Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ የአለም ዜናዎች

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዓለም ዙሪያ ሰላም ይሰፍን ዘንድ የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ከፍተኛ እንደ ሆነ ተገለጸ።

ያለመታደል ሆኖ ቀጣይነት ባለው ግጭቶች በተሞላችው ዓለማችን ውስጥ የሚታየውን ሰቆቃ እና ኢፍታዊ ተግብራት ማብቂያ ያገኙ ዘንድ፣ በግጭቶችና በጦርነት ፍጥጫ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ተሰባስበው በመወያየት ችግሮቻቸውን በሰላማዊ ሁኔታ ይፈቱ ዘንድ ስነ-ምግባራዊ አመራር የሚሰጡ እምነትን መሠረት ያደርጉ ተቋማት አስተዋጾ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!


በተለይም ደግሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዓለም ዙሪያ ሰላም ይሰፍን ዘንድ በሚያደርጉት ጠንካራ  መንፈሳዊና ስነ-ምግባራዊ የሆነ አመራር፣ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ተብሎ የሚታወቀው በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥር የሚተዳደረው ማኅበር በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ፣ በኮንጎ በመንግሥትና መንግሥትን በሚቃወሙ አንጃዎች መካከል እየተደረገ ያለው ግጭት በሰላም ይፈታ ዘንድ እያደረጉት የሚገኘው ከፍተኛ ጥረት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዓለም ዙሪያ ሰላም ይሰፍን ዘንድ የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በዋቢነት የሚያሳይ መሆኑም ይጠቀሳል።

ይህ ቀደም ሲል ያነበባችሁት አስተያየት በአፍሪካ የአሜሪካ የሲቪል-ወታደራዊ ንቅናቄ  ዋና አዛዥ የሆኑት የአምባሳደር አሌክሳንደር ላስካሪስ አስተያየት ሲሆን እኝሁ አምባሳደር ሕይወታቸውን ዘመን ሁሉ የአፍሪካን ጉዳዮች በመከታተል ያሳለፉ እንደ ነበረም የታወቀ ሲሆን በአሁኑ ጊዜም ወደ ሮም በመምጣት በሮም በሚገኘው የአሜሪካ ኤንባሲ፣ በቅድስት መንበርና በቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር መካከል ያለውን ግንኙነት ይጠነካር ዘንድ እንደ ሚሰሩም ገልጸዋል።

አንባሳደር አለክሳንደር ላስካሪስ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋዜጠኛ ሊንዳ ቦርዶኒ ጋር በነበራቸው ቆይታ በአፍሪካ በነበራቸው የግል ተመክሮ በመነሳት እንደ ገለጹት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ተቃዋሚ አንጃዎች  መካከል ያለው ልዩነት በውይይት እንዲፈታ፣ ሰላም እና እርቅ እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረገች የምትገኝ ቤተክርስቲያን መሆኑዋን አባሳደሩ ጨምረው ገልጸዋል።  

በአፍሪካ የአሜሪካ የሲቪል-ወታደራዊ ንቅናቄ  ዋና አዛዥ የሆኑት አምባሳደር አሌክሳንደር ላስካሪስ ጨምረው እንደ ገለጹት “የአሜርካን ስልታዊ ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎን በአፍሪካ ለመትግበር በምንሠራበት ወቅት ይህንን ተግባራችንን ያለ አፍሪካ የሐይማኖት መሪዎች ተሳትፎ በተሳካ መልኩ ገቢራዊ ለማድረግ አይቻልም” በማለት አስተያየታቸውን የቀጠሉት አባሳደር አሌክሳንደር “በግጭቶች ምክንያት ውጥቅጣቸው በወጣው የአንድ አንድ የአፍሪካ ሀገረት ውስጥ ሰላምን መልሶ ለማስፈን የሚደረገው ከፍተኛ ጥረት ያለ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሞራላዊ አመራር፣ የለቅድስት መንበር ተሳትፎ፣ ያለ ቫቲካን የውጭ ጉዳይ ሚንስተር ጣልቃ ገብነትና በእነዚ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ መንፈሳዊ ማኅበራት ተሳትፎ ለሰላም የሚደረገው ጥረት እና ውይይት ውጤታማ ሊሆን እንደ ማይችል በሚገባ እንረዳለን” ብለዋል።

“በጦርነት እና በተለያዩ አስከፊ ግጭቶች ውስጥ የሚገኙ ሀገራትን ወደ ሰላም መድረክ ለመመለስ የጦር መሳሪያ ካነገቡ ሰዎች ጋር መወያየት ይኖርብናል” ያሉት አንባሳደር አሌክሳንደር ላስካሪስ “ነገር ግን ይህ ውይይት ብዙን ጊዜ ዘላቂ የሆነ ሰላም ስያስገኝ አላየንም” ብለው “ይህ የጦር መሳሪያ ባነገቡ እና የጦር መሳሪያ ባልታጠቁ አንጃዎች መካከል መግባባት እንዲፈጠር ወደ ውይይት መድረክ ለመጋበዝ በሁለቱም ወገኖች መካከል ያለውን ልዩነት በቅድሚያ ማጥበብ ሰለሚገባ በዚህ ረገደ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስተዋጾ ከፍተኝ ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ሰላም በዓለም ዙሪያ ይሰፍን ዘንድ የሚያደርጉ ጥሪ እና ከፍተኝ አዎንታዊ የሆነ ተግባር የተለያዩ ተቃዋሚ አንጃዎች በጠረጴዛ ዙሪያ ቀርበው እንዲወያዩ ከማድረጉም ባሻገር የማሕበረሰቡ  ግንዛቤ እንዲዳብር በማድረግ ተጨባጭ ሰላም እንዲረጋገጥ የራሱን አስተዋጾ እያደርገ እንደ ሆነም ጨምረው ገልጸዋል።

“በተለይም ደግሞ በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ በሚገኙ ክርስቲያኖች እና የሙስሊም እምነት ተከታዮች መካከል ግጭት በተፈጠረበት ወቅት ቅዱስነታቸው በእዚያው ስፍራ በአካል በመገኘት በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ በባንጉዊ ከተማ ከሚገኘው ካቴድራል ተነስተው በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘው መስጊድ ድረስ በመሄድ ይህም ሁለቱ ማለትም ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች ተፋጠው ይገኙበት የነበረውን የጦርነት ቀጣና አቋርጠው በማለፍ የሁለቱን ሐይማኖት መሪዎች ፊት ለፊት ተገናኝተው እንዲነጋገሩ በማድረግ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ያደረጉትን ጥረት በአፍሪካ የአሜሪካ የሲቪል-ወታደራዊ ንቅናቄ ዋና አዛዥ የሆኑት የአምባሳደር አሌክሳንደር ላስካሪስ በዋቢነት በመጥቀስ ለሰላም መስፈን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስተዋጾ ከፍተኝ ነው ብለዋል።

 

22/07/2017 13:40