Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ፍትሕና ሰላም

ዝክረ መቶኛው ዓመት የር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 15 ትርጉም አልቦ እልቂት የተሰየመው የሰላም መልእክት

ዝክረ መቶኛው ዓመት የር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 15 ትርጉም አልቦ እልቂት የተሰየመው የሰላም መልእክት - RV

02/08/2017 15:36

የኦስትሪያ ሃንጋርይ ግዛት በሰርቢያ ግዛት ላይ ያወጀውና በሳራየቮ ለፍራንቸስኮ ፈርዲናንዶ ዘኣውስበርግ ቅትለት ምክንያት የሆነውን ያንን እ.ኤ.አ. በ 1914 ዓ.ም. እስከ 1918 ዓ.ም. በኤውሮጳ እንዲቀጣጠል ላደረገው አንደኛው የዓለም ጦርነት ትርጉም አልቦ እልቂት በሚል ርእስ ሥር ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 15ኛ ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲቆም እ.ኤ.አ. ነሐሴ 1 ቀን 1917 ዓ.ም. በመካሄድ ላይ በነበረው ጦርነት ተወናያን ለነበሩት የአገሮች መንግሥታት ያስተላለፉት መልእክት ዝክረ መቶኛው ዓመት ምክንያት ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 31 ቀን 2017 ዓ.ም.  ባወጣው ኅትመቱ ሰፊ ሃተታ ሰጥቶበታል።

ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 15ኛ  ያንን እ.ኤ.አ. ከ 1914 ዓ.ም. በፊት የነበረው ብሎም ጦርነቱ ካበቃለት ከ 1918 ዓ.ም. በኋላ የተረጋገጠው የኤውሮጳ መልክአ ምድር በማነጻጸር የሚዳስስና የሩሲያው ንጉሳዊ ሥርዓት እንዲሁም የኦቶማን መንግሥት መገርሰስ የጀርመንና ኦስትሪያ መንግሥት የተገረሰሰበት በጠቅላላ የነበረው ታሪካዊ ክንዋኔዎችን የሚተነትን አራት ዓመት ጭካኔ የተሞላበት ዕልቂት ወታደሮችና ንፁሓን ዜጎች በጠቅላላ 17 ሚሊዮን ሰዎች ለሞት የዳረገው አሰቃቂው በ 1914 ዓ.ም. የተቀጣጠለውን ጦርነት ለማቆም የሚያስችል ወደ ሰላም የሚመራውን መንገድ በማመላከት የጦርነት አስከፊነት በጥልቀት ያብራሩበት መልእክት እንደነበር ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ ባወጣው ኅትመቱ ይጠቁማል።

የስለጠነው ዓለም የዕልቂት ሰፈር ለመሆን ገዛ እራሱን እንዴት ዝቅ ያደርጋል? ያች ክብርትና በመፍካት ላይ ያለቸው ኤውሮጳ እንዴት ሆና ነው እራስ በመሳት ችግር ታጥራ ከራሰ ቅትለት ጋር ለመገናኘት የምትጓጓው የሚል ጥያቄ በመልእክቱ ያኖሩት ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 15ኛ እንዲህ ባለ ፖለቲካዊ ማሕበራዊ ሰብአዊ ሃይማኖታዊ ስጋት ባለበት ሁኔታ የሰላምን ጥሪ እናስተጋባለን ብለው እነዚያ የአገሮች ዕጣ ፋንታ በእጃቸው ለሆነው መንግሥታት የጋለ የሰላም ጥሪ አናቀርባለን እንዳሉ ያስታወሰው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ አክሎ፥ ጃኮሞ ደላ ከዛ በርእሰ ሊቀነ ጳጳሳዊ መጸውዕ ስማቸው በነዲክቶስ 15ኛ ዓመጽና ጦርነት እንዲቆም ጥሪ በማቅረብ ብቻ ሳይገቱ በግብረአዊነትና በጽናት መንግሥታት ሊያስማማ የሚያስችለውና ወደ ሰላም የሚያደርሱ ናቸው የሚሉዋቸውን ሃሳቦች፥ ትጥቅ መፍታት የጦር መሣሪያ ቅነሣ በጦርነት የተያዙት ክልሎች ለተገቢ ሕጋዊ ባለቤት ለሆነው አገር ለማስረከብ የሚል መሠረት ያደረገ ግልጽና ነጻ የሆነው ገላጋይ አካል አስፈላጊነት እንዳለው ማብራራታቸው ያመለክታል።

ከዚያ ከሁሉም ምእመናን ከእግዚአብሔር ልጆችና በሁሉም ሰዎች ዘንድ ያለው የሰላም አስተንፍሶ አማካኝነት ተነቃቅተው የግል ጥቅም መሻት ከሚለው ምርጫ ተላቆ የሕዝብና የአገር ጥቅም በማስቀደም፡ የአርመናውያን የባልካን አገሮች የፖላንድ ግዛት ያጸኑ አገሮች ጉዳይ የሚመለከቱትን ጥያቄዎች በቂ መልስ እንዲሰጥበት በማለት ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 15ኛ ያቀረቡት ጥሪ ኤውሮጳ መልስ ከመስጠት ተቆጥባ ርእሰ ውድመትን መርጣ በአንደኛው የዓለም ጦርነት እጅግ መጎዳትዋ አልበቃ ብሎ ልክ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ በትክክል ከ20 ዓመት በኋላ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ መነከርዋ እጅግ የሚያሳዝን መሆኑ ያብራራው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በጀርመን ሃምበርግ ከተማ ተካሂዶ ወደ ነበረው በኢንዳስትሪ የበለጸጉ ሃያ አገሮች ጉባኤ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. አስተላልፈዉት በነበረው መልእክት አገሮች ከራስ ወዳድነት ወደ ውጥረትና ግጭት ከሚገፋፋው ተግባር ሁሉ ነጻ እንዲሆኑ በማለት ያሰመሩበት ሃሳብ የር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 15ኛ መልእክት የሚያንጸባርቅ የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት የሚያጎላ መሆኑ ያረጋግጣል።

በነዲክቶስ 15ኛ የሰው ልጅ ታሪክ ዛሬም ቢሆን ወደ ጦርነት የሚገፋፉው የተለያየ እምቅ ኃይል መኖሩ ያመለክታል። ስለዚህ ሁሉም የጦርነት ተወናያን አገሮች ያንን ትርጉም አልቦ የሆነው ዕልቂት እንዲገታ ትጥቅ በመፍታት ውሳኔ እንዲተጉ አደራ ብለው እንደነበር የጠቆመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ፥ አክሎ ይኽ የአደራው ጥሪ ወቅታዊነት ያለው ርእሰ ጉዳይ ነው ሲል የር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 15ኛ የሰላም መልእክት ዙሪያ ያሰጠው ሰፊ ሐተታ ይቋጫል።

02/08/2017 15:36