2017-08-07 15:13:00

እስያ አቀፍ የካቶሊክ ወጣቶች ቀን


ከሃያ አንድ የእስያ አገሮች የተወጣጡ ካቶሊክ ወጣቶች ያሳተፈው በኢንዶነዢያ ርእሰ ከተማ ጃካርታ የተካሄደው እስያ አቀፍ ሰባተኛው የካቶሊክ ወጣቶች ቀን እ.ኤ.አ. ሐምሌ 30 ቀን ተጀሮ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ.ም.  መጠናቀቁ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ይኽ ጃካርታ በሚገኘው ወታደራዊ አየር ማረፊያ አደባባይ የአገሪቱ ምክትል ርእሰ ብሔር ጁኡፍ ካላ በተገኙበት ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የተጠናቀቀው የእስያ አገሮች ካቶሊክ ወጣቶች ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ፊርማ የተኖርበት ባስተላለፉት መልእክት፥ የእስያ ካቶሊክ ወጣቶች በእምነትና በጽናት መልስ የሚሰጡበት ከጌታ የሚቀርብላቸውን ጥሪ በጥልቅ እንዲያዳምጡ አደራ በማለት ወጣቶች የማርያም ለጋስነት እነሆኝ ባይነት እራስነትን በሙላት ለጌታ እቅድ የማቅረቡን አርአያ አስተንፍሶ በማድረግ ሐዋርያትና ልኡካነ ወንጌል እንዲሆኑ ለማርያም አፍቃሪው እናትነት ገዛ እራሳቸውን እንዲያወክፉና በእርሷ አማላጅነትም እንዲጸልዩ ማሳሰባቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎ አስታወቀ፡

ይኽ በኅብረ ባህል በሆነችው እስያ ወንጌል መኖር በሚል ቃል ሥር ተመርቶ የተካሄደው የእስያ ካቶሊክ ወጣቶች ቀን በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የፊሊፒንስ ርእሰ ከተማ ሊቀ ጳጳስ የተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራትን የሚያቅፈው በካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ለሚጠራው ማኅበር ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ልዊስ አንቶኒዮ ታግለ፥ በእስያ ካቶሊክ ወጣቶች ቀን ሲገኙ ለሦስተኛ ጊዚያቸው እንደሆነ በማስታውስ፡ በዚህ ኅብረ ባህልና ኅብረ ሃይማኖት በሚኖርበት ክፍለ ዓለም የሚኖሩት ካቶሊክ ወጣቶች እርስ በእርስ በመገናኘት ባህል በመኖርና ኅብረአዊነት የሚያቀራርብ ለመተዋወቅ የሚገፋፋ ክብር መሆኑ በማስተዋል ልዩነት የሰላም መሣሪያ እንዲያደርጉ በስፋት ጥሪ የቀረበበትና በዚህ ጉዞም የሕይወት ምስክርነት የቀረበበት ውይይት መከባበርና መቀራረብ ለአንድ ኅብረተሰብ ለሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ መሠረት ነው፡ ልዩነት የመገነጣጠል የመከፋፈል የማግለያ መሣሪያ ሳይሆን የአንድ ኅብረተሰብ የሥልጣኔዊ ሃብት መሆኑ ይኽ የተካሄደው የእስያ ካቶሊክ ወጣቶች ቀን ተጨባጭ ምስክር ነው ብሏል።

ኢንዶነዢያ ለሁሉም የእስያ አግሮች አቢይ ትርጉም ያላት አገር ነች። ምክንያቱም የኢንዶነዢያ አገር አበው አገሪቱ የኅብረ ባህል የኅብረ ሃይማኖት አገር እንድትሆንና የሕሊና ነጻነት ሁሉም የሚከተለውን ሃይማኖት በመኖር ከጥልቅ ሃይማኖታዊ ክብር በመደርደር አብሮ ይኸንን ያላትን ኅብረአዊነት በማክበር እንድትኖር ያደረጉ በመሆናቸው፡ ይኽ እሴት ለሁሉም እስያ አገሮች አብነት ነው፡ በመሆኑም ይላሉ ብፁዕነታቸው፥ በጃካርታ የተካሄደው የእስያ ካቶሊክ ወጣቶች ቀን የተዋጣለት የኅብረ ባህልና ኅብረ ሃይማኖት ለመቀራረብ መሠረት መሆኑ አስረግጦ መስክሯል።

ለማቀራረብ የሚያስችል እድል መፍጠር እንጂ የሚለያይ ግንብ ሰላም የሚያረጋግጥ ሳይሆን እርስ በእርስ ተፈራርቶ ለመኖርና ለከፋ ማኅበራዊ ሰብአዊ ችግር የሚያጋልጥ መሆኑ ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች። ልዩነት ለማቀራረብ የሚያነቃቃ አቢይ ውስጣዊ ግፊትና እድል እንደሆነ የሚያተኵር ኅብረተሰብ ሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ይኖረዋል። ለዚህም ነው ልዩነት የሚያገናኝ ሃብት እንጂ ለያይ አጥር አስገንቢ ምክንያት ሊሆን አይችልም የሚባለው። ባህላዊም ይሁን ሃይማኖታዊ ልዩነት ለመተዋወቅ የሚገፋፋ ጉጉት እንጂ ለመገነጣጠል በጠላትነት መንፈስ ለመተያየት የሚገፋፋ ምክንያት ሊሆን እንደሚያይገባው ያሳሰቡት ብፁዕ ካርዲናል ታግለ አያይዘው፥ ድኾችን የማይረሳ ወደ የክልሎችና የህልውና ጥጋ ጥግ ክልል የሚል ኅብረተሰብ የመገናኘት ባህል ድኻውንና የተነጠለውን በተለያየ ምክንያት ተነጥሎ እንዲኖር የተግደደውን ማቅረብ የሚለው በተደጋጋሚ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚያስተላፉት ሥልጣናዊ ትምህርት ካልታከለበት በእውነቱ ሰላማዊ የአብሮ መኖር ባህል እውን ማድረግ አይቻልም።

በዓለማችን የሚታየው ህልውናዊ ባህላዊ ኤኮኖሚያዊ ተገሎነት እንዲቀረፍ ተገሎ ወደ ሚኖረው ማቅናትና ለተገለለው ቅርብ መሆን ያስፈልጋል። በተለያየ መልኩ የሚታየው ሕዳጣንነት ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናንዋ ለአስፍሆተ ወንጌል ምክንያት መሆን አለበት። አብላጫው ሃይማኖትም ይሁን አብላጫው ባህል ለሕድጣኑ አምባገነን መሆን የለበትም እንዳውም ሕዳጣኑ ባህሉንና ሃማኖቱን እንዲኖር በማድረግ ኅብረአዊነት ሃብት መሆኑ እንዲመሰክር የሚያነቃቃ መሆን ይገባዋል። ይህ በሃይማኖት ብቻ ሳይሆን በሁሉም መስክ ሊኖር የሚገባው ክብር ነው፡ ይኽ እሴት በኢንዶነዢያ የተካሄደው ሰባተኛው የእስያ ካቶሊክ ወጣቶች ቀን በትክክል መስክሮታል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።     








All the contents on this site are copyrighted ©.