Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ቫቲካን \ ድርጊቶች

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ከእምነት ገዛ እራሱን ለሚያገል ሁሉ ክርስቲያናዊ ተስፋን እናቅርብ

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ከእምነት ገዛ እራሱን ለሚያገል ሁሉ ክርስቲያናዊ ተስፋን እናቅርብ - RV

06/07/2017 15:56

መቼም ቢሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የሆነውን ደስታችን አንዘንጋ፡ የእርሱ ፍቅር ማለቂያ የለውም ታማኝም ነው። ስለዚህ አንድ ክርስቲያን ሲከፋና ሲተክዝ ከኢየሱስ ርቋል ማለት ነው፡ ይኸንን ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ለወርሃ ሐምሌ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሐሳብ ከእምነት ስለ ራቁት ክርስቲያን ምእመናን መጸለይ የሚለውን መርሐ ግብር ይፋ ባደረጉበት በምስልና ድምጽ ተሸኝቶ ባስተላለፉት የድምጸ እይታ መልእክት መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት፥ አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ሲርቅ፥ ለብቻው ልንተወው አይገባንም። ባንጻሩ በቃል በተለይ ደግሞ በቃልና በሕይወት በተሸኘ ምስክርነት በነጻነትና በሐሴት ክርስቲያናዊ ተስፋ ልናቀርብለት ይገባል ብለው የድምጸ ርእየት መልእክታቸውን ስለ እነዚያ ከእግዚብሒር ገዛ እራሳቸው  ላራቁት ወንድሞቻችን የክርስትና ሕይወት ውበት ዳግም ለማግኘት እንዲችሉ ጸሎትና ወንጌላዊ ምስክርነ እናቅርብ በሚል ቃለ ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

06/07/2017 15:56