2017-07-29 08:59:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የአምስት ዓመት ር.ሊ.ጵጵስና መታሰቢያ መዳይ


የቦነስ አይረስ ሊቀ ጳጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ቦርጎሊዮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተሾሙበት ዝክረ ዓምስተኛ ዓመት የርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸ መታሰቢያ የተሠራው ሜዳይ  እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን የሐዋርያዊ መንበር ርስት መስተዳድር ቢሮ እንዲሁም በቫቲኣካን ማተሚያ ቤት ለሽያጭ እንደሚቀርብ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

በሜዳዩ ገጾችም የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አርማ ወይንም ምስል የተኖረበትና በስሩም በላቲን ቋንቋ FRANCISCUS P.P. ANNO V MMXVI - ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አምስተኛ ዓመት 2017 ዓ.ም. የሚል ጽሑፍ የታተመበት ሆኖ አገረ ቫቲካን የሚል በትንሹ ጽሑፍ ያረፈበትና የሜዳዩ ቁጥር መለያ ያለበት በተጨማሪም ኪነ ጥበበኛው የሥነ ቅብ ሥነ ሐወልት ሥራ ምስሉን የቀረጸው ፊርማ ያለበት ሲሆን መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

በሁለተኛው ገጹ ደግሞ አንዲት በተለያየ ችግር ምክንያ ተገፋፍተው የገዛ አገራቸውን ጥለው ለስደት ያቀኑትን ስደተኞች ያሳፈረች ጀልባና ስደተኞችን ለእርዳታ ይዘረጉትን እጆች ለመርዳት የፈጠነ የአንድ እጅ ምስል የተቀረጸበትና ከማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 25 ቍ. 35 hospes eram et collegistis me - እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና የሚል የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል የተጻፈበት፡ አንድ ክርስቶስን የሚመስል በብዙ ሕዝብ መካከል ቁጭ ብሎ የተጎሳቆለ የሚያስተናግደው ቀርቦ የሚቀበለው የሚጠባበቅ የአንድ ሰው ምስል የታተመበትና ከዚህ ጋር ተያይዞም በማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 25 ቍ. 40 ላይ ያለው “ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለኣአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው የሚል ወንጌላዊ ቃል የታተመበት እንደሆነም የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አመለከተ።

የዚህ መስል ሠሪው የኪነ ጥበብ ባለ ሞያ የሐውልት ቀራጭና የሥነ ቅብና ሥነ ስእል ሊቅ ማሪያአንጀላ ክሪሾቲ መሆናቸው ያስታወቀው ቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታውቋል አክሎ፥ የሜዳዩ ቅጅ ወይንም በተምሳይ ሰርቶ ለንግድ ለማቅረብ እንዳይቻልም የራሱ መለያ ያለውና እውነተኛ መሆኑ የሚያረጋግጥ የመታወቂያ ወረቀት አብሮት ለገዢው እንደሚሰጥ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.