2017-08-02 15:41:00

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፥ በቨነዝወላ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ ዓመጽ ዴሞክራሲያዊ መትሔ ያሻዋል አሉ


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን እ.ኤ.አ. ሐምሌ 31 ቀን 2017 ዓ.ም. በቨነዝወላ እልባት ያጣው ሕዝባዊ ዓመጽ እንዲገታ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና አገረ ቫቲካን ዲሞክራሲያዊ ሂደት የሚያመነጨው መፍትሔ አስፈላጊ መሆኑ በማሳሰብ ይኽ ደግሞ የሚፈጠረው አለ መግባባት በሰላማዊ መንገድ ሲቀረፍ ሰላም ዘላቂነት እንደሚኖረው የሚያመላክት መንገድ መሆኑ አንሳ ከተሰየመው የዜና አገልግሎት ጋር ባካሄዱት ቃል ምልልስ ገልጠዋ።

አገረ ቫቲካን አለ ምንም ውገና በቨነዘወላ ተከስቶ ያለው ችግር መፍትሄ እንዲያገኝ ከሁሉም ጋር ለመወያየትና ሁሉም ኃላፊነቱን በመቀበል የሰላም መንገድ ሊመርጥ ይገባዋ። ስለዚህ መፍትሔ የመሻቱ ሂደት የሕዝብ ጥቅም መሠረት ያደረገ መሆን አለበት እንዳሉ የጠቆመው አንሳ የዜና አገልግሎት አያይዞ፥

ባለፈው እሁድ የርእሰ ብሔር ኒኮላስ ማዱሮ መንግሥት ውሳኔ መሠረት አንድ አዲስ የሕግ መወሰኛ የበላይ ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድ ባደረገበት እ.ኤ.አ. ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በተከሰተው ግጭት ሳቢያ አስራ ሦስት ሰዎች መገደላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጃመስ ብለአርስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፡ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በሊቀ መንበሩ በኩማ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲየጎ ራፋኤለ ሳንቸስ በኵል ቀደም ብሎ የቨነዘወላ መንግሥት የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት በአዲስ መልኵ ለማቋቋም የወጠነው የምርጫ ውሳኔ ቀድም ብሎም ምርጫው ከተካሄደውም በኋላ ተቀባይነት የሌለው የሕዝብ ፍላጎት የማያንጸባርቅ ምርጫ ነው በማለት ተቃውሞ በማሰማት ማንኛውም ማኅበራዊ ውጥረትና ግጭት የሚፈታው በነውጥ አልቦ ትግል ብቻ ነው፡ ስለዚህ ኃይል የመጠቀሙ ምርጫ እንዲገታ በማለት የሕዝብና የአገር ጥቅም ላይ እንዲተኮር አሳስበው እንደነበርም ፊደስ የዜና አገልግሎት ካስራጨ የዜና ምንጭ ለመረዳት ተችሏል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታችን ሆይ በዚህ ቨነዝወላ በስቃይ ላይ ባለችበት ወቅት በአንት እንታመናለን በሚል ጸሎት ላይ ያማከለ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በሁሉም ሰበካዎችና ቁምስናዎች በመንፈሳዊ ማኅበራት ቤት ጭምር እንዲካሄድ የጠሩት የጸሎት መርሐ ግብር ባለፈው እሁድ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. መከናወኑ ፊደስ የዜና አገልግሎት ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.