2017-08-24 09:01:00

ክርስቲያናዊ ተስፋ የሚመነጨው በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ አዳዲስ ነገሮችን በሚፈጥረው በእግዚብሔር ላይ ባለው እምነት ነው።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሳምንት አንድ ቀን ርዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኚዎች የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የዚህ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው የዛሬው ቀን ማለትም የነሐሴ 17/2009 ዓ.ም አስተምህሮዋቸው ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በዩሐንስ ራእይ 21:5-7 ላይ በተጠቀሰው “በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውም፣ “እነሆ፤ እኔ ሁሉን ነገር አዲስ አደርጋለሁ” አለ፤ ደግሞም፣ “ይህ ቃል የታመነና እውነት ስለ ሆነ ጻፍ” አለ። እንዲህም አለኝ፤ “ተፈጸመ፤ አልፋና ዖሜጋ፣ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እኔ ነኝ፤ ለተጠማ ከሕይወት ውሃ ምንጭ ያለ ዋጋ እሰጣለሁ። ድል የሚነሣ ይህን ሁሉ ይወርሳል፤ እኔም አምላክ እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል” በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘተ ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው ቀን ያደረጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛችኃለን

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ ቀደም ሲል ከዩሐንስ ራእይ ተወስዶ በተነበበው ምንባብ ላይ “እነሆ፤ እኔ ሁሉን ነገር አዲስ አደርጋለሁየሚለውን የእግዚኣብሔር ቃል አዳምጠናል። ክርስቲያናዊ ተስፋ የሚመነጨው በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ አዳዲስ ነገሮችን በሚፈጥረው በእግዚብሔር ላይ ባለው እምነት ነው። የእኛ እግዚኣብሔር አዳዲስ የሆኑ ነገሮችን በመፍጥር የሚያስደንቀን አምላክ በመሆኑ የተነሳ ነው። አዲስ እና ድንቅ የሆነ ክስተት ይፈጥራል።

አሳማዎች ሁልጊዜ ወደ መሬት ወይም ወደታች እየተመለከቱ እንደ ሚጓዙ ሁሉ ክርስቲያኖችም እንደ አሳማዎች ሳይሆን አንገታቸውን ወደ ላይ ቀና አድርገው መጓዝ ይኖርባቸዋል። ሁሉም ነገር እዚሁ ከጥቂት ሜትሮች ቡኃላ ያበቃ ይመስል፣ ሕይወታችን ምንም መዳረሻ ወይም ማረፊያ የሌለው ይመስል ወደ ፊት ከመጓዝ ይልቅ ያለምንም ምክንያት ወደ ኃላ መመልስ እንፈልጋለን። ይህ ግን የአንድ ክርስቲያን ተግባር ሊሆን አይገባም።

የመጽሐፍ ቅዱሳችን የመጨረሻው መጽሐፍ አማኞች ወደ ላይ ቀና በማለት ሰማያዊቷን ኢየስሩሳሌምን ይመለከቱ ዘንድ አደራ ይለናል። እርሷም እግዚኣብሔር ሁላችንንም ሰብስቦን እስከ ዘለዓለም አብረነው እንድንኖር የምያደርግበት ሰማያዊቷ ድንኳን ተደርጋ  ተመስላለች። የእኛ ተስፋ ያረፈው በዚሁ ላይ ነው። ደግሞስ እግዚአብሔር በጨረሻ ቀን ከእርሱ ጋር በምንሆንበት ወቅት ምን ሊያደርገን ይችላል? ለረጅም ጊዜ ሲታገሉና ሲሰቃዩ የነበሩትን ልጆቹን በደስታ እንደሚቀበል እንደ አንድ አባት ዘላለማዊ ጥንካሬን ይሰጠናል። ዩሐንስ በራእዩ “እነሆ፤ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሰዎች መካከል ነው፤ እርሱ ከእነርሱ ጋር ይኖራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔር ራሱም ከእነርሱ ጋር ይኖራል፤ አምላካቸውም ይሆናል። እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት ወይም ሐዘን ወይም ልቅሶ ወይም ሥቃይ አይኖርም፤ የቀድሞው ሥርዐት ዐልፎአልና” ይለናል። እግዚኣብሔር አዲስ ነገር የመፍጠር ብቃት አለው!

ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስሜታዊ በሆነ መንገድ ለማሰላሰል ሞክሩ፡ ነገር ግን በቴለቪዢን መስኮቶች እና በጋዜጦች የፊት ገዞች ላይ ስትመለከቱ በጣም ብዙ አሳዛኝ ነገሮች፣ ሲነገሩ ስናይ እራሳችን በእዛ ሁኔታ ውስጥ በማስገባት እንመልከት። በባርሴሎና በደረሰውን አሳዛኝ ድርጊት ሰላባ የሆኑ ሰዎችን  አስቢያለው ወይ?! በኮንጎ አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ያሉትን ሰዎች አስበናል ወይ! በተለያዩ መከራ ውስጥ ያሉ ሰዎችን አስበናል ወይ?! እስቲ ፊታቸው በጦረንት ምክንያት የተጎሳቆሉ ሕጻናትን፣ የእናቶችን ለቅሶ፣ ሕላማቸው ከንቱ ሆኖ የቀር ወጣቶችን፣ በጣም አደገኛ የተባሉ ጎዞዎችን የሚያደርጉ ስደተኞችን ለማሰብ ሞክሩ። ያለ መታደል ሆኖ ሕይወት አንድ አንዴ ይህንን ይመስላል። አንድ አንድ ጊዜም ይህንን የግድ መወጣት ይገባኛል ማለት ይኖርብናል።

ከእኛ ጋር ሆኖ የሚያልቅስ አባት አለን ወይ? ለልጆቹ ሲል እንባውን የሚያንጠፈጥፍ አባት አለን ወይ? ብለን ልንጠይቅ እንችል ይሆናል። ከእኛ ጋር ማልቀስ የሚችል አባት አለን። ልያጽናናን የሚጠብቀን አባት አለን፣ ምክንያቱም መከራዎቻችንን ስለሚያውቅና ለወደፊቱ ጊዜያችን ለየት ያለ ነገር ስላዘጋጀልን ነው።  በእነዚያ መከራዎቻችን ውስጥ ሁሉ ሆነን ወደፊ እንድንራመድ እና እንድናድግ የሚያደርገን የክርስቲያን ትልቁ የተስፋ ራእይ ይህ ነው።

እግዚአብሔር ራሳችንን እና ሕይወታችንን በከፍተኝ ኣጭንቀት ውስጥ በመክተት ሕይወታችን ወደ ስህተት ውስጥ እንዲገባ አይፈልግም። እግዚኣብሔር ፈጥሮናል፣ የፈጠረንም እንድንደሰት ነው። እኛ አሁን እግዚኣብሔር የሚፈልገውን ዓይነት ሕይወት እየኖርን ካልሆንን ልጁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ቤዛ አድርጎ በመላክ ለኃጢኣታችን ስርኄት እንደ ሚሰጠን ያረጋግጥልናል። እርሱ ሁል ጊዜም የሚሠራው እኛን ለማዳን ነው።

እኛ ሞት እና ጥላቻ በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ የሚከሰቱ የመጨረሻዎች ክንውኖች ናቸው ብለን አናምንም። ክርስቲያን መሆን ማለት አዳዲስ አመለካከቶችን ማጸባረቅ ማለት ነው፣ ይህም በተስፋ የተሞላ አዲስ ምልከታ ነው። አንዳንዶች ሕይወት በወጣትነት ዘመን እና ባለፉት ጊዜያት ውስጥ ተከናውኖ ያለፈ ነገር እንደ ሆነ አምነው ያ የደስታ ዘመንና ሕይወት አሁን የለም ይላሉ። ሌሎች ደግሞ አሁንም ቢሆን ደስታችን ውስብስብ እና ጥልቅ ስሜት ያለው እንደ ሆነ ይሰማቸዋል፣ እናም በሰዎች ሕይወት ውስጥ ስሜትን ሊፈጥር የሚችል ነገር ነው ይላሉ። በመከራ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ደግሞ “ሕይወት ለእኛ ትርጉም የለውም። እኛ የያዝነው መንገድ ስሜት አይሰጥም ብለው ያምናሉ። ነገር ግን በአንጻሩ ከሰዎች ራስ በላይ ሁል ጊዜ ብርሃን የሚሰጥ ፀሐይ እንዳለ እናምናለን። መልካም የሚባሉ ጊዜያት እንደ ሚመጡም እናምናለን።

ሁልጊዜም ቢሆን ችግሮች፣ አለመግባባቶች፣ ጦርነቶች፣ በሽታ . . .ወዘተርፈ እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ ችግሮች ሁልጊዜም ቢሆን ይከሰታሉ። በውስጣችን ያለው ተክል ያድጋል በመጨረሻም ክፉ ነገሮች ሁሉ ይወገዳሉ።  መጪው ጊዜ የእኛ ባመሆኑ የተነሣ መገመት ቢያዳግተንም ቅሉ፣ ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የሕይወት ጸጋ ሊሰጠን በዚያ እንደ ሚገኝ ግን እናውቃለን፣ በመጨረሻ ሰዓት አቅፎ የሚየዘን የእግዚኣብሔር እጅ እንዳለም እናውቃለን፣ ይህም አሁንም ቢሆን በሕይወታችን ጎዳና የሚያጅበን እና የሚያጽናናን እንደ ሆነም እናምናለን።

ሁሉም ነገር ፍጻሜ ወይም ምልአት በሚያገኝበት ጊዜ፣ እንባችንን ከዓይናችን ላይ ያብሳል “እግዚኣብሔር ራሱ እነሆ፤ እኔ ሁሉን ነገር አዲስ አደርጋለሁ” በማለት ቡራኬውን ይሰጠናል። አዎን የእኛ አባት አዲስ ነገር ሊፈጥር የሚችልና ድንቅ ነገሮችን ለማድረግ የሚችል አምላክ ነው። በእርግጥም በዚያን ቀን ሁላችንም ደስተኞች እንሆናለን እናለቅሳለንም። ለቅሶዋችን ግን የሐዘን ሳይሆን የደስታ ነው። 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.