Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ሐዋርያዊ ጉዞዎችና ጉብኝቶች

ቅዱስ አባታችን፥ እንደ አባ ማዞላሪ የጠፉትን የምትፈልግና ድኾችን የምታፈቅር ቤተ ክርስቲያን እንሁን

ቅዱስ አባታችን፥ እንደ አባ ማዞላሪ የጠፉትን የምትፈልግና ድኾችን የምታፈቅር ቤተ ክርስቲያን እንሁን - REUTERS

21/06/2017 16:37

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሎምባርዲያ ክፍለ ሃገር ማንቶቫ አውራጃ በምትገኘው በከተማ ቦዞሎ የሚገኘውን የአባ ፕሪሞ ማዞላሪ የመቃብር ሥፍራ መንፈሳዊ ንግደት ፈጽመው ጸሎት ማሳረቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አያይዘው፥ የክረሞና ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ናፖሊዮኒ በዚህ አጋጣሚም እ.ኤ.አ. መስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም.  ቤተ ክርስቲያን ለአባ ማዞላሪ ብፁዕና ለማወጅ የሚያስችለው ቤተ ክርስቲያናዊ ሂደት መጀመሩንም ማሳወቃቸው ጠቁመው፡ ቅዱስ አባታችን በዚህ በአባ ማዞላሪ አጽም ባረፈበት ሥፍራ ተገኝተው የግል መንፈሳዊ ንግደት ፈጽመዋል፡ ሆኖም የግል ያሉት መሆኑ ቀርቶ ባንድ ወቅት አባ ማዞላሪ፥ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ፍቅሩ አለኝ በማለት የተናገሩት ቃል እንደ መንፈሳዊ መርሕ ያነገቡ ብዙ የአባ ማዞላሪ ወዳጆች ምእመናንና ወጣቶች መገኘታቸው ገልጠው፥ በዚህ አጋጣሚም ቅዱስነታቸው በለገሱት ቃለ ምዕዳን፡ አባ ማዞላሪን የኖሩት ሕይወት የክርስትናን ሕይወት በሚገባ ለማይኖሩ ሁሉ እንቅፋት ነበር፡ ይኽም ክርስቲያን ነን ባዮች በተግባር ግን ክርስቲያን ያልሆነ ሕይወት ይኖር ለበሩት ሁሉ እንቅፋት ነበር፡ ፈሪሳዊነት ያማይኖር ክህነት ለቤተ ክርስቲያን ኃይል መሆኑ አስመስክረዋል፡ አባ ማዞላሪም ይኸንን ዓይነት ክህነት በኢጣሊያ የኖሩ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ናቸው፡ ያሉት ቅዱስ አባታችን አያይዘውም አባ ፕሪሞ ማዞላሪ የኢጣሊያ ቆሞስ በማለት ገልጠው፥ ያንን ባንድ ወቅት ጳውሎስ ስድስተኛ ይኸንን ነቢይ የሆነው የቦዞሎ ቆሞስ እግር እግሩን መከተል ምንኛ ይከብዳል ብለው ትልቅና ጥልቅ ካህን ነቢይም በማለት ገልጠዉት እንደነበርም አስታውሰው “የአባ ማዞላሪ ቃልና ስብከትና ጽሑፍ በጠቅላላ ከዚያ ከእግዚአብሔር ቃል የመነጨ ወደ ማንኛውም ተራና ልሙድ ተግባር ሳያወርዱ የቅዱሳት ሚሥጥራት አሰራራቸውና የሚያሳርጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወንጌላዊነት የተካነ አሳማኝ፡ ጥልቅ እምነት የሚያንጸባርቅ ይኸንን የሚከታተል ውስጡ ከመነካት አልፎ ከአሳማኝ እምነት ጋር የሚያገናኝ ነበር፡ እራሳቸውን በመለወጥ ሌሎችንና ዓለምን ለመለወጥ ጥረት ካደረጉት የቤተ ክርስቲያን ልጆች ውስጥ አንዱ ናቸው፡ የእግዚአብሔር ምሕረት ያስቀድሙ ናቸው” በማለትም እንደገለጡዋቸው አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።

ቤተ ክርስቲያንን ላለፈው ታርክ እስረኛ ሳትሆን ቤተ ክርስቲያንና ዓለምን ገዛ እራሱ አሳልፎ በሰጠው ፍቅር አማካኝነት ለመለወጥ ቃል ሥጋ ሆነ በእኛም መካከልም አደራ የሚለውን የትስብእቱ ቲዮሎጊያ የቁምስና ማእከል በማድረግ ሰብአዊነታችንን ዳግም ሊያጎናጽፈን የመጣው ኢየሱስ በመከተል ይኸንን አዲስ ሰብአዊነት በማስፋፋት ቁምስና የህልውናና የከተሞቻችን ጥጋ ጥግ ወደ ሆነው ክልል በማቅናት የሕዝበ እግዚአብሔር ቤት እንድትሆን የጣሩ መሆናቸው ያስረዱት ቅዱስ አባታችን አያይዘው፥ አባ ማዞላሪ የዓለማችን ዕጣ እድል በዚያ በህልውናና በከተሞቻችን ጥጋ ጥግ የጸና መሆኑ ታምነው የጠፉትን ፍለጋ የተጉ በመሆናቸውም ለራቁት ቆሞስ የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው ከመሆኑም ባሻገር ማንም ለእግዚአብሔር ፍቅር ሩቅ እንዳልሆነ በማስተማር በድኽነት የኖሩ እንጂ ድኻ ካህን እንዳልነበሩ ገልጠዋል ያሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው ሁሉም የአባ ማዞላሪ መንፈሳዊነት እንደ ትልቅ መንፈሳዊ ሃብት በመመልከት የእሳቸውን አብነት በመከተል ማንም ከድህነት እቅድ ውጭ እንዳልሆነና የመዳን እቅድ እግዚአብሔር ለሁሉ ሰው ዘር የሰጠው ጸጋ ነው እንዳሉ አስታወቀዋል።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን የአባ ማዞላሪ ጽሎት እርሱም ያንን የእዚአብሔር ምህረት የሚያስታውስ ማንም ለምህረቱ ብቃት ያለው ሳይሆን የእግዚአብሔር መሓሪነት ብቃት አልቦነታችን ሐጢኣተኝነታችንን ሁሉ ተሻግሮ እኛነታችንን የሚሻ መሆኑ በጥልቀት የሚያብራራውን የድህነት ጸጋ ላይ ያማከለውን ጸሎታቸውን ደግመው ለተመሳሳይ የግል መንፈሳዊ ጉብኝት ወደ የአባ ሚላኒ የመቃብር ስፍራ ወደ ሚገኝበት ባርቢያና ከተማ ከመነሳታቸው በፊት እዛው ለተገኙትን ሁሉ ሐዋርያው ቡራኬ መስጠታቸው ጂሶቲ ገልጡ።

21/06/2017 16:37