2017-07-20 15:12:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለአንቀጸ እምነት ተንክባካቢ ቅዱስ ማኅበር አዲስ ዋና ጸሓፊ ሰየሙ


በአንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ምክትል ዋና ጸሓፊ በመሆን በማገልገል ላይ ያነበሩት ብፁዕ ጃኮሞ ሞራንዲ ከሊቀ ጳጳስነት ማዕርግ ጋር የቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊና የቸርቨትሪ ስዩም ጳጳስ ሆነው እንዲያገለግሉ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መሰየማቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ባለፈው ሳምንት የዚህ ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ልዊስ ፍራንሲስኮ ላዳሪያ ፈረረ ኅየንተ እንዲሆኑ ብቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መሰየማቸው የሚታወስ ሲሆን፥ አዲሱ ዋና ጸሓፊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጃኮሞ ሞራንዲ እ.ኤ.አ. ነሐሰ 24 ቀን 1965 ዓ.ም. በኢጣሊያ ኤሚሊያ ሮማኛ አውራጃ ርእስ በሆነቸው በሞደና ከተማ የተወለዱ በሞደና ኖናንቶላ ሰበካ በ 1990 ዓ.ም. ማዕርገ ክህነት የተቀበሉ በ1992 ዓ.ም. በጳጳሳዊ የሥነ ቅዱስ መጽሓፍ ተቋም በስነ ቅዱስ መጽሓፍ ስነ ምርምር ተመርቀው በመቀጠልም በ 2008 ዓ.ም. በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ በሥነ አስፍሆተ ወንጌል ቲዮሎጊያ (ሥነ ወንጌላዊ ተልእኮ) ሊቅነት እንዳስመሰከሩ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ብፁዕነታቸው በተለያዩ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ኃላፊነት ሥር ካገለገሉ በኋላ የትምህርተ ክርስቶስ ሓዋርያዊ ጽሕፈት ቤት ለሞደና ኖናትቶላ ሰበካ ለጳጳስ ተጠሪ፡ የሰበካው ካቴድራል ሊቀ ካህናት ከዛም የርእሰ ሰበካው ምክልት ሊቀ ጳጳስ፡ ሞደና በሚገኘው በሥነ ሃይማኖት ሥነ ምርምር ተቋም የሥነ ቅዱስ መጽሓፍ መምህር ሮማ በሚገኘው በአለቲ ማእከል ብፁዕ ካርዲናል ስፒድሊክ የቲዮሎጊያ ተቋም የቤተ ክርስቲያን አበው ትምህርት ሥነ ትንተና መምህር ሆነው በማገልገል ላይ እያሉ በ2015 ዓ.ም. የዓንቀጸ እምነት ተከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ምክትል ዋና ጸሓፊ ሆነው መሾማቸው በማስታወስ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.