2017-07-22 08:31:00

ብፁዕ አቡነ ኣውዛ፥ አማኞች ተቀባይነት ላለው ልማት ቀዳሚ ተወናያን መሆን ይጠበቅባቸዋል


እ.ኤ.አ. ሐምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ኒው ዮርክ በሚገኘው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ ኣዳራሽ ሁሉም ሃይማኖቶች ለሰላም የተሰየመው ማኅበር፥ የተለያዩ ሃይማኖቶች ሁሉንም በሚያሳትፍ ትብብርና ኃላፊነት በተሞላው መንፈስ ድኽነት እንዲያከትም ሰላም ለማነቃቃት በጋራ  ተነቃቅተው እንዲሠሩ በሚል ርእስ ዙሪያ በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ በመሳተፍ ንግግር ያስደመጡት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ በርናርዲቶ አውዛ፥ ምእመናን ማኅበረሰብ በርትተው በጽናት ያንን ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ በስፋት ግንዛቤ እንዲያገኝና ግቡም ተለይቶ እንዲታወቅ በሚደረገው ርብርቦሽ ድጋፍ ሊያቀርቡ ይገባቸዋል ብለው ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ ተደራሽ ብሎ የሚያስቀምጠው ግብ ተጨባጭ ለማድረግ የሚያግዝ ማስተግበሪያ በትክክል ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ማስተግበሪያው ወደ ፍጻሜው የሚሸኝ እንጂ ለገዛ እራሱ ፍጻሜ አንዳልሆነ መታወቅ ይኖርበታል፡ አለ ማኅበረ ምእመናን የሃይማኖት ማኅበራትም ድጋፍና ትብብር ያንን ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ እንደ ግብ የሚያስቀምጠው ሙሉ በሙሉ እንዲስተዋልና እንዲጨበጥም ለማድረግ አስቸጋሪ መሆኑ በማስረዳት። ይኽ ማለት ደግሞ እንደ ግቦች የሚያስቀምጣቸው ዝርዝሮች ልቅ ባጣ ኤኮኖሚያዊ ምህዳራዊና ሥነ ማኅበራዊ መመዘኛዎች አማካኝነት ብቻ ሙሉ በሙሉ እንዲስተዋልና እንዲጨበጥ ለማድረግ የሚቻል እንዳልሆነ ለማመላከትና ያለውን ሥነ ምግባራዊና ሥነ ሰብእ ጎኑን በቂ ግንዛቤ እንዲሰጥበት ለማሳሰብ መሆኑ ባስደመጡት ንግግር በስፋት መተንተናቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

የሃይማኖት መሪዎች የፖለቲካ መሪዎች ወይንም የሥነ ማኅበራዊ ተመራማርያን እይደሉም። በቅድሚያ የሃይማኖት ዋነኛው ተግባር ተለይቶ እንዲታወቅ መላውን ሰብኣዊ ፍጥረት በተግባር እንዲነቃ ጥሪና አስተንፍሶ የሚያቀርቡ ናቸው። በዚህ ተዛማጅ ባህል እርሱም ሁሉም እንደ አማራጭ የሚያስቀምጥ የሥነ ምርምርና የሥነ ባህል አመለካከት ይኽ አይነቱ ተዛማጅ ባህል በሥነ ምግባር ውስጥ ጭምር እየተካተተ እሴቶችን እየተዛባ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሰብአዊ ፍጡር ያንን የእውነት ውበትና ውህበት እንዲሁም የመልካምነትን ሃልዮ (ግንዛቤ) እንዲያቅብ መደገፍ ያስፈልጋል እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥

ብፁዕነታቸው፥ የሃይማኖት መሪዎች በዓለም ከነገሮች ሁሉ በስተጀርባም ይሁን በግብራውያን ነገሮች ዘንድ ሁሉ አሻራውን የሚያስቀምጥ በሁሉም ሃይማኖቶች የሚገለጽና የሚታመን በሥነ ምርምራዊ አመክንዮና ሥነ ሃሳብ አማካኝነትም ሊደረስ የሚቻል በፍጥረት ዘንድ ሁሉ ምልክታውን የሚያኖር (የመሆን ፍንጩን የሚያስቀምጥ) ነገሮችን ህያው የሚያደርግ ፈጣሪ እንዳለ ህያውነት በሁሉም እንዲስተዋል የሚያግዙና በዚህ መሠረት ደግሞ ያንን የፈጣሪ ፍጥረት ሁሉ እንዴት እንደምንመለከትና እንደምናስተናግደው የሚደገፉ ናቸው። ስለዚህም ሁሉም ሃይማኖቶች ተቀባይነት ወዳለው ወደ አንድ የልማት እቅድ እንዲ ደረስ ኃላፊነት በተሞላው መንፈስ እንዲሠራና ወደ ምሉእ ሥነ ምህዳር ይደረስም ዘንድ የሚደገፉና ይኸንን ምሉእ ሥነ ምህዳር የሚያነቃቁ ናቸው፡ ምሉእ ሥነ ምሕዳር ተጨባጭ እንዲሆን የሚደገፉም ናቸው በማለት ያስደመጡት ንግግር እንዳልጠቃለሉ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.