Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ቤተ ክርስትያን \ ኢትዮጵያ

የፍልሰታ ማሪያም አስተምህሮ ክፍል አራት

የፍልሰታ ማሪያም አስተምህሮ ክፍል አራት - RV

17/08/2017 09:43

የፍልሰተ ማሪያም አስተምህሮ ክፍል አራት

እንደ አገራችን ሥርዓተ አምልኮና መንፈሳዊ ልማድ በእመቤታችን በኩል እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ስለገለጠው ተስፋና በእርስዋም ጸጋ መሞላት ላደረገልን ቸርነት በተለየ ሁኔታ በየዓመቱ ለ16 ቀናት የሚዘለቀወን ጾምና ምህለላ የምናደርግበት የፍልሰታ ዘመን ላይ እንገኛለን። እግዚአብሔር አብ በእርሱ ለኖሩት ሁሉ ሊያደርግላቸው ቃል የገባውን እውነታ እርሱ በፈቀደው መልኩ በእመቤታችን የተገበረበትን ጸጋ እንወድሳለን፤ ለእኛም ይሆንልን ዘንድ “ማርያም ሆይ! ቸር፣ የሰው ልጆች ሁሉ አዳኝ ወደ ሆነው ልጅሽ ለምኝልን/ በማለት የእናትነት አማላጅነቷን የምንማጽንበት የፍልሰታ ወቅት ላይ እንገኛለን።

ኢየሱስ ወደ ዚህ ምድር መቶ ተስቃይቶ ተሰቅሎ መሞቱን እና በሦስተኛው ቀን ከሙታን መነሳቱን በሚዘከርበት የእርገት ቀን መካከል እና ማሪያም ወደ ሰማይ የፈለሰችበት አጋጣሚዎች ግን የተለያዩ እንደ ሆነ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጠንቅቀን እንድንረዳ አደራ ትለናለች። የእግዚኣብሔር ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣  ሞትን ድል ነስቶ ወደ ሰማይ የወጣው በመለኮታዊ ኃይሉ አማክይነት ሲሆን ነገር ግን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያ ወደ ሰማይ የፈለሰቺው በእግዚኣብሔር መለኮታዊ ኃይል እንደ ሆነ ልብ ሊባል ይገባል።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ በቁጥር 966 ላይ “በመጨረሻም ንጽሕት ድንግል ማሪያም ከአዳም ኃጢያት ሁሉ ተጠብቃ የምድራዊ የሕይወቷ ጉዞ ሲያበቃ በነብስ እና በስጋ ወደ ሰማያዊ ክብር ተወሰደች። የጌቶች ሁሉ ጌታ ከሆነውና ኃጢኣትንና ሞትን ካሸነፈው ከልጇ ጋር አንድነቷ ይበልጥ የተሟላ መሆንኑን ለመመስከር በሁሉም ነገሮች ላይ ንግሥት ሆና በጌታ ከበረች”።  የብፅዕት ድንግል እርገት በልጇ ትንሣኤ ያደረገችሁ ልዩ ተሳትፎ ከመሆኑም በላይ የሌሎች ክርስቲያኖች ተስፋ ነው” ይላል።

የእግዚኣብሔር እናት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ከመጀመሪያው ማለትም ከጽነሰቷ እለት ጀምሮ ያለ አዳም ኃጢኣያት የተጸነሰች ናት የሚለው አስተምህሮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዶግማ ወይም አንቀጸ-እምነት የማይለወጥ የማይሻር አስተምህሮ ተደርጎ በወቅቱ በነበሩት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በፒዮስ 9ኛ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1854 ዓ.ም። በተወሰነበት ወቅት በወቅቱ የነበሩ ምዕመናን ልብ በደስታ ተሞልቶ እንደ ነበረና ከዚያም በመቀጠል ማሪያም በሥጋና በነፍስ ወደ ሰማይ መፍለሱዋም በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ውስጥ ይካተታል የሚል ተስፋ አድሮባቸው ነበር።

ለቁጥር የሚያዳግቱ በጣም ብዙ የሚባሉ በዓለም ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መጠሪያቸውን ከማሪያም ስም ጋር በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የተያያዘ ነው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን የማሪያምን ሥም በእየለቱ በመጥራት አማላጅነቷን ይማጸናሉ። በሚልዮን የሚቆጠሩ የማሪያም ምስል የያዙ ቅርጻቅርሶች በእየቤቱ በእየቤተክርስቲያኑ በእየሰው አንገትም ላይ ሳይቀር ተሰቅለው ወይም ተንጠልጥለው ማየት የተለመደ ነው።

በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እምነት እና ባሕል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያ ከፍተኛ የሆነ ቦታ ተሰጥቱዋት ገዳማት፣ አብያተ ክርስቲያናት ሳይቀሩ በስሟ ተገንብቶላት ከፍተኛ ክብር እየሚሰጣት የቤተክርስቲያን እናት ናት፣ አማላጅነቷንም ሁል ጊዜ እንማጸናለን። የእመበታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም አካባሪ የነበረውና ማሪያም በሥጋ እና በነብስ ወደ ሰማይ ፈልሳለች የሚለው አስተምህሮ እውነት እና ትክክለኛ አስተምህሮ ነው የሚል ጽኑ አቋም የነበረው የደማቆው ቅዱስ ዩሐንስ ስለማሪያም መፍለስ እንዲህ ብሎት ተናግሮ ነበር “ከወለደችም ቡኃላ ድንግልናዋን ጠብቃ የቆየች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ከሞተችም ቡኃላ እንኳን ሰውነቷ ሊበስበስ አይገባውም” ይለናል።

“የፈጣሪን ልጅ የተሸከመች፣ ከጡቷም ያጥባችሁ እናት በመለኮታዊ ድንኳን ውስጥ ለዘለዓለም ልትኖር ይገባታል።  እግዚኣብሔር ለልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ የመረጣት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በመለኮታዊ ሥፍራ ልትኖር ይገባታል። ልጇን በመስቀል ላይ ያየች እና ልጇን በመለደችበት ወቅት ያየቺውን ስቃይ በማስታወስ የጭንቀት ሰይፍ ልቡዋን የወጋት እናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም፣ አሁን ደግሞ ከአባቱ ጋር ሲቀመጥ እሱን ማየት ይኖርባታል። የአምላክ እናት የልጇን ውርስ ልትወርስ ይገባታል፣ እንዲሁም  እናትና የአምላክ ድንቅ ሥራ ውጤት በመሆኑ የተነሳ  በፍጥረታት ሁሉ ዘንድ ልትከበር ይገባታል።” በማለት የደማቆው ቅዱስ ዩሐንስ ለማሪያም ያለውን ክብር በመግለጽ በሥጋ እና በነፍስ ወደ ሰማይ መፍለሷን በማመን ያመነውንም በማስተማር እውነታውን ያጠናክራል።

17/08/2017 09:43