2017-07-29 16:24:00

እስራኤል፥ ለሰላምና ይቅር ለመባባል ዓለም አቀፍ የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ጉባኤ


በቅድስት መሬት የሚገኙት በአሃዱ እግዚአብሔር አማኝ ሃይማኖቶችን የሚወክሉ የበላይ መንፈሳውያን መሪዎች በእየሩሳሌም “ከኃይለኛው ማዕበል ማዶ መመልከት” በሚል መርሆ ሥር እ.ኤ.አ. ከሐሜ 12 ቀን እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም. በቅድስት እመቤት ዘእየሩሳሌም ማእከል መካሄዱ በእየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ለትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ይፋዊ ድረ ገጽ ያሰራጨው ዜና የጠቀሰው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ይኽ ለሰላምና ይቅር ለመባባል የሚያነቃቃው የውስጠ ሃይማኖቶች የጋራው ጉባኤ ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ አበይት የሃይማኖት መሪዎችና የማኒላ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካዲናል ልዊስ አንቶኒዮ ታግለ፡ በያውንዴ መንበረ ጥበብ መምህር ዶክተር አዳሙ ንዳም ንጆያ በእንግልጣር የአይሁድ ሃይማኖት ልሂቅ አቢይ መምህር ጆናታን ሄንርይ ሳክስ በእየሩሳሌምና በዮርዳኖ የላቲን ሥርዓት ለትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምክትል ፓትሪያክ ብፁዕ አቡነ ዊሊያም ሾማሊ፡ የፍልስጥኤም ራስ ገዝ መስተዳድር የሃይማኖቶች ጉዳይ ሚኒ. ማህሙድ አል ሓባሽ ሌሎች መልካም ፈቃድ ያላቸው አካላትና ምሁራን ያካተተ ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ አበይት አካላት ምሕረትና ይቅር መባባል ዙሪያ የሰጡት አስተምህሮ ጭምር ያስተናገደ እንደነበርም የገለጠው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አክሎ፥

በምሕረትና በፍትሕ መካከል ተቃርኖ የለም

በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ንግግር ያስደመጡት ብፁዕ ካርዲናል ታግለ፥ “በዚህ በቀጣይነት መራራና የከረረ ጥላቻ በሚታይበት ዓለም ሌላውን ማቁሰል ልሙድና እንደ አንድ የጊዜ ማሳለፍያ ተግባር እየሆነ መጥቷል” በማለት እነዚህ ሦስቱ በአንድ እግዚአብሔር አማኝ ሃይማኖቶች በጋራ አለ ዓመጽና አለ ጥላቻ በጋራ የሚኖር ኅብረተሰብ ለመገንባት የሚያስችለውን መንገድ ለይቶ ለመጠቆም በመገናኘት ይኸንን ሰላማዊ የጋራው ኑሮ አረጋግጦ ለመጪው ትውልድ በማስረከብ ሰላም በሰላም ባህል መዋስ እንደሚያስፈልግ በጥልቀት ማብራራታቸው ጠቁሞ፡ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በሚገኘው የሲኮንሲን መንበረ ጥበብ የሥነ ምሕረት ሥነ ምርምር መምህር ኤንራይት በበኩላቸውም በምሕረትና በፍትሕ መካከል ተቃርኖ የሚኖረው ጥላቻ ሲኖር ነው፡ ስለዚህ በጥላቻ ላይ አለ መቅረት በምሕረትና በፍትሕ መካከል ያለው ውስጠ ግንኙነት ለይቶ ለማወቅና ለመመስከር ያለው አስፈላጊነት በጥልቀት ካስረዱ በኋላ ሁሉም ተጋባኣያን የምሕረት መስካሪያን እንዲሆኑና ያን ለሞት የፈረዱትን በመስቅል እንዲሞት ላደረጉት ምሕረትና ይቅርታን የሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስን በመከተል የሰላምና የምሕረት ሰዎች እንዲሆኑ አደራ ማለታቸውንም አስታቋል።

እሴቶች ዙሪያ ማነጽ እሴቶችን ለትውልድ ማስተላለፍ

ብፁዕ አቡነ ሾማሊ የጥላቻ አሉታዊነቱን በማብራራት ለቂምና ለብቀላ የሚገፋ ለተበቃይ አክላዊና ስነ አእምሮአዊ ተጽእኖ የሚያሳድር ሲሆን። ቂም ይዞ ለብቀላ የሚያቀናው ሰው ፈጽሞ ውስጣዊ ነጻነት አይኖረውም፡ ስለዚህ የመጀመሪያው ነጻነትና ፈውስ ጥላቻንና የብቀላ መንፈስን መገሰጽና ማራቅ ነው። ይኽ ደግሞ እሴታዊ ሕንጸትና እሴቶችን ለትውልድ ማስተላለፍ ያለው አስፈላጊነት የሚጠቁም ተግባር ይሆናል ብለው፥ ከእሴቶች ውስጥ አንዱም የውይይት ባህል ለይተወ በመጥቀስ፡ ሌላውን ለማወቅ ለመረዳት የሚያስችል የበለጠው መሣሪያ ውይይት ነው፡ በሌላው ረገድም ውይይት የመተማመን ሁኔታ የሚፈጥርና አብሮ ለመጓዝ የሚያችል መገድ የሚያመቻች መሆኑ በስፋት ከገለጡ በኋላ “ወጣቱን ትውልድ  ገና ክሕጻንነቱ ጀምሮ በምሕረት ዙሪያ እንዲታነጽ ማድረግ እሴቶችን ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ የሚያደርግ ተግባር ነው” እንዳሉ ኤሺያን ኒውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ውይይት ለሰላም የጋራ ዓላማ

በመጨረሻም ሁሉም ተጋባእያን የተካሄደው የጋራው ዓውደ ጉባኤ ያለው አስፈላጊነትና የዚህ ዓይነቱ ውይይትና ግኑኝነት አመጽና ጥላቻ ሲያጋጥም ብቻ ሳይሆን የሰላም ባህል ዋስትና እንዲኖረው በተለያዩ ሃይማኖቶች በተለያዩ የፖለቲካ አካላት በመንግሥታት መካከል እንዲቀጥል በተለያየ ወቅት መከወን ያለበት መሆኑ በመስማማት ውይይት የሚከናወነው ሁሉም በአንድ ነጥብ ላይ እንዲስማሙ ለማድረግ ግድ ለማለት ሳይሆን ያንን ሰላም የተሰኘውን የጋራ ግብ እንዳይሳት ለማድረግና ሁሉም ሰላምን በማነጣጠር ወደ መግባባት እርቅና ይቅር መባባል እሴት እንዲል ለማድረግ ነው የሚለውን ጥልቅ ሃሳብ ማስተጋባታቸው የኢየሩሳሌምና የዮርዳኖስ የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቢተ ክርስቲያን ፓትሪያክ ይፋዊ ድረ ገጽ ዋቢ ካደረገው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ካስረጨው ዜና ለመረዳት ተችሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.