2017-08-04 16:21:00

መክሲኮ፥ የካህናትና የጋዜጠኞች ሕይወት ለአደጋ መጋለጥ


ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በመከሲኮ ሲቲ በሚገኘው ካቲድራል መሥዋዕተ ቅዳሴ ፈጽመው እንዳበቁ ባልታወቁ ሰዎች በጩቤት ተወግተው ከባድ የመቁሰል አደጋ ያጋጠማቸውና በህክምና ሲረዱ የቆዩት አባ ኾሴ ሚገል ማቾሮን ጨምሮ በዓለማችን ጠቅላላ እ.ኤ.አ. በ 2017 ዓ.ም. 10 ካህናት መገደላቸውና በመሲኮ አራት፡ አንድ ካህን በቨነዝወላ ሌላው አንድ ካህን ደግሞ በኰሎምቢያ መገደላቸውና ሌሎች ካህናት ደግሞ በማዳጋስካር በብሩንዲ ሁለት ደግሞ በካመሩን በጠቅላላ በአፍሪቃ አራት ካህናት እንዲሁም በቦሊቪያ በደቡብ ሱዳንና በናይጀሪያም በጠቅላላ ሶስት የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ኣባላት ምእመናን መገደላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳ ተችሏል።

እጅግ አሳሳቢ ሆኖ ያለው በመክሲኰ የሚታየውና ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ በመሄድ ላይ ያለው ጸረ የካህናትና ጸረ የመገናኛ ብዙኃን ሙያተኞና ጋዜጠኞች ላይ ያነጣተረ እመጽ ሲሆን። እ.ኤ.አ. በ 2016 ዓ.ም. ዘጠኝ ጋዜጠኞች መግደላቸውና በ 2017 ዓ.ም. ውስጥ ደግሞ ሰባት ጋዜጠኞች ለሞት ተዳርገዋል። መክሲኰ በዓለም የጋዜጠኞች ሕይወት ለአደጋ ከተጋለጡባቸው አገሮች ውስጥ በሦስተኛ ደረጃ ተመድባለች። እ.ኤ.አ. ከ2000 እስከ 2017 ዓ.ም. ውስጥ በጠቅላላ 100 ጋዜጠኞች መገደላቸው አንቀጽ 19ኝ የተሰየመው የብሪጣንያው ድርጅት የሰጠው ዘገባ ዋቢ ያደረጉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጣኛ ጂሶቲ አያይዘው፥ ድንበር አልቦ ዘጋቢያን ማኅበር ያሰራጭው ጥናታዊ ሰነድ በማስደገፍ መክሲኮ በዓለም የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት አክባሪ አገሮች ዝርዝር ውስጥ በ147ኛ ደረጃ እንደተቀመጠች ጠቅሰው በአሁኑ ሰዓት በ21 አገሮች ውስጥ የጋዜጠኞች ሕይወት ለከፋ አደጋ ተጋልጦ እንደሚገኝ ይናገራሉ። 

በአንደንዛዥ እጸዋት አዘዋዋሪ የወንጀል ቡድኖች መካከል ባለው ግጭትና ከዚህ ጋር ተያይዞም የሚከሰተው አመጽና ውጥረት በተለይ ደግሞ የወንጀል ቡድኖች ተግባርና ማንነት የአደንዛዥ እጽዋት ዝውውርና እንቅስቃሴውም ከየትና ወዴት ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት በጥልቅ በመከታተል የሚገኙትና የወንጀል ቡድኖች ጋር ግኑኝነት ባላቸው የፖለቲካና የኤኮኖሚው ዓለም አካላት ማንነት ገሃድ የሚያደርጉ ዘጋቢያን ጋዜጠኞች ሕይወት ለከፋ አደጋ የተጋለጠ መሆኑ የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑት ማኅበራት ካለ መታከት ቢያሳውቁም አሁንም ቢሆን ጋዜጠኞች ለክፈፋ አደጋ ተጋልጠው እንድሚገኙና በአደንዛዥ እጸዋት ሱሰኝነት ለተጠቁት ዜጎች ከወደቁበት አስከፊው አደጋ ለማዳን ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው ሰብአዊ መንፈሳዊና ስነ አእምሮአዊ አገልግሎ ምክንያት ብሎል የአደንዛዥ እጸዋት ዝውውር በመቃወም በምታረማምደው እንቅስቃሴ ምክንያት አባላቷ ካህናት ገዳማውያን ዓለማውያን ምእመናን ጭምር ለከፋ አደጋ ተጋልጠው እንደሚገኙም ጂሶቲ ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.