Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

እያንዳንዳችን ቤተ ክርስቲያንን በመገንባት ጊደት ውስጥ የራሳችንን ሚና ልንጫወት ይገባል !

ቅዱስነታቸው በቫቲካን በሚገኘው በቅ. ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመና የወንጌል አስተንትኖ ባደረጉበት ወቅት። - ANSA

28/08/2017 14:59

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኚዎች በእለቱ በላቲን ሥርዓት አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በሚነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የዚህ መርዐ ግብር አንዱ ክፍል በሆነው በትላንትናው እለት ማለትም በነሐሴ 21/2009 ዓ.ም. ያደረጉት አስተንትኖ ከማቴዎስ ወንጌል 16:13-20 ላይ የተወሰድውና የሐዋሪያው ጴጥሮስ እምነትና ምስክርነት ዙሪያ በሚያጠነጥነው የወንጌል ክፍል ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

 ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛችኃለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው ቀን የተነበበል ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በመጓዝ ላይ በነበረበት ወቅት ለእነርሱ አቅርቦላቸው የነበረውን ቅልፉ የሆነ ጥያቄ ያመልክታል፣ በዚህም ጥያቄው ደቀ መዛሙርቱ በእርሱ ላይ የነበራቸውን እምነት ምን ያህል ደረጃ ላይ ደርሶ እንደ ነበረም ለመረዳት ፈልጎ ያቀረበው ጥያቄ ነበር። በቅድሚያም ሰዎች ስለእርሱ ምን እንደ ሚያስቡ ለማወቅ ፈልጎ ነበር፣ በእርግጥ ሰዎች የእርሱን ማንነት በጥልቀት ሳይረዱ፣ የእርሱን ሕይወት ምእከል እና ተልዕኮ በሚገባ ሳይረዱት ከነቢያት አንዱ እንደ ሆነ አድርገው ይቆጥሩት ነበረ። ከዚያም በመቀጠል በልቡ ውስጥ የነበረውን ሌላኛውን ጥያቄ “እናንተስ እኔን ማንት ትሉኛላችሁ?” በማለት ለደቀ መዛሙርቱ ያቀርብላቸዋል። “እናንተስ” በሚለው ቃል ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከተቀሩት ተከታዮቹ ከነበሩ ሰዎች ይለያቸዋል፣ ይህም ማለት እናንተ ሁል ቀን ከእኔ ጋር የነበራቸው ሰዎች፣ እናንተ እኔን በሚገባ የምታውቁ ሰዎች፣ ከሌሎች ሰዎች በተሻለ ስለእኔ ምን ተገነዘባችሁ? ለማለት ፈልጎ ያቀረበላቸው ጥያቄ ነበር። ጌታ ከተቀረው ሕዝብ አስተያየት የተሻለ እና የበለጠ ነገር የእርሱ ከሆኑ ወገኖቹ ይጠብቃል። በእርግጥ ስሞዖን ጴጥሮስ “አንተ የሕያው እግዚኣብሔር ልጅ የሆንህ መሲሕ ነህ!” የሚለው ቃል የወጣውም በዚሁ ምክንያት ነው። ስምዖን ጴትሮስ ከእርሱ አቅም በላይ የሆነ ቃል፣ ከእርሱ ተፍጥሮአዊ ችሎታ ልቆ የሚታይ ቃል የወጣውም በዚሁ ምክንያት ነው። ምን አልባትም ስምዖን ጴጥሮስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት እንኳን የተከታተል ሰው ባይመለኝም ይህንን ታላቅ የሆነ የእምነት ምስክርነት ግን ለማደርግ ችሎ ነበር፣ ለዚህም ነው ኢየሱስ ይህንን የገለጠልህ በሰማይ ያለው አባቴ ነው እንጂ ሰው አይደለም በማለት ከዓስራ ሁለቱ አንዱ የሆነው እና በቀዳሚነት ስለ ኢየሱስ በይፋ “በእውነት አንተ መሲሕ፣ የሕያው የእግዚኣብሔር ልጅ፣ ዓለም ለማዳን የመጣህ ነህ” በማለት ለመመስከር ግን ችሎ ነበር። ይህንን እመነት ለሰጠው ለእግዚኣብሔር ምስጋ ይግባው እና ከዚህ ምላሽ ኢየሱስ አንድ ተጨባጭ ቤተ ክርስቲያኑን የሚገነባበት መሰረት ማግኘቱን ተረድቶ ነበር። ለዚህም ነው “ጴጥሮስ አንተ አለት ነህ! በዚህችም የመሠረት ድንጋይ ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ” በማለት ኢየሱስ የተነጋረው።

ዛሬም ቢሆን ኢየሱስ ከእኛ ጋር በመሆን ጠንካራ መሠረት የሌላቸውን፣ እንከን ያለባቸውን፣ ጥገና የሚያስፈልጋቸውን አብያት አክርስቲያናት አብረን እንድንገነባ ይፈልግል። ሁልጊዜም ቢሆን ልክ የአሲዚው ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘመን እንደ ነበረው ሁሉ ቤተ ክርስቲያን መታደስ፣ መሻሻል እና መጠገን ይኖርባታል። በእርግጥም እኛ ዐለት የሆንን ሰዎች መስሎ አይሰማንም ይሆናል፣ ነገር ግን ትናንሽ ጠጠሮች ነን። ይሁን እንጂ ትናንሽ የሆኑ ጠጠሮች ጥቅም የላቸው ግን ማለት አንችልም፣  ይሁን እንጂ እነዚህ ትናንሽ ጠጠሮች በጌታ እጅ የተከበሩ ናቸው፣ ምክንያቱም የሚሰበስበው እርሱ ነው፣ በርኅራኄ የሚመለከተው እርሱ ነው፣ በመንፈሱ የሚያድሰው እርሱ ነው፣ በትክክለኛው ስፍራ የሚያስቀምጠውም እርሱ ነው፣ እርሱ ቀደም ሲልና አሁንም ቢሆን በየተኛው ሥፍራ ጠቃሚ እንደ ሆንን ያውቃል በዚያም ያኖረናል።

እያንዳንዳችን አንደ አንዲት ትንሽ ጠጠር ነን፣ ነገር ግን በኢየሱስ እጅ ውስጥ ስንገባ በቤተ ክርስቲያን ግንባታ ሂደት ውስጥ እንድንሳተፍ ያደርገናል። ሁላችንም ትንሽ እንሁን ትልቅ “ሕያው አለት” ነን፣ ምክንያቱ  ኢየሱስ የራሱ የሆኑትን አለተቶች በእጁ በሚያስገባበት ወቅት፣ የራሱ በማድረግ ሕያው ያደርጋቸዋል፣ በመንፈስ ቅዱስ እና በፍቅሩ አማክይነት የተትረፈረፈ ሕይወት እንድንኖር በማድረግ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እና በቤተ ክርስቲያን ተልዕክ ውስጥ ሥፍራ እንዲኖረን ያደርጋል፣ እርሱዋም በብዙ ትናንሽና የተለያዩ በሆኑ ጠጠሮች ስብስብ የተገነባች ሕንጻ በመሆን የወንድማማችነት እና የሕብረት መገለጫ ስፍራ ትሆናለች።

በሌላ በኩል ደግሞ በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ከሐዋሪያ ጴጥሮስ ጋር ህብረት የምንመሰርትበት ማዕከላዊ እንብርት እንድትሆንም ፈልጉዋል። እርሱም ቢሆን (ማለትም ሐዋሪያው ጴጥሮስ ማለት ነው) ትንሽ የሆነ አለት የነበረ ቢሆንም ቅሉ፣ በኢየሱስ በመመረጡ የተነሳ የሁሉም መአከል ለመሆን በቅቱዋል። ከሐዋሪያ ጴጥሮ ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ እለት ድረስም ቢሆን ተመሳሳይ የሆነ ኃልፊነት የተሰጣቸው የጴጥሮስ ተከታይ የሆኑው የሮም እና የመላው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን ሐዋሪያት ጴጥሮስ እና ጳውሎስም ደማቸውን በማፍሰስ መስዋዕት የሆኑበት በሮም ከተማ ይገኛሉ።

እነርሱንም የሐዋሪያት ንግሥትና የቤተ ክርስቲያን እናት ለሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በአደራ መልክ ልንሰጥ ይገባል።  መንፈስ ቅዱስ በሐዋሪያቱ ላይ በእሳት አማሳል ወርዶ ቅዱስ ወንጌልን ለማወጅ እንዲወጡ በዳረገበት ወቅት ማሪያ ከጴጥሮስ አጠገብ ተቀምጣ ነበር። ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በአማላጅነቷ ከእኛ ጋር በመሆን ብራታን ትሰጠናለች፣ ምክንያቱ ኢየሱስና የእርሱ ደቀ መዛሙርቱ የፈልጉት ዓይነት ሕብረት በምልአት እውን የሆን ዘንድ ነው።

28/08/2017 14:59