Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ባደረጉት አስተምህሮ "ምስጢረ ጥምቀት የተስፋ በር ነው " ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በዛሬው እለት በጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ የጠቅላላ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት። - ANSA

02/08/2017 15:39

ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ ነጋዲያ እንዲሁም  ከተለያዩ ሀገራት ለተውጣጡ የሀገር ጎብኝዎች በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስትምህሮ ወይም ትምህርተ ክርስቶስ ጠቅለል ባለ መልኩ እንደ ሚሰጥ ይታወቃል። የዚህ አስተምህሮ መርሃ-ግብር አንዱ አካል በሆነ በዛሬው እለት ማለትም በሐምሌ 26/2009 ዓ.ም. በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ቅዱስነታቸው ያደረጉት አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው ከዚህ ቀደም “የክርስቲያን ተስፋ” በሚል ጭብጥ ከዚህ ቀደም ስያደርጉት የነበረው ተከታታይ አስተምህሮ ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረም ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፤ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁላችሁ ክርስቶስን ለብሳችሁታልና። በአይሁድና በግሪክ፣ በባሪያና በነጻ ሰው፣ በወንድና በሴት መካከል ልዩነት የለም፤ ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ናችሁ” በሚለው ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ገላቲያ በጻፈው መልእክቱ በምዕራ 3: 26-28 ላይ መሰረቱን ባደረገው  የዛሬው እለት አስተምህሮዋቸው ምስጢረ ጥምቀት የተስፋ በር ነው ማለታቸው ተገለጸ።

የዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን በማስከተል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በሐምሌ 26/2009 ዓ.ም. በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ ነጋዲያን እንዲሁም የሀገር ጎብኝዎች ያደረጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

 

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ።

አብያተ ክርስቲያንት ፊታቸውን ወደ ምስርቅ በማድረግ ወደ እዚሁ ቅዱስ ቤተ መቅደስ  ውስጥ በሚገባበት ወቅት ወደ ምስርቅ መመልከት እንችል ዘንድ  ዋና በራቸው ወደ ምዕራብ እንዲከፈት ተደርጎ የሚሰራበት ደንብ  በአንድ ወቅት ነበር። ይህም አሠራር በወቅቱ ለነበሩ ሰዎች በጣም አስፈላጊ ነገረ ስራዓት የነበረ ሲሆን ይህ አሥራር ግን ቀስ በቀስ በታሪክ ሂደት ልምዱን እያጣ መቱዋል። እኛ በዚህ ዘመናዊ በሚባል ዘመን የምንኖር ሰዎች፣ በትዕይንተ-አለም ወይም በእንግሊዘኛው cosmos ያሉትን ምልክቶች የመረዳት ባሕላችን በጣም እየቀነሰ በመምጣቱ የተነሳ እነዚን ዓይነት ነገሮች መረዳት እያዳገተን መጥቱዋል። ፀሐይ የምትጠልቀው እና ብርሃን የሚጨልምበት ዋነኛ አቅጣች የምዕራብ አቅጣጫ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ጨለማ ድል የሚሆንበትና ብርሃን የሚያሸንፍበት የመጀመሪያ ጎህ የሚቅድበት የዓለም አድማስ የሚታይበት ክርስቶስ የሚታወስበት በምስርቅ አቅጣጫ ነው።

በጥንት ጊዜ የነበረው የምስጢረ ጥምቀት አስጣጥ ስነ-ስርዓት እንደ ሚያመለክተው ለመጠመቅ በዝግጅት ላይ ያለ አንድ ሰው ጸሎተ ሐይማኖት የሚደግመው ፊቱን ወደ ምዕራብ በማዞር ነበር። በዚህም የምስጢረ ጥምቀት ስነ-ስርዓት ወቅት ካህኑ አዲስ ተጠማቂውን ሰው “የስይጣንን አስተምህሮ እና ተግባር ትክዳለህን?” ብሎ ወደ ክርስትና እምነት ሊቀላቀል የሚዘጋጀውን ሰው በሚጠይቅበት ወቅት እርሱ/እርሷ “አዎን እክዳለሁ!” ብለው የሚመልሱት ወደ ምዕራብ በመመልከት ነበር። ከዚያም በመቀጠል ይህ ለመጥመቅ በዝግጅት ላይ ያለ ሰው “በእግዚኣብሔር አብ፣ በልጁና በመንፈስ ቅዱስ ታምናላህን?” ተብሎ በካህኑ ሲጠየቅ “አዎን አምናለሁ!” ብሎ የሚመልሰው ፀሐይ ወደ ምትፈነጥቅበት ወደ ምስርቅ አቅጣጫ እንዲመለከት በማድረግ ነው።

አሁን ባለንበት በዚህ ዘመናዊ በሆነ ዘመን ለትይነተ-ዓለም የምንሰጠው ትኩረት እየቀነሰ በመምጣቱ የተነሳ ይህን ትጉም ያለውን ስነ-ስርዓት በከፊሉም ቢሆን እየረሳን እንገኛለን። ታዲያ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው? ክርስቲያን ማለት ወደ ብርሃን መመልከት፣ ዓለም በድቅድቅ ጨለማ በሚዋጥበት ወቅትም እንኳን ወደ ብርሃን በመመለከት እምነታችንን በቀጣይነት መገልጽ ማለት ነው።

እኛ ክርስቲያኖች በዓለም ውስጥ የምንኖር በመሆናችን የተነሳ ውስጣዊና አከባቢያዊ /ውጫዊ ከሆነ ጨለማ ነጻ የሆንን ሰዎች አይደለንም። ነገር ግን በጥምቀታች ወቅት በተቀበልነው የክርስቶስ ጸጋ ምክንያት ክርስቲያኖች በጨለማ ሳይሆን ግልጽ በሆነ በብርሃን ነው የምናንምነው፣ ክርስቲያኖች ጎህ እንደ ሚቀድ ተስፋ ሰለሚያደርጉ ጨለማ አያሸንፋቸውም፣ ከሞት ለመነሳት ጥረት ሰለሚያደርጉ ሞት ድል አያደርጋቸውም፣ ሁል ጊዜም ቢሆን  መልካም የሆኑ አጋጣሚዎች እንደሚኖሩ  ስለሚያምኑ በክፉ ነገሮች አይሸነፉም።

እኛ ክርስቲያኖች እግዚኣብሔር አባት እንደ ሆነ እናምናለን፣ ይህም ብርሃናች ነው። ክርስቶስ በመካከላችን በመሆን በእኛ ሕይወት ውስጥ ይራመዳል፣ በተለይም ደግሞ በድኾችና ለጥቃት ከጠጋለጡ ሰዎች ጋር አብሮ እንደ ሚሆንም እናምናለን፣ ይህም ብርሃናች ነው። እኛ መንፈስ ቅዱስ በሰው ዘር ውስጥ እና በዓለም ላይ በትጋት እየሠራ ታላላቅ የሚባሉ መከራዎችን እንድንወጣ እንደ ሚያደርገን እናምናለን፣ ዘወትር ጥዋት ጥዋት ተስፋችን እንዲለመልም የሚያደርገውም ይህ እምነታችን ነው።

አንድ ክርስቲያን በተለይም ደግሞ በሐዘን አረቋ ውስጥ ለሚገኙ፣ ተስፋ ለቆረጡ፣ በጨለማ ውስጥ ለሚገኙና የተጠሉ ሰዎች ወደ ሚገኙበት ዓለም እውነተኛ ለውጥ በማምጣት ክርስቶስን ወደ ዓለም መውሰድ  መቻሉ ትልቅ ጸጋ ነው። አንድ ክርስቲያን ይህ የክርስቶስ ጸጋ እናድለው እና እንደ ሌለው የሚረዳው በሕይወቱ ውስጥ በሚታዩት ጥቃቅን የሆኑ የብርሃን ምልክቶች ለምሳሌም በዓይኑ ውስጥ ከሚታየው ብርሃን፣ ውስብስብ በሆኑ ወቅቶች ሁሉ ውስጥ በሚያሳየው መረጋጋት፣ ምንም እንኳን ተስፋ የሚያስቆርጥ ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ነገር ግን ሕይወትን በአዲስ መልክ በመልካም ሁኔታ ለመጀመር ከሚያሳየው ፍላጎት ለመረዳት እንችላለልን። ለጥምቀታችን ታማኝ በምንሆንበት ወቅት የተስፋ ምንጭ የሆነውን የእግዚኣብሔርን ብርሃን በትጋት በመጠበቅ የሚቀጥለው ትውልድ ምክንያታዊ የሆነ ሕይወት እንዲኖር ልናደርግ እንችላለን።

 

02/08/2017 15:39