2017-06-21 16:42:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ አባ ሚላኒ ለወንጌል የታመነ ሕይወት አብነት


እ.ኤ.አ. ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባርቢያና ከተማ ወደ ሚገኘው የአባ ሎረንዞ ሚላኒ አጽም ወደ አረፈበት የመቃብር ሥፍራ የግል መንፈሳዊ ንግደት ፈጽመው ጸሎት ማሳረጋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሉካ ኮላዲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

እነዚህ ሁለቱ የኢጣሊያ ዜጋ የሆኑት ካህናት በኢጣሊያና በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በተለይ ደግሞ ወንጌላዊ ባህል በቃልና በሕይወት በማስፋፋት ወንጌላዊ ሕይወት በመኖራቸው ብቻ እንቅፋት ሆነው ቢታዩም ኢየሱስን የመምሰል መንገድ ብቻ ግድ ያላቸው የድኾች ሰብአዊ መብትና ክብር ሙሉ በሙሉ እንዲከበር ያስተማሩ ለተናቁት ለድኾች ጠበቃ ሆነው ክህነታዊ ሕይወታቸውን ድምጽ ለሌለው ድምጽ በመሆን በሙላት የኖሩ ጥለዉት ያለፉትን ክርስቲያናዊ ምስክርነት ዳግም የሚያነቃቃ ሐዋርያዊ ጉብኝት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ፈጽመው ባስደመጡት ቃል፥

“ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ መሆን፡ አለ ቃል ሰብአዊ መብትና ክብር የለም። በሥራና ሙሉ በሙሉ የቤተ ክርስቲያን አባል በመሆን በምትኖርበት ማኅበረሰብ ዘንድ ሙሉ ዜጋዊ ሆኖ ለመኖር የሚያስችለው መንገድ የሚከፍት ቃል ነው። ድምጽ ለሌለው ድምጽና ቃል በመሆን ለሰብአዊ መብትና ክብር ጠበቃ መሆን” ያለው አስፈላጊነት አበክረው፡ አባ ሚላኒ በሰማያዊ ቤት የተወለዱበትን ዝክረ 50ኛ ዓመት ምክንያት ቅዱስነታቸው ባካሄዱት መንፈሳዊ ንግደት፥ አባ ሚላኒ ገዛ እራሳቸውን በሙላት ለኢየሱስ ክርስቶስ በመስጠት በእርሱ አማካኝነት ወንድሞች ጋር በመገናኘትና ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ቅርብ በመሆን ይኸንን ቅርበት ስለ ክብራቸውና መብታቸው በመከራከር ተርጉመው ሰብአዊ መብትና ክብር መቼም ቢሆን መጣስ የሌለበት የእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ ሆነን በመፈጠራቸን ላይ ንቡር የሆነ መለያችን መሆኑ ያስገነዘቡ ናቸው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኮላዲ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን በዚህ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ያንን አባ ሚላኒ በሕይወ ዘመኑ ይመኘው የነበረው በጳጳሱና በሮማው ጳጳስ ተሰሚነት አግኝተው እሳቸው ያነቃቁት የነበረው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ቤተ ክርስቲያን ተቀባይነት በመስጠት ትደግፍላቸው ዘንድ ይመኙት የነበረውን ነገር ግን በዚያኑ ወቅት ያልታደሉትን ተቀባይነት የሚሰጥና ሙሉ እወቅና የሚሰጥ ወንጌላዊ አገልግሎታቸው ብዙውን ጊዜ በአሁኑ ሰዓት የሚታየው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መደናገር የሌለበት በቀጥታ ድምጽ ለሌለ ድምጽ ለተናቀውና ለድኻው ጠበቃ በመሆን ክርስቶሳዊ ሕይወት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመሰከሩ ፍትህ ያነቃቁ፥ የሁሉም መሠረታዊ ፍላጎት መጠለያ ሕክምና ትምህርት ምግብ የማግኘት መብት አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲረጋገጥላቸው ካለ መታከት ፍትህ እኩልነትና ወንድማማችነትን ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ የሰበኩ መሆናቸው መስክረዋል ያሉት ልኡክ ጋዜጠኛ ኮላዲ አያይዘው፥ ቅዱስ አባታችን፥ በዚህ ባካሄዱት ጉብኝት የአባ ሚላኒ የሕንጸ ስልት በመከተል በዚህ እጅግ ከባድ በሆነው ዘመን በሕንጸት ተልእኮ የሚያገለግሉት ኣባ ሚላኒ በቅርበት ያወቁዋቸው በአሁኑ ሰዓት በእድሜ የገፉት ሌሎች ታሪካቸው በማንበብ ጥለዉት ያለው አብነት በመከተል የአባ ሚላኒ የሕንጸት ሥልት በመከተል የሚያገለግሉትን ሁሉ አመስግነው፥ “አባ ሚላኒ ቤተ ክርስቲያን እንዴት መፈቀር እንዳለባትና በውስጧ እንዴት መኖር እንዳለብን በቃልና በሕይወት ያስተማሩ ናቸው ምንም እንኳ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስቃይ ቢደርስብንም ቤተ ክርስቲያንን ማፍቅር። እውነትን በመከተልና በመኖር የመሰከሩት ምናልባት ውጥረት የፈጠረ መስሎ ቢታይም ነገር ግን ፈጽሞ ከቤተ ክርስቲያን እራሱን ያላገለለ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የኖረ ካህን ነበር” ካሉ በኋላ ቅዱስ አባታችን አክለው የእሳቸው እዛው መገኘት በመቃብሩ ሥፍራ ተገኝተው ጸሎት ለማሳረግ መወሰናቸው ያንን የአባ ሚላኒ እናት ልጃቸው ክህነት ተቀብሎ የኖረው ሕይወት የሰጠው አገልግሎት ለመለያየት ምክንያት ሳይሆን ለውህደትና ለቤተ ክርስቲያን ክብር መሆኑ እንዲታወቅለት አገልግሎቱና ምስክርነቱ ለቤተ ክርስቲያን ፍቅር እንደሆነ ከቤተ ክርስቲያን እውቅና እንዲያገኝ የነበራቸው ምኞት ምክንያት ይኸው በልጃቸው የመቃብር ሥፍራ በመገኘት ለመጸለይ እንደፈለጉና አባ ሚላኒ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ መሆናቸው ለማረጋገጥ መሆኑ ባስደመጡት ቃል ማብራራታቸው ኮላዲ ይጠቁማሉ።

ልጄን እጅግ ያሰቃየች ቤተ ክርስቲያን ክህነቱን የሰጠቸውም እርሷ ነች። የሚደንቀኝ የልጄ ትልቅ እምነት ነው፡ በማለት የአባ ሚላኒ እናት በአንድ ወቅት የተናገሩትን ቃል ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን በእውነቱ አባ ሚላኒ እውነተኛ ካህን ናቸው፡ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ እግዚአብሒርንን ድኾችን በክርስቶስ ያፈቀረ ካህን ነው በማለት ያስደመጡት ቃል አጠቃለው እዛው በአባ ሚላኒ የመቃብር ሥፍራ ለተገኙት ሁሉ ማመስገናቸው ልኡክ ጋዜጠኛ ኮላዲ አስታውቁ፡








All the contents on this site are copyrighted ©.