Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ፍትሕና ሰላም

ፓትሪያርክ ሳኮ፥ የተፈናቀለው ማኅበረ ክርስትያን ወደ ክልሉ ይመለስ ዘንድ የዓለም ማኅበረሰብ ድጋፉን ያቀርብ ዘንድ ጥሪ አቀረቡ

ፓትሪያርክ ሳኮ፥ የተፈናቀለው ማኅበረ ክርስትያን ወደ ክልሉ ይመለስ ዘንድ የዓለም ማኅበረሰብ ድጋፉን ያቀርብ ዘንድ ጥሪ አቀረቡ - RV

04/08/2017 15:52

ባለፉት አስራ አምስት አመታት ውስጥ በእስላማዊው አክራሪ ኃይሎች ከዛም ገዛ እራሱን እስላማዊ አገር ብሎ በሰየመው አሸባሪው ኃይል በሚሰነዝረው ጭካኔ የተሞላው እጅግ አሰቃቂ ጸረ ክርስቲያን ጥቃት ሳቢያ በኢራቅ ሰሚናዊ ክልል ይኖር የነበረው ማኅበረ ክርስቲያን ለመፈናል ለስደት መዳረጉ የሚታወስ ነው። በጎሳ በዘር የሚታየው መከፋፈል በኢራቅ ያለው ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ ብሎም ፖለቲካዊ ኪሳራ ሰላማዊ ማሕበራዊ ኖሮ እጅግ እየተናጋ መሆኑ ይነገራል።

እ.ኤ.አ. በ1990 ዎች ዓመታት የአገሪቱ ማኅበረ ክርስቲያን ከአንድ ሚሊዮን በላይ እንደነበርና ከ 2006 ዓ.ም. ወዲህ ወደ ሦስት መቶ ሺሕ ዝቅ ብሎ መገኘቱና ባጠቃላይ በመካከለኛው ምስራቅ የማኅበረክርስቲያን ሁኔታ ለዘርፈ ብዙ አደጋ ተጋልጦ እንድሚገኝም  በር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 11ኛ እ.ኤ.አ. በ 1926 ዓ.ም. የተመሠረተው የመካከለኛ ምስራቅ ድኾች ተንከባካቢ ማኅበር የሰጠው መረጃ ያሳያል።

በጠቅላላ በቆጵሮስ ግብጽ ኢራቅ እስራኤል ዮርዳኖስ ሊባኖስ በዮርዳኖስ ምዕራባዊ ዳርቻ በጋዛ በሶሪያ እንዲሁም በቱርክ የማኅበረ ክርስቲያን ብዛት 14 ሚሊዮን ከግማሽ እንደነበርና እ.ኤ.አ. በ 2017 ዓም. ያለው ብዛት ከ 2000 ዓ.ም. ጋር ከነበረው ሲነጻጸር በ 200 አኃድ ዝቅ እንዳለም የቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ዓመታዊ የዝርዝር ሰነድ አቅራቢ ቢሮ ሲያመለክት። በተያያዘ መልኩም የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት  ሁነቶችን በአኃዝ የተደገፈ መረጃ አቅራቢ ቢሮ በዓለም የማኅበረ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ  ዙሪያ ባጠናቀሩት ጥናታዊ ሰነድ የተረጋገጠ ጥናት መሆኑም የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሪና ታማሮ ባጠናቀሩት ዘገባ ይጠቁማሉ።

እ.ኤ.አ. ከ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በተለ ደግሞ ከ 2010 እስከ 2014 ዓ.ም. በኢራቅ ከፍተኛ የማኅበረ ክርስቲያን ጸዓት የተከሰተ ሲሆን ሆን ተብሎ ቀጣይነት ባለው በጸረ ማኅበረ ክርስቲያን ጥቃት አማካኝነት ብዙ ማኅበረ ክርስቲያን ክልሉን ለቆ ለመፈናቀልና ለስደት ሲዳረግ። ብዙዎችም ሕይወታቸው እንዳጡ የመካከለኛ ምስራቅ ድኾች ተንከባካቢ ማኅበር ባወጣው ሰነድ ገልጦ፡ በሶሪያ የማኅበረ ክርስቲያ ብዛት ከ 2.2 ሚሊዮን እ.ኤ.አ. በ2017 ዓ.ም. ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ 1.1. ሚሊዮን መውረዱንም ይጠቁማል።

ግብጽ በመካከለኛ ምስራቅ ክልል አግሮች ከፍተኛ የማኅበረ ክርስቲያን ብዛት ከሚገኙባቸው አገሮች ውስጥ ቀዳሚውን ይዛ እንደትገኝና የግብጽ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ምእመን ብዛት ከግብጽ ሕዝብ ብዛት አንጻር ሲታይ 10% የሚሸፍንና ጠቅላይ ብዛቱ 9.4 ሚሊዮን ሲሆን፡ በአሁኑ ሰዓት በአገሪቱ ባለው ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ውዝግብ ሳቢያ ለተለያየ ችግር እንደተጋለጠና ባለፉት ጥቂት የመጨረሻ ዓመታት ውስጥ ብቻ 76 አቢያተ ክርስቲያን በእሳት መጋየታቸው ሰነዱን የጠቀሱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ታማሮ አያይዘው፥

በእስራኤል ያለው ሁኔታም ስንመለከት በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ማኅበረ ክርስቲያን ብዙዎቹም አረብ እስራኤላውያን የሚገኙባቸው ሆኖ በጠቅላላ 170 ሺሕ ሲሆን ከእስራኤል የሕዝብ ብዛት ሲነጻጸር 2.4% የሚሸፍን መሆኑ ይናገራሉ።

በ 1948 ዓ.ም. እስራኤል እንደ አገር በተወለደችበት ማግስት የክልሉ ክርስቲያን ከጠቅላላው ሕዝብ ብዛት ውስጥ 20% ይሸንፍ እንደነበር ሰነዱ ጠቁሞ፡ ሆኖም በአረብና እስራኤል ጦርነት መቀጣጠል ምክንያት ብዙ ፍልስጥኤማውያን ክርስትያኖች ክልሉን ለቀው ተሰዷል። በዮርዳኖ ምዕራባዊ ዳርቻ ክርስቲያኖች 59 ሺሕ ሲሆኑ፡ በጋዛው ክልል ካለው ሁለት ሚሊዮን ከሚገመተው ሕዝብ ብዛት ውስጥ 1,300 ብቻ ክርስቲያን ነው፡ በኢየሩሳሌም ከሚኖረው ከ 870 ሺሕ ሕዝብ ውስጥ 15,800 ብቻ ክርስቲያን መሆኑ ሰነዱን ዋቢ ያደረጉ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ታማሮ ያመለክታሉ።

በዮርዳኖስ በአሁኑ ወቅት 350 ሺሕ ክርስቲያን እንደሚኖና ከጠቅላላው ሕዝብ ብዛት አንጻር ሲታይ 2.2% የሚሸፍን ሲሆን፡ አብላጫ የአገሪቱ ሕዝብ ሱኒ ሙስሊሞች መሆናቸው ሰነዱ ጠቁሞ፡ በኢራቅ እስላማዊ መንግሥት ብሎ በሰየመው እስላማዊ አሸባሪ ኃይል ጥቃት ሳቢያ ወደ 30 ሺህ የሚገመቱ ክርስቲያን ኢራቃውያን በዮርዳኖስ በጥገኝነት እንዲኖር ማስገደዱ ጠቅሶ በሊቦኖስ እ.ኤከ በ 1932 ዓ.ም. ክርስቲያን የአገሪቱ ዜጋ ከጠቅላላው የአገሪቱ ብዛት ውስጥ 50% ይሸንፍ እንደነበና በአሁኑ ሰዓት ወደ 40% ዝቅ እንዳለምም ሰዱን ዋቢ ያደረጉ ልእክት ጋዜጠኛ ታማሮ ይጠቁማሉ።።

የማኅበረ ክርስቲያን በመካከለኛ ምስራቅ ሁኔታ በተመለከተ የባቢሎን ከለዳዊ ስርዓት ተከታይ ማኅበረ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ልዊስ ራፋኢል ቀዳማዊ ሳኰ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ የመካከለኛው ምስራቅ ማኅበረ ክርስቲያን በገዛ አገሩ የመኖር መብቱ ሊከበርለት ይገባል። ስለዚህ የዓለም አቀፍ ማኅበረስብ ድጋፍ ያስፈልጓል። በአሁኑ ሰዓት በክልሉ ጸረ ክርስቲያን ያነጣጠረ ጥቃትና ግብረ ሽበራ አለ ይኽ ደግሞ ማኅበረ ክርስቲያኑ ለስደት ለመፈናቀል አደጋ እያጋለጠ መሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም። በመካከለኛው ምስራቅ የማኅበረ ክርስቲያን ህላዌ ጥንታዊና ከክልሉ ታሪክ ጋር የተቆራኘ ነው፡ ስለዚህ ሊደገፍና ትብብር የሚያሻው የኅብረተሰብ ክፍል ነው ብሏል።

እርግጥ ነው ይላሉ በአሁኑ ሰዓት በኢራቅ ያለው ሁኔታ መጠነኛ መሻሻል እያሳየ ቢሆንም ቅሉ፡ ፍርሃቱ እንዳለ ነው ፡ ያለው ግጭት አልተቛጨም። የተፈናቀለው ማኅበረ ክርስቲያን ወደ ክልሉ እንዲመለስ መሠረታዊ አስፍላጊ ነግሮች ሊቀርብለት ይገባል። ቤቱንና ንብረቱን አጥቱል። ስለዚህ መኖሪያ ቤቶችን ዳግም መገንባት ያስፈልጋል በክልሉ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በዚሁ መስክ አቢይ አስተዋጽኦ እያበረከተች ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።

04/08/2017 15:52