Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ፍትሕና ሰላም

ደቡብ ሱዳን፥ ብፁዕ አቡነ ኩሳላ፥ የጋራ ውይይት እንዲረጋገጥ ከህዝብ ጎን ለመሆን የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት

ደቡብ ሱዳን፥ ብፁዕ አቡነ ኩሳላ፥ የጋራ ውይይት እንዲረጋገጥ ከህዝብ ጎን ለመሆን የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት - ANSA

14/08/2017 15:48

ባለፉት የመጨረሻ ወራቶች በደቡብ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት እልባት እንዲያገኝ ተደርሶ የነበረው የቶክስ አቍም ስምምን ጥሰት ተከትሎ እየታየ ያለው ፖለቲካዊ ውዝግብ በአገሪቱ ያለው ሁኔታ እጅግ የተወሳሰበና የከፋ እንዲሆን እያደረገ መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ፈደሪኮ ፒያና አስታወቁ።

የጦርነቱ ምክንያት ፖለቲካዊ ሳይሆን ጎሳዊና ባህላዊ ነው ሲሉ የሱዳይ የቶምቡራና ያምቢዮ ሰበካ ጳጳስ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ኤድዋርድ ሂቦሮ ኩሳላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።

እኛ የምንፈልገው ይላሉ ብፁዕነታቸው፥ ደቡብ ሱዳን እንደ አገር የሚያጸናት ስምምነት ሰላም ፍትህ እንዲረጋገጥ እንጂ የአገሪቱን ሕዝብ ጨርሶ ኑሮውን እንዲያሻሽል የማያደርገው የፖለቲካው ሥልጣንና የአገሪቱን ሃብት ለመቆጣጠር የሚደረግ ፍጥጫና የርእስ በእርስ ግጭት አይደለም

በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሱዳንን ለመጎብኘት ያላቸው ፍላጎት ገሃድ አድርገዋል። ሆኖም በአገሪቱ ምድር ላይ ያለው ሁኔታ ግምት በመስጠት ሐዋርያዊ ጉብኝቱን እ.ኤ.አ. በዚህ በ 2017 ዓ.ም. ይከወናሉ ብሎ ለመናገሩ የሚያዳግት ቢሆንም በደቡብ ሱዳን የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ግብኝቱ እንዲከናወን የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንዲረጋገጡ በማድረጉ ረገድ አቢይ ጥረት እያከናወነች እንደምትገኝ ገልጠው ተስፈኛም ነች ብሏል።

አሁንም ቢሆን በደቡብ ሱዳን ያለው ሁኔታ እጅግ የከፋ ነው። ምንም’ኳ የሰላም ውይይት ቢከናወንም በመንግሥት ወታደሮችና አማጽያኑ መካከል ግጭቱ አልረገበም ጦርነቱም እልባት አላገኘም፡ የዚህ ጦርነት ሰለባም ንጹሓን ዜጎች ናቸው። በደቡብ ሱዳን ስቃይና ችግር የማይታይበት ክልል አንድም የለም ምክንያቱም ጦርነቱ እንደ ወረርሽኝ በሁሉም ክልል እየተዛመተ ነው፡ ይኽ ደግሞ ለሚሰቃየው ሕዝብ መሰረታዊ ፍልጎቶቹን ለማርካት በሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ የሚያስችሉ መርሃ ግብሮች ለመከወን አዳጋች እንዲሆን እያደረገ ነው። የቤተ ክርስቲያን አቋም የሰላም መሣሪያ በመሆን ሰላምና እርቅ እንዲረጋገጥ ማድረግ የሚል የግብረ ገብና ድምጽ ለሌለው ድምጽ በመሆን የሰላም ውይይት በማረጋገጥ የአገሪቱና የሕዝቡ ጥቅም መረጋገጥ አለበት የሚል ነው፡ ሆኖም ለዚህ ለምታደርግው ጥረት ከማንኛውም አካል አወንታዊ ምላሽ አልስተሰጠበትም ይላሉ።

በደቡብ ሱዳን ያለቸው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ታጣቂ ኃይሎች ከመንግሥት ጋር እንዲደራደሩ ለመገፋፋት ተጨባጭ ተግባሮችን እያከናወነች ትገኛለች። ጦርነቱ እስካለ ድረስ የአገሪቱ መንግሥት የሕዝብ መሰረታዊ ፍላጎት ለማርካትም ሆነ የአገልግሎት መስጫ ተቋሞች የተሟላ ለማድረግ አይቻልም። በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ቤተ ክርስቲያን ቀዳሚው ሥፍራ ይዛ ብትገኝም ረጅ አካላት የክልሉ ጦርነት ቀጣይ በመሆኑ ምክንያት እያሰለቻቸው ያለ ይመስላል፡ ያአገሪቱ መንግሥትና ታጣቂ ኃይሎች ጦርነቱን ለማቆም ፍላጎት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል። ይኽ ጦርነት ለመግታት የሚለው ፍላጎት ጦርነቱ እልባት እንዲያገኝ ለሚደረገው ጥረት ውሳኝ ነው፡ ካልሆነ የርእር በእርሱ ጦርነት ለማስወገድ አይቻልም ብሏል።

ሕዝቡ ምግብም ሆነ የሕይወት ደህንነት እንዲያገኝም መጠለያ ለማግኘት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይጎርፋል። ቤተ ክርስቲያን አብራው የስቃዩ ተካፋይ በመሆን የሰላም ጥሪ ከማቅረብ አልቦዘነችም ዘወትር ከሚሰቃየው ሕዝብ ጋር ነች በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።

14/08/2017 15:48