Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ፍትሕና ሰላም

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፥ አሰቃቂው የሰው ልጅ ንግድ ልሙድ ሊሆን የማይገባው አቢይ ወንጀል ነው

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፥ አሰቃቂው የሰው ልጅ ንግድ ልሙድ ሊሆን የማይገባው አቢይ ወንጀል ነው - AFP

31/07/2017 15:55

እ.ኤ.አ. ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የተባብሩት መንግሥታት ድርጅት ውሳኔ መሠረት ዓለም አቀፍ ጸረ ሕገ ወጥ የሰው ዘር ዝውውር ታስቦ በዋለበት ዕለት በሁሉም አገሮች በምትገኘው ካቲሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በመፈሳዊና ባህላዊ መርሓ ግብሮች ሥር ተመርቶ ታስቦ የዋለ ሲሆን፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እኩለ ቀን በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ኣሳርገው እንዳበቁም ዕለቱ ዓለም አቀፍ ጸረ ሕገ ወጥ የሰው ዘር ዝውውር የሚዘከርበት መሆኑ ጠቅሰው፥ ሰዎችን በሕገ ወጥ ተግባር ከቦታ ቦታን ዝውውርና የሰው ልጅ ንግድ ልሙድ ወይንም ቅቡል ሊሆን የማይገባው አቢይ ጸረ ሰብአዊ ወንጀል ነው በማለት፥ ይኸ በአሁኑ ሰዓት የሚታየው የዘመኑ ባርነት፥ አሰቃቂ ጨካኝ መንፈስ የሚታይበት አቢይ ወንጀል ነው። ጥንት የነበረው የባርነት ሥርዓት አዘምኖ በማቅረብ ይኸንን በብዙ ሺሕ የሚገመቱት ንጹሓን ዜጎች ለከፋ አደጋ የሚያጋልጠው አሰቃቂው ጸረ ሰብአዊ ድርጊት ቅቡል ወይንም ልሙድ አድርጎ መመልከቱ ለገዛ እራሱ በተባባሪነት የሚያስጠቅ ነው። በአሁኑ ሰዓት በሕገ ወጥ ተግባር ሰዎችን ከቦታ ቦታ የማዘዋወሩ ሂደት፥ ለበዛዥ ሥራ ለግብረ ሥጋ መስኅብ ብሎም ለሰውነት አባላካል ንግድ አቅርቦት ማርኪያ ለሆነው ለጸረ አሰቃቂ ኢሰብአዊ አደጋ የሚያጋልጥ ነው፡ በማለት አያይዘው በማርያም አማላጅነት እነዚያ ይኸንን ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውወር የሚያረማምዱ ሰዎች ልባቸው ይለወጥ ዘንድ መማጠናቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸቺሊያ ሰፒያ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

በዚህ ዘመናዊ ባርነት ተብሎ በሚገለጠው ተግባር በብዛት ሴቶችና ህፃናት የሚገኙበት ከ 21 እስከ 35 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች የሚያጠቃ መሆኑ የሕጻናት አድን አለም ዓቀፍ ድርጅት ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ሲቻል የዚህ ጸያፍ ተግባር ተጠቂ ከሆኑት ውስጥ አንድ አራተኛውም ለአቅመ አዳም ያልደረሰ ዜጋ መሆኑ ያመለክታል።

ለአቅመ አዳም ያልደረሱት ዜጎች በሥራ ዓለም ማሰማራት ለጋብቻ በመዳረግ፡ ለማሕፀን ኪራይ ለመሳሰሉት አደጋዎች የታጋለጡም ሲሆን። ይኽ ሁሉ ለወቅታዊው ዓለም እና ለሰብአዊ ህሊና አቢይ ተግዳሮት እንደሆነም ቀኑን ምክንያት በማድረግ የረፓብሊካዊት ኢጣሊያ ርዕሰ ብሔር ሰርጆ ማታረላ ባስተላለፉት ብሔራዊ መልክት እንዳሰመሩበት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሰፒያ ያመለክታሉ።

በዚህ አሰቃቂው ጸረ ሰብአዊ ተግባር ፊት የሚታየው ቸልተኝነትና ግድ የለሸትነት ተግባር ጨርሶ እንዲወገድና የዓለም ሕዝብም ሆነ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋሞች ተገቢ ምላሽ እንዲሰጡበት ሁሉም ዜጋ በየፊናው እንዲቃወመውና ይኽ አሰቃቂው ተግባር የሚያስከትለው ጉዳት ዙሪያ ያለው ግንዛቤው ከፍ እንዲያደርግ ሕሊናዊ ሕንጸት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር የሚቃወምና  በዚህ ጸረ ሰብአዊ ተግባር ለአደጋ የተጋለጡት ሴቶችና ለአቅመ አዳም ያልደረሱት ዜጎች ለማዳን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጠው ክሰባ በላይ የሚገመቱት የተለያዩ የደናግል ማኅበራት የሚያቅፈው ከአንድ መቶ በላይ የሚገመት መጠለያ ማእከል ላለው ማኅበር አማካሪ የኮንሶላታ ደናግሎች ማኅበር አባል እናቴ ኤውጀኒያ ቦነቲ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የገለጡ ሲሆን፥ ይኽ ጸረ ሰብአዊ ተግባር ለወንጀል ቡድኖች እስከ 40 ሚሊያርድ ዶላር የሚገመት ገቢ የሚያገኙበት እንደሆነም ጠቅሰው በዚህ ጸያፍ ተግባር እጅግ የተጠቁት የናይጀሪያ ዜጎች መሆናቸውንም ያመለክታሉ።

31/07/2017 15:55