2017-08-21 14:15:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ "እምነታችንን እና በኢየሱስ ላይ ያለንን መተማመን እያሳደግን መሄድ ይኖርብናል" ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኚዎች በእለቱ በላቲን ሥርዓት አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በሚነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የዚህ መርዐ ግብር አንዱ አካል በሆነው በትላንትናው እለት ማለትም በነሐሴ 14/2009 ዓ.ም. ያደረጉት አስተንትኖ ከማቴዎስ ወንጌል 15:21-28 ላይ የተወሰድውና የከነዓናዊቱዋ ሴት እምነት በሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል። ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛችኃለን።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የዛሬው ቅዱስ ወንጌል ለአይሁዳዊያን እንግዳ የሆነች አንዲት ከነዓናዊት ሴት ከኢየሱስ ጋር መገናኘቷንና የነበራትን ልዩ እምነት በምሳሌነት ያቀርብልናል። ይህም ትዕይንት የተከሰተው ኢየሱስ ወደ ጢሮስ እና ሲዶና በሚጓዝበት ወቅት የነበረ ሲሆን ይቺህ ሴት ወደ ኢየሱስ ቀርባ የዛሬው ቅዱስ ወንጌል እንደ ሚገልጸውልጄ በርኩስ መንፈስ ተይዛ በጣም ትሠቃያለችእባክህን አድናት በማለት እየጮኸች ትለምነው ጀመር። በመጀመሪያ ደረጃ ጌታ የደቀ መዛሙርቱ የምልጃ ድምጽ ጣልቃ እስኪገባ ድረስ ይህንን የስቃይ ጩኸቷን ያልሰማ ይመስል ነበር። ነገር ግን ይህ የኢየሱስ ችላ ማለት ይህቺ ሴት ተስፋ እንድትቆርጥ ግን አላደረጋትም እንዲያውም ይበልጡኑ አጥብቃ እንድትለምነው አድርጓት ነበር።

የዚህች ሴት ውስጣዊ ኃይል እያንዳንዱን መሰናክል አልፋ እንድትሄድ በማድረግ ከእናትነት ፍቅሩዋ በመነሳትና ኢየሱስ የልቧን መሻት እንደ ሚፈጽምላት በመተማመን ፍለጋዋን ቀጥላለች። ይህም ይቺህ ሴት የነበራትን ኃይል እንዳስብ አድርጎኛል፣ ሴቶች በራሳቸው ኃይል ተነሳስተው ብዙ ነገር ማከናውን እንደ ሚችሉም አስይታለች፣ ይህንንም የመሳሰሉ ብዙ ክስተቶች እንዳሉም እናውቃለን። በእዚህች ሴት ውስጥ የነበረው ፍቅር እምነቱዋን አንቀሳቅሶታል፣ እምነቷ ደግሞ ከኢየሱስ ዘንድ የፍቅር ሽልማት አስግኝቶላታል። ለልጅዋ የነበራት ፍቅር  “ጌታ ሆይ፤ የዳዊት ልጅ ሆይ፤ ራራልኝበማለት እንድትጮኽ አነሳስቶዋት ነበር። በኢየሱስ በነበራት ቀጣይነት ባለው እምነት የተነሳ ተስፋ እንዳትቆርጥ አድርጓት የነበረ ሲሆን በዚህም የተነሳ ይቺህ ሴትእግሩ ላይ ወድቃ፣ጌታ ሆይ፤ ርዳኝበማለት የቾኸችሁም በዚህ እምነቷ የተነሳ ነው።

በመጨረሻም ብዙ ጥረቶችን ካደረገች ቡኃላ ኢየሱስ የዚህችን አረማዊ የነበረች ሴት እምነት በጣም አደነቀ። ማድነቁንምአንቺ ሴት እምነትሽ ታላቅ ነው እንደ ፈለግሽው ይሁንልሽ” ካለ ቡኃላ የስቴቲየዋ ልጇ ከዚያ ሰዓት ጀምሮ በመፈወስአድናቆቱን በተግባር አሳይቱዋል። ይቺህ ትሑት ሴት የማይናወጥ እምነት ማሳየቷን ኢየሱስ በዋቢነት ተጠቅሷሶታል። የክርስቶስን ጣልቃ ገብነት በመጠባበቅ ላይ ለሚገኝ ሰው ይህ ታሪክ የሚያስተላልፈው ጥብቅ ማሳሰቢያ አለ።  እኛ በችግሮችና በሕይወት ፈተናዎች ውስጥ በምንገባባቸው ወቅቶች ሁሉ ተስፋ ሳንቆርጥ መለመን እንደ ሚገባን ያስተምረናል ያሳስበናልም። እኛ ችግር ላይ በምንሆንባቸው ወቅቶች ሁሉ ኢየሱስ ፊቱን ከእኛ ወዲያ አያዞርም፣ ነገር ግን አንድ አንድ ጊዜ ፊቱን ከእኛ ያዞረ በሚመስለን ወቅቶች ሁሉ የእምነታችንን ጥልቀት ለመፈተሽ ፈልጎ ሊሆን ስለሚችል እኛ እንደ እዚህች ከነዓናዊት ሴት ሳንሰለች ጩኸታችንን በመቀጠልጌታ ሆይ እርዳኝ፣ ጊታ ሆይ እርዳኝ!” እያልን መጮኻችንን ልንቀጥል ይገባናል። ይህንንም በጽናት እና በብርታት ልናከናውነው ይገባል። የዚህ ዓይነቱ ጽናት እና ብርታት ሁል ጊዜም ቢሆን በምንጸልይበት ወቅት ያስፈልገናል።

ይህ የዛሬው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ሁላችን እምነታችንን እና በኢየሱስ ላይ ያለንን መተማመን እያሳደግን መሄድ እንዳለብን እንድንረዳ ያግዘናል። የሕይወት አቅጣጫ መጠቆሚያ መሳሪያ ወይም ኮፓሳችን በሚጠፋበት ወቅት እርሱ ሕይወታችንን መልሰን እንድናገኝ ያደርገናል፣ መንገዳችን የተስተካከል በማይሆንበት ጊዜ እርሱ ያስተካክለዋል፣ የተሰጠንን የሥራ ኃላፊነት በሚከብደን ሰዓት እርሱ ያግዘናል። ስለዚህም እምነታችንን በእየለቱ በእግዚኣብሔር ቃል፣ ምስጢራትን በመካፈል፣ የግል የሆነ ጸሎት በማድረግ ወደ እርሱጌታ ሆይ እርዳን ብለን በመጮኽናተጨባጭ የሆኑ የፍቅር ተግባራትን ለባልንጅሮቻችን በማከናወን እመነታችንን መኮትኮትና መመገብ ይኖርብናል።

በእመንት እና በጽናት መጓዝ እንችል ዘንድ እንዲረዳን መንፈስ ቅዱስን ልንለምነው ይገባል። መንፈስ ቅዱስ የማያምነውን ልብ አማኝ ወደ ሆነ ልብ ይለውጣል፣ ለሕይወታችን እና ለምናደርገው ክርስቲያናዊ ምስክርነት  ጉልበት ይሰጣል፣ በእግዚኣብሔር ተማምነን መኖር እንድንችል እና ወንድሞቻችንን ችል እንዳንል ይረዳናል።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታ እና መንፈሱ ቅዱስ እንደሚያስፈልጉን ይበልጥ እንድንገነዘብ፣ በፍቅር እንድንሞላና በፍቅር እና በጽናት እግዚኣብሔርን መለመን የምችልበትን ጸጋ እንድንጎናጸፍ  ትርዳን አሜን!

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.