2017-08-05 10:07:00

የማሮናይት ጳጳሳት በሊባኖስ የሚኖሩ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ዘንድ ዓለማቀፋዊ እቅድ እንዲወጣ አሳሰቡ።


የሊባኖስ የሲቪል ተቋማት በሊባኖስ በመኖር ላይ የሚገኙ የሶሪያ ስደተኞችን ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ የሚያመቻች "በዓለም አቀፍ ደረጃ እቅድ" እንዲወጣ አበክረው መሳሰባቸው ተገለጸ። ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት በትላንትናው እለት በሊባኖስ የሚገኙ ያማሮናይት ስርዓተ አምልኮን በሚከተሉ የምስራቃዊያን አብያተ ክርስቲያናት ብጹዐን ጳጳሳት ወራዊ ስብሰባቸውን ባጠናቀቁበት ወቅት በፓትሪያርክ ቤካራ ብሮስ ራይ መሪነት በተደረገው የመዝጊያ ዝግጅት ላይ እንደ ነበረም የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ጳጳሳቱ እንደገለጹት የስደተኞችን አስቸኳይ ሁኔታ ለመቆጣጠር የሚያስችል አጠቃላይ ዕቅድ አለመኖሩ በሊባኖስ ሕዝብ ላይ ትልቅ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን ገልጸዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በሊባኖስ የሚኖሩ የሶሪያ ስደተኞች በሊባኖስ መንግሥት፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቢሮዎች እና ተቋማት እንዲሁም በተለያዩ የበጎ አድረጎት ሰጭ ተቋማት የተመዘገቡ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞ በሊባኖስ እንደ ሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፣  ከዚህም ባሻገር በዓለማቀፋዊ ድርጅቶች ወይም በሊባኖስ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ተቋማት ያልተመዘገቡ ሌሎች ብዙ ስደተኞች እንደ ሚገኙ የተገለጸ ሲሆን ይህም ከሀገሪቷ የመሸከም አቅም በላይ የሆነ በመሆኑ ማኅበራዊ ቀውስ እያስከተለ በመምጣቱ የተነሳ አስቸኳይ የሆነ ምፍትሄ እንዲፈለግለት ጥሪ አቅርበዋል።

ይህንን በተመለከተ የማሮናይት ፓትርያርክ የሆኑት ፓትሪያርክ ቤካራ ብሮስ ራይ በሐምሌ 9/2009 ዓ.ም ለሊባኖስ ፕሬዚዳንት  ሚሼል አኡን በሳን የዚህ ጉዳዩን አሳሳቢነት የሚያመለክት መልእክት መላካቸውም ተገልጹዋል።

“እኛ የሊባኖስ ሕዝቦች ለስደተኞች ያለንን አጋርነት እና ድጋፍ አሁንም እያሳየን እንገኛለን” ያሉት ፓትሪያርክ ቤካራ ብሮስ ራይ ከዚህ ባሻገር ግን ይህ በስደተኞች አማካይነት እየተፈጠረ የሚገኘው ማኅበራዊ የሆነ ቀውስ በዘላቂነት የሚፈታው ርዳታን በተቀላጠፈ መልኩ በማቅረብ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የፖለቲካ መድረኮችን በመክፈትና በተለያዩ ባላንጣ አካላት መካከል ያለውን ልዩነት በውይይት በመፍታት፣ በእየ ሀገራቸው ሰላም እንዲረጋገጥ በማድረግ፣ ስደተኞቹም ወደ እየሀገራቸው በደህና እንዲመለሱ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ያስፈልጋል በማለት የዓለማቀፉ ማኅበረሰብ የበኩሉን አስተዋጾ እንዲያደርግ ጥሪ አቅረበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.