2017-06-20 12:29:00

“በቀላሉ ተሰባሪ በሆነው ሥጋው እና ደሙ አማካይነት ኢየሱስ እኛን ለመገናኘት መጥቱዋል።


በሰኔ 11/2009 ዓ.ም. በመላው ዓለም በሚገኙ የላቲን ሥርዓተ አምልኮ አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናኖች ዘንድ ክቡር የሆነው የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋው እና ክቡር ደም የሚዘከርበት አመታዊ ክብረ በዓል በደመቀ ሁኔት ተክብሮ ማለፉን መጥቀሳችን ይታወሳል። ቅዱስነታቸው ይህንን በዓል ለማክበር በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕማና እና የሀገር ጎብኝዎች ካደረጉት አስተንትኖ በመቀጠል አመሻሹ ላይ በሮም ከተማ በሚገኘው የቅዱስ ዩሐንስ ላቴራን ባዚሊካ መስዋዕተ ቅዳሴን በሳቸው መሪነት አስራገው እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን በወቅቱም ያሰሙት ስብከት “መታሰቢያ” በሚል ጭብጥ ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ ገልጸው ይህም “ጌታ ለእኛ ሲል ያደረገውን ሁሉ መሆኑን በማስታወስ የመዳኛችን ታሪክ መሠረት ነው" ብለዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮ የክርስቶስ ቅድሱ ሥጋ እና ክቡር ደም በተዘከረበት አመታዊ ክብረ በዓል ላይ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

በዚህ የክርስቶስ ቅድሱ ሥጋ እና ክቡር ደም በተዘከረበት አመታዊ ክብረ በዓል ላይመታሰቢያየሚለው ቃል በተደጋጋሚ ተገልጹዋል። ሙሴ ለሕዝቡአምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ትእዛዞቹን መጠበቅህንና በልብህ ያለውን ለማወቅ፣ ትሑት ሊያደርግህና ሊፈትንህ በእነዚህ አርባ ዓመታት በዚህ ምድረ በዳ ጒዞህ ሁሉ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ። ልብህ ይታበይና ከባርነት ምድር፣ ከግብፅ ያወጣህን አምላክህንእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ትረሳለህ። በመጨረሻ መልካም እንዲሆንልህ፣ አንተን ትሑት ለማድረግና ለመፈተን፣ አባቶችህ ፈጽሞ የማያውቁትን መና በምድረ በዳ መገበህ” (ዘዳግም 82,14,16) ብሎ ተናግሮ ነበር። ኢየሱስም ለእኛይህንን የእኔ መታሰቢያ አድርጉ” (1ቆሮ 1124) በማለት ተናግሮናል።ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ” (የሐንስ 651) እውነተኛ እና ተጨባጭ በሆነ መንገድ እግዚኣብሔር ለእኛ ያለውን የፍቅር ታሪክ የሚያስታውሰን የመታሰቢያ ምስጢር ነው።

ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል እያንዳንዳችን  አስታውስ! ይላል። ጌታ ሕዝቡን በበረሃ የመራበትን እና ሕዝቦቹን በበረሃ ያደረጉትን ጉዞ እንዲወጡ ብርታት እንደ ሰጣቸው፣ ማስታወስ፣ በእያንዳዳችን የግል በደኅነነት ታሪክ ውስጥ ጌታ የጣለውን መሠረት አስታውሱ ይለናል። ውሃ ለአንድ ተክል አስፈላጊ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ማስታወስ የሚለው ቃል ደግሞ ለእምነት ወሳኝ ነገር ነው። አንድ ተክል ያለ ውሃ በሕይወት ቆይቶ ፍሬ ማፍራት አይችልም። እንዲሁም እምነታችን በጥልቀት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ያደረገውን ተግባር ትውስታ የማይጠጣ ከሆነ ፍሬ ሊያፈራ አይችልም ማለት ነው።

አስታውሱ! ማስታወስ በጣም ጠቃሚ የሆነ ነገር ነው፣ ምክንያቱ ማን እንደ ወደደን በፍጹም እንዳንረሳና እኛም በምላሹ ማንን ለመውደድ እንደ ተጠራን እንድናስታውስ በማድረግ  በፍቅርና በጥንቃቄ እንድንኖር ያደርገናል። ሆኖም በአሁኑ ጊዜ ይህ ጌታ ቀጣይነት ባለው መልኩ በተናጥል የሰጠን እለታዊ ችሎታ በጣም እየተዳከመ መጥቱዋል። በጣም የተጨናነቀ እንቅስቃሴዎችን ከማድረግ የተነሳ ብዙ ሰዎች ግራ በተጋቡ ክስተቶች ውስጥ ይገኛሉ። ይህ በሚሆንበት ወቅት ትውስታዎችን መልሰን ለመቀናጀት ያስችለን ዘንድ የማስታወሻ ገጾችን መገለባበጥ ያስፈልጋል። ትእዛዛቶችን ወደ ኃላ ጥለን በአሁኑ ወቅት ብቻ ለመኖር ስንሞክር በጥልቀት ሳይሆን ነገሮችን ላይ ላያቸውን ብቻ በማየት፣ ማን እንደ ሆንን እና ወደ የት እንደ ምንሄድ ሰፋ አድርገን መመልከት ያዳግተናል። በዚህ መንገድ የእኛ ሕይወት የተፈረካከሰ እና የደነዘዘ ይሆናል።

ሆኖም ዛሬ ይህ ታላቅ በዓል ያልተሟላውን ሕይወታችን ጌታ ተወዳጅናበቀላሉ ተሰባሪ በሆነው ሥጋው እና ደሙ አማካይነት እኛን ለመገናኘት መጥቱዋል። የሕይወት እንጀራ በመሆን ጌታ ራሱን የዋህና ትውስታችንን የሚፈውስ መብል በመሆን ወደ እኛ መጥቱዋል። ቅዱስ ቁርባን የእግዚኣብሔር ፍቅር ማስታወሻ ነው።  “የክርስቶስ መከራ ማስታወሻ ነው እግዚኣብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር የሚታወስበት ነው፣ ይህም ጥናካሬን የሚሰጥና በጉዞዋችን የሚደግፈን ነው። የክርስቶስን ክቡር ሥጋና ደም ማስታውስ መልካም የሆነ ስሜት የሚፈጥርብን በዚሁ ምክንያት ነው። ረቂቅ፣ ቀዝቃዛ እና ጥልቅ መሰረት የሌለው ነገር ሳይሆን ነገር ግን የእግዚኣብሔርን ፍቅር የሚገልጽ የሕይወት ማስታወሻ ነው። ቅዱስ ቁርባን የተገለልን ሰዎች እንዳልሆንን ነገር ግን የክርስቶስ አንዱ አካል እንደ ሆንን ያስታውሰናል። በበረሃ የነበሩ ሕዝቦች ከሰማይ የወረደውን መና እንደ ሰብሰቡ ሁሉ ከሰማይ የወረደ የክርስቶስ እንጀራ ሁላችንም እንድንቀበለው እና ከእርሱ ጋር እንድንቋደስ ይጠራናል። ቅዱስ ቁርባን የአንድነት ሚስጢር ነው። የሚቀበለው ሁሉ ሰላምን ያገኛል። ይህንን ታላቅ ስጦታ ስለሰጠን ጌታን ማምለክ እና ማመስገን ይገባናል፣ የእርሱ ህያው የሆነ የፍቅር ማስታወሻ አንድ አካል እንያደርገን እና ወደ ህብረት እንዲመራን እንጸልይ።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ቀደም ሲል ስትከታተሉት የቆያችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮ የክርስቶስ ክቡር ሥጋ እና ክቡር ደም በተዘከረበት አመታዊ ክብረ በዓል ላይ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን ነበር።








All the contents on this site are copyrighted ©.