጋል። ለየት ባለ መልኩ እንድናልም ይፈልጋል። አንደኛው ሕልማችን በሚቋረጥበት ወቅት፣ ተስፋን እና የመጀመሪያ ግንኙነታችንን በማስታወስ እንደ ገና አዲስ ሕልም እንድናልም ይፈልጋል።

ኢየሱስን ማስታወስ፣ የእርሱን የፍቅር እሳት ይህም የክርስቲያን ሕይወት መሰረት ነው፣  

እናም የክርስትና ሕይወት መሠረታዊ ተነሳሽነት ይህ ነው፡ ኢየሱስ ሆይ, አንድ ቀን ሕይወታችንን እንደ አንድ መልካም መርሃ ግብር አድርገን በመቁጠር ያንተ የፍቅር እሳት ተስፋችንን በማለምለም በፍቅር ነበልባል ይሙልናን።

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ይህ ቀደም ሲል ያዳመጣችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደርጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት ነበር አብራችሁን በመሆን ስላደመጥእችሁን ከልብ እናመስግናችኃለን።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.