2017-06-29 12:24:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሰኔ 20/2009 ዓ.ም. ስመተ ጵጵስና የተቀበሉበትን 25 አመት አከበሩ!


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሰኔ 20/2009 ዓ.ም.  ስመተ ጵጵስና የተቀበሉበትን 25 አመት ማክበራቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው በትላንትንው እለት በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ የጸሎት ቤት ካህናት እና ብጹዐን ጳጳሳት በተገኙበት የምስጋና መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በእለቱም በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር መስረት በቀዳሚነት በተነበበው የእግዚኣብሔር ቃል ላይ ተመርኩዘው ቅዱስነታቸው ያሰሙት ስብከት የአብርሃም እና የሎጥ ታሪክ ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በተለይም እግዚኣብሔር በእምነት አባታችን ለሆነው አብርሃም ተናግሮት በነበረው ተነስ!  ውጣ!  ተስፋ አድርግ! "በሚሉ ሦስት ቃላት ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ ለመረዳት ትችሉዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

“አብርሃም በእግዚኣብሔር በተጠራበት ወቅት ከሞላ ጎደል የእኛን ያህል እድሜ ነበረው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምንም እንኳን አብራሃም እንደ ማንኛውም በእድሜ የገፋ ሰው፣ ህመም እና ድካም ይሰማው የነበረ ሰው ቢሆንም እግዚኣብሔር ግን አብርሃምን ልክ እንደ አንድ ወጣት ሰው በመቁጠር ተንስ! ተመልከት ተስፋ አትቁረጥ ብሎት እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

በእዚያን ወቅት እግዚኣብሔር ለአብርሃም የሰጠውን ይህንን ትእዛዝ ዛሬም ቢሆን በተመሳሳይ መልኩ “እንድንነሳ፣ ከአድማስ ባሻገር አሻግረን እድንመለከት፣ ተስፋ በሌለበት ቦታ ተስፋ ማድረግ እንድንችል ይህንን ትእዛዝ ለእኛም ይሰጠናል ብለዋል።

ተነስ! አሻግረህ ተመልከት! ተስፋ አድርግ! የሚሉትን ቃላት ሁልጊዜም ቢሆን በሕይወታችን ማለም የሚገባን ቃላቶች ሊሆኑ ይገባል ያሉት ቅዱስነታቸው እኛ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች እንደ መሆናችን መጠን ይህንን እልም ለወጣቱ ትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል ካሉ ቡኃላ በእዚህ ከእኛ በወረሱት ሕልም ታግዘው መልካም ነገሮችን መመኘት እንዲችሉ፣ ብሎም ሥራቸውን በአግባቡ መከናውን እንዲችሉ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እንደ የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሕዳር 17/1936 ዓ.ም. በአርጄንቲና ዋና ከተማ በቦነስ አይረስ መወለዳቸው የሚታወቅ ሲሆን እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በሕዳር 13/1969 ዓ.ም. የክህነት ማዕረግ መቀበላቸው ያታወቃል። እንደ የአውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር  በሰኔ 27/1992 ዓ.ም. መዕረገ ጵጵስና የተቀበሉ ሲሆን በየካቲት 21/2001 ዓ.ም. በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት ከዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ የካርዲናልነት ማዕረግ መቀበላቸው እና በ2013 ዓ.ም. የቀደሞውን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት የነበሩትን በኔዴክቶስ 16ኛ ተክተው 266ኛው የዓለም አቀፋዊቷ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል። 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.