Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ሥርዓተ አምልኮ \ ክብረ በዓላት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ለአምስት ጳጳሳት የካርዲናልነትን ማዕረግ መስጠታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው ለአምስት ጳጳሳት የጫርዲናልነትን መዐረግ ሰጡ። - REUTERS

30/06/2017 16:19

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሰኔ 21/2009 ዓ.ም. ከተለያዩ ሀገራት ለተውጣጡ 5 ጳጳሳት የካርዲናልነት ማዕረግ መስጠታቸው ታወቀ። የእነዚህ አዳዲስ ካርዲናሎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው።

  1.  የባማኮ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ካርዲናል ጂን ዜርቦ
  2. የባርሴሎና ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ካርዲናል ዣን ጆዜ ኦሜላ
  3. የስቶኮልም ሀገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት ካርዲናል አንድሽ አርቦሌየስ
  4. የፓኬሴ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት ካርዲናል  ሉዊስ ማሪዬ ሊንግ ማንካኔኩን
  5. የሳን ሳንሳልቫዶር ጳጳስ የሆኑት ካርዲናል ግሬጎሪዮ ሮዛ ቻቬስ መሆናቸውም ተገልጹዋል።

ቅዱስነታቸው ይህንን የካርዲናልነት ማዕረግ ለጳጳሳቱ ከሰጡ ቡኃላ ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት እነዚህ አዳዲስ ካርዲናሎች “ኢየሱስ የሁሉም ሕዝብ አገልጋይ ሆነ እንደ መጣ ሁሉ እነርሱም፣ እርሱ የሰጣቸውን አብነት በመከተልና ከእርሱ ጋር በመሆን ይህንን መንፈሳዊ አገልግሎት ለወንድም እህቶቻቸው አጠናክረው መስጠት እንዳለባቸው ቅዱስነታቸው አሳስበው በአሁኑ ወቅት የሚታዩትን ተጨባጭ የሆኑ የሰው ልጆች ስቃይ በመመልከት  መፍትሄ እንድትፈልጉ ነው ክርስቶስ የጠራችሁ” ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜ በዓለማችን የሚታዩ ኃጢኣቶችንና በሕዝቡ ላይ ሊፈጥሩ የሚችሉትን አሉታዊ ተጽህኖ መጋፈጥ ይኖርባችዋል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስን በመከተል ትኩረታችሁን በኢየሱስ መስቀል እና በትንሳኤው ላይ በማድረግ ከእግዚኣብሔር ሕዝብ ፊት ለፊት ቀድማችሁ በመሄድ ይኖርባችኃል ብለዋል።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሕግ እና ስርዓት መሰረት አንድ ካርዲናል በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን የማማከር፣ አዲስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሚሾሙበት ወቅት በምርጫው ላይ በመሳተፍ የመምረጥ እና የመመረጥ መብት እንዳለቸው የሚታወቅ ሲሆን እንዲሁም ወሳኝ በሚባሉ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ የቤተ ክርስቲያኗ እምነት እና አስተምህሮ መስመሩን ጠብቆ እንዲጓዝ የምድረግ ኃልፊነት እንደ ተጣለባቸው ይታወቃል።

 

30/06/2017 16:19