2017-07-29 10:34:00

የእድሜ ባለጸጎች ለአንድ ማኅበረሰብ ውድ የሆኑ ስጦታዎች ናቸው!


“የእድሜ ባለጸጎች በቤተሰብ ህይወት ውስጥ አስፈላጊ የሆነ ሚና በመጫወት በእያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ የአንድነትን እና የእምነትን መንፈስ ይስርጽ ዘንድ እነዚህን እሴቶች በውርስነ ለማኅበረሰቡ ያቀርባሉ”፣ ይህ ቀደም ሲል የተጠቀሰው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ @ponifex በሚለው በዓለም ዙሪያ ተጽኖ ፈጣሪ ከተባሉ ሰዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰውን የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚደንት  ባራክ ኦባማን በሁለተኛ ደረጃ በማስከተል በዓለም ዙሪያ ከ14 ሚልዮን በላይ ተከታዮች ባሉት የቲውተር ገጻቸው ላይ በሐምሌ 19/2009 ዓ.ም. በዘጠኝ ቋንቋዎች ይፋ ካደረጉት መልእክ የተወሰደ ነው።

የዚህን ዘገባ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ  የእድሜ ባለጸጋዎች ለማኅበራዊ ሕይወት አንድነት እና እምነትን በውርስ የማስተላለፍ ሚናቸው ከፍተኛ እንደ ሆነ ጠቅሰው በተለይም ደግሞ አሁን ባለንበት የራስ ወዳድነት መንፈስ እየተንሰራፋ ባለበት ዓለማችን የእድሜ ባለጸጋዎች እያበረከቱት የሚገኙት አስተዋጾ ከፍተኝ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።፣

ቅዱስነታቸው ቀደም ሲል የተጠቀሰውን በቲውተር ገጻቸው ላይ ካስተላለፉት ምልእክት ባሻገር በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በሐምሌ 19/2009 ዓ.ም. በተከበረው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማሪያም ወላጆች የሆኑት የቅዱሳን ኢየቄም እና ሃና አመታዊ በዓል ላይ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ቤተክርስቲያን የእድሜ ባለጸጋ የሆኑ ሰዎች ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጾ እውቅናን በመስጠት በስስት እንደ ምትመለከታቸው ገልጸው አረጋዊያን ከፍተኛ የሆነ የሕይወት ተመክሮ ሰላላቸው፣ ውድ የሆኑ ስጦታዎች በመሆናቸውም የተነሳ፣ የአረጋዊያን በማኅበረሰቡ ውስጥ መኖር ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው ገልጸው መጭውን ጊዜ በኃላፊነት እና በተስፋ እንድንጠባበቅ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጉልናል ብለዋል።

አረጋዊያን በእድሜያች ያካበቱት ብስለት እና ጥበብ አሁን የሚገኘውን የወጣቱን ትውልድ ለማነጽ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል ያሉት ቅዱስነታቸው በሕይወታችን ዘመን በጣም ከፍተኛ የሚባሉ ፈተናዎች በሚያጋጥመን ወቅቶች ሁሉ ተስፋ ሳንቆርጥ በእግዚኣብሔር ተማምነን እንዴት መኖር እንደ ሚገባን ያስተምሩናል ይህም በትዕግስት መልካም ፍሬ ማፍራት እንደ ሚቻልም ያስተምሩናል በማለት ጨምረው ገለጸዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.