2017-08-11 10:26:00

"መለኮታዊ ምሕረት የክርስቲያን ተስፋ መሰረት ነው" ር.ሊ.ጳ .ፍራንቸስኮ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኚዎች በተለያዩ አርእስቶች ዙሪያ የትምህረተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የዚሁ መርሀ ግብር አንዱ አካል በሆነው በሐምሌ 3/2009 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ያደረጉት የትምህረተ ክርስቶስ አስተምህሮ ትኩረቱን ያደረገው በሉቃስ ወንጌል 7:36-50 ላይ የነበረ  ሲሆን በዚሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ አንዲት ሴት የኢየሱስን እግር ሽቶ መቀባቷን በሚያመለክተው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህን አስተምህሮ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

 

በእለቱ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል ሉቃስ 7:36-50

“ከዚህ በኋላ ከፈሪሳውያን አንዱ ምግብ አብሮት እንዲበላ ኢየሱስን ጋበዘው፤ እርሱም ወደ ፈሪሳዊው ቤት ሄዶ በማእድ ተቀመጠ። በዚያ ከተማ የምትኖር አንዲት ኀጢአተኛ ሴት፣ ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት በማእድ መቀመጡን በሰማች ጊዜ አንድ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ሽቶ ይዛ መጣች፤ ከበስተ ኋላው እግሩ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች እግሩን በእንባዋ ታርስ፣ በራሷም ጠጒር ታብሰው ጀመር፤ እግሩንም እየሳመች ሽቱውን ቀባችው።

የጋበዘውም ፈሪሳዊ ይህን ባየ ጊዜ፣ይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ፣ የነካችው ሴት ማን እንደሆነች፣ ደግሞም ምን ዐይነት ሰው እንደሆነች ባወቀ ነበር፤ ኀጢአተኛ ናትናብሎ በልቡ አሰበ። ኢየሱስም፣ “ስምዖን ሆይ፤ የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። እርሱም፣መምህር ሆይ፤ ንገረኝአለው።

ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “ከአንድ አበዳሪ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ አንደኛው አምስት መቶ ዲናር፣ ሁለተኛው ደግሞ አምሳ ዲናር ነበረበት። የሚከፍሉትም ቢያጡ ዕዳቸውን ለሁለቱም ተወላቸው። እንግዲህ ከሁለቱ አበዳሪውን አብልጦ የሚወደው የትኛው ነው?” ስምዖንም፣ብዙው ዕዳ የተተወለት ይመስለኛልሲል መለሰ።

ኢየሱስም፣ “ትክክል ፈርደሃል” አለው።

ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፤ “ይህቺን ሴት ታያታለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ አንተ ለእግሬ ውሃ እንኳ አላቀረብህልኝም፤ እርሷ ግን እግሬን በእንባዋ እያራሰች በጠጒሯ አበሰች። አንተ ከቶ አልሳምኸኝም፤ እርሷ ግን ከገባሁ ጀምራ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም። አንተ ራሴን ዘይት አልቀባህም፤ እርሷ ግን እግሬን ሽቶ ቀባች። ስለዚህ እልሃለሁ፤ እጅግ ወዳለችና ብዙው ኀጢአቷ ተሰርዮላታል፤ በትንሹ የተሰረየለት ግን የሚወደው በትንሹ ነው።

ኢየሱስም ሴቲቱን፣ “ኀጢአትሽ ተሰርዮልሻል” አላት። አብረውት በማእድ ተቀምጠው የነበሩ እንግዶችም፣ይህ ኀጢአትን እንኳ የሚያስተስረይ እርሱ ማን ነው?” ብለው በልባቸው አሰቡ። ኢየሱስም ሴቲቱን፣ “እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ” አላት” (ሉቃስ 7:36-50)

 

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደረጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ

ከፈሪሳውያን አንዱ ምግብ አብሮት እንዲበላ ኢየሱስን በቤቱ በጋበዘው ወቅት አብረውት በማእድ ተቀምጠው የነበሩ ፈሪሳዊው  ስምዖን እንግዶችይህ ኃጢአትን እንኳ የሚያስተስረይ እርሱ ማን ነው?” (ሉቃ. 7:49) ብለው ተናግረው እንደ ነበር ከዛሬው ቅዱስ ወንጌል ሰምተናል።  ኢየሱስ ይህንን ተግባር በፈጸበት ወቅት በዚያ የነበሩ ሰዎች የአሉባልታ ወሬ ሰለባ ሆኑዋል። በዚያ ከተማ የምትኖር አንዲት በሁሉም ዘንድ የምትታወቅ ኃጢአተኛ ሴት፣ ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት በማእድ መቀመጡን በሰማች ጊዜ አንድ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ሽቶ ይዛ መጣች፤ እግሩንም እየሳመች ሽቱውን ቀባችው። ይህንን የተመለክቱት በዚያ የነበሩ ሰዎችይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ፣ የነካችው ሴት ማን እንደሆነች፣ ደግሞም ምን ዐይነት ሰው እንደሆነች ባወቀ ነበር፤ ኀጢአተኛ ናትናበማለት  በዚያ ግብዣ ላይ የነበሩ ሰዎች ማጉረምረም ጀመሩ። በእርግጥ በዚያን ወቅት ቅዱስ በሆነ ሰው እና ኃጢአተኛ በሆነ ሰው መካከል፣ ንጹዕ በሚባል ሰው እና ባልነጻ ሰው መካከል፣ ያለው ልዩነት ግልጽ በሆነ መልኩ ሊቀመጥ የገባዋል የሚል አስተሳሰብ ነበረ።

ነገር ግን ኢየሱስ ያሳየው ከእዚህ አስተሳሰብ ለየት ያለ ባሕሪ ነበረ። አገልግሎቱን በይፋ ከጀመረበት ከገሊላ አንስቶ እርሱ በለምጽ በሽታ የተጠቁ ሰዎችን፣ ክፉ መንፈስ የተጠናወታቸው ሰዎች፣ የታመሙትን እና የተገለሉ ሰዎችን ይቀርብ ነበር። የዚህ ዓይነቱ ባሕሪ ግን ወቅቱ የተለመደ ባሕሪ አልነበረም፣ እውነት ነው ኢየሱስ ለተገለሉ ሰዎችና ሰዎች ለመንካት እንኳን ለሚጸየፉቸውን ሰዎች የሚያሳየው ርኅራኄ በዚያን ዘመን የነበሩትን ሰዎች የሚረብሹ ተግባር መሆኑ እሙን ነው። አንድ ሰው በሚሰቃይበት ወቅት ኢየሱስ የዛን ሰው ስቃይ የራሱ በማድረግ ያን ሰው ይንከባከበዋል። አንድ ሰው ማንኛውም ዓይነት የቅጣት ሁኔታ በጀግንነት መቋቋም አለበት ብሎም አልሰበከም። ማንኛውንም የተቸገረ ሰው በሚገናኝበት ወቅት ኢየሱስ የሰዎችን መከራ በመካፈል የክርስቲያን መገለጫ ባሕሪ የሆነውን ምሕረቱን ያሳያቸዋል። በግርዱፉ ሲታይ የዚህ ዓይነት ሁኔታ ስያጋጥመው ኢየሱስ አንጀቱን ይበላዋል። ይህንንም ተግባሩን በቅዱስ ወንጌል ውስጥ በብዙ ቦታዎች ውስጥ እናገኘዋለን። ኢየሱስ የነበረው የልብ ዓይነት የእግዚኣብሔር ልብ  መገለጫ የነበረ ሲሆን በዚህም ምክንያት አንድ ወንድ ወይም ሴት በሚሰቃዩበት ሥፍራ የእነርሱን ፈውስ የሚመኝ፣ የእነርሱን ነጻ መውጣት የሚፈልግ፣ ምልአት ያለው ሕይወት እንዲኖሩ የሚፈልግ የሥጋ ልብ ነበር የነበረው።

ኢየሱስ እጆቹን ለኃአጢያተኞች የሚዘረጋው በዚሁ ምክንያት ነው። ዛሬም ቢሆን በእግዚኣብሔር ልብ ተሞልተው ይህም ማለት በተስፋ ተሞልተው የሚመራቸውና መንገድ የሚያሳያቸው ሰው በማጣታቸው የተነሳ በተሳሳተ ጎዳና ላይ የሚረመዱ ብዙ ሰዎች አሉ። ኢየሱስ ግን በጣም ብዙ የተባለ የተከማቼ ስህተት ያላቸውን ሰዎች ሳይቀር ከዚህ ሸክማቸው የሚያላቅቃቸው የትንሣኤ እድል ይሰጣቸዋል።

ከዚህም እግዚኣብሔር ቤተክርስቲያኑን የመሰረተበት ምክንያት መቼም ቢሆን የማይሳሳቱ ሰዎች ለመሰብሰብ ብቻ ፈልጎ እንዳልሆነ እንረዳለን። ቤተክርስቲያን ማለት ኃጢኣተኛ የሆኑ ሰዎች የእግዚኣብሔርን ምሕረት እና ይቅርታ የሚያገኙበት ሥፍራ ማለት ነው።  ጴጥሮስ ያከናውናቸው የነበረው መልካም ሥራዎቹ ልቡን በማሳበጥ ከሌሎች የበላይ እንደ ሆነ የሚሰማው ስሜት እንዲያስወግድ ያደረገውና ስለራሱ ማንነት እውነታውን የተረዳው ዶሮ በጮኸበት ወቅት ነበር።

ኃጢኣተኞች ከኃጢኣታቸው የሚነጹት በዚሁ መልኩ ነው። ኢየሱስ የተሳሳተ የሕይወት መንገድ ለነበራቸው ሰዎች ሁሉየአዲስ ሕይወት ተስፋ ይሰጣቸዋል፣ በፍቅር የተሞላ ሕይወትም ያጎናጽፋቸዋል። ቅራጭ የነበረው ማቴዎስ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ሆኑዋል። የኢየሪኮ ሀገር ሰው የነበረው ሀብታም ሙሰኛው  ዘኪዮስ፣ ለድኾች የበጎ አድርጎት ተግባር የሚፈጽም ሰው ሆኑዋል።  የሰማሪያ ሀገር ሰው የነበረችሁና ከዚህ ቀደም አምስት ባሎች የነበሩዋት ነገር ግን አሁን ከአንዱ ጋር ብቻ እየኖረች የነበረቺው ሴት “ጌታዬ፤ እንዳልጠማና ውሃ ለመቅዳት እንዳልመላለስ፣ እባክህ ይህን የሕይወት ውሃ ስጠኝ” (የሐንስ። 4:14) በማለት መንፈሳዊ ጥማቱዋን ገልጻለች።

ሁላችንም ምስኪን ኃጢኣተኞች  በመሆናችን የተነሳ ሊቀይረን የሚችል ኃይል ያለውና በእየለቱ  ተስፋ የሚሰጠን የእግዚኣብሔር ምሕረት ያስፈልገናል። ይህንን መሰረታዊ እውነተ ለተገነዘቡ ሰዎች እግዚኣብሔር በዓለም ውስት ውብ የሆነ ተልእኮን ይሰጣቸዋል፣ ይህም ማለት ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን እርሱ ለማንም የማይከለክለውን ምሕረቱን ማወጅ ነው።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.