2017-06-17 08:52:00

አገረ ቫቲካን፡ ሙስናና የሙስና ተግባር የሚያስከተለው እክል ዙሪያ ዓውደ ጉባኤ ተካሄደ


እ.ኤ.አ. ሰነ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. የኵላዊት ቤተ ክርስቲያንና የሕግና ፍትሕ አካላት የተለያዩ የጸረ ሙስና አቀንቃኝ እንዲሁም የወንጀል ቡድኖች ሰለባ የሆኑትን የሚያቅፈው የጸረ የወንጀል ቡድኖች ማኅበራት ተወካዮች ያሳተፈ ሙስንና ግብረ ሙስና የሚያስከተለው ሰብአዊና ማኅበራዊ እክሎች ዙሪያ የመከረ ዓውደ ጉባኤ መካሄዱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታወቁ።

ዓውደ ጉባኤው ከጳጳሳዊ የስነ ማኅበራዊ ስነ ምርምር ተቋም ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ጳጳሳዊ የምሉእ እድገት አገልግሎት ተንከባካቢ ጽሕፈት ቤት ሲሆን፡ ጸረ ሙስናና ሙስና የሚያስከትለው ችግር ለመቅረፍ መለያና ዓላማ በሚል ርእስ ሥር የረቀቀው ሰነድ ዙሪያ በመወያየትም የሚታከል በማከልና የሚታረምም በማረም ሰነዱን በማጽደቅ መፈጸሙንም የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ በማስከተል፥ ሙስናን ይኸንን ሰብአዊና ማኅበራዊ ነቀርሳ የሆነው ኢግብረ ገባዊና ኢሰብአዊ ተግባር ለመዋጋት የሚያግዝ ባህል ለማስፋፋት የሚደግፍ ሰነድ መሆኑ ጳጳሳዊ የምሉእ ሰብአዊ አገልግሎት ተንከባካቢ ጽሕፈት ቤት ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፒተር ቱርክሶን ለጉኤው ባስደመጡት ንግግር በማስታወስ፥ ይኽ ዓለም አቀፍ አውደ ጉባኤ ስለ ሙስናና መዘዙንም ጭምር ለመወያየት ያቀደውም ይኸንን የሰውን ልጅ ሰብአዊ ክብር የሚሰርዝ የሚረግጥ ሰብአዊነትን ለሚተላለፉ ምክንያቶች የሚዳርግ በመሆኑና እያንዳንዱ በሙስና የተዘፈቀውን ሰው ውስጥነቱን እንደ ነቀርሳ እያሰለለ መላ ስብእናውን የሚያፈርስና እንደ ወረርሽኝ በሽታ እየተዛመተም ማኅበራዊ ጥቅም በማጥቃት አገርንና ሕዝብ ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ ነው፡ ስለዚህ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ተግቶ መንቃት ሙስናን በመዋጋት ጭምር የሚገለጥ ተግባር ነው እንዳሉ ይጠቁማሉ።

ቀጥለወም በጉባኤው ንግግር ያስደመጡት የጳጳሳዊ ለምሉእ እድገት አገልግሎት ተንከባካቢ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሓፊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማዚ ሲሆኑ፡ ብፁዕነታቸው የዚህ ዓውደ ጉባኤ ዋና ዓላማዎች ከሚባሉት ውስጥ አንዱ በዓለማችን በጠቅላላ አገሮች የሙስና መቅጫ ሕግ አለ። ሆኖም ሙስናን በጸረ ሙስና መቅጫ ሕግ ብቻ ሳይሆን ይኸንን ሰብአዊና ማኅበራዊ ነቀርሳ ለመዋጋት የሚያስችለው በሽታውን አስቀድሞ ለመከላከል ፖለቲካዊ እንዲህም የሕግና ፍትሕ መሣሪያ ጭምር እንዲኖርና የጸረ ሙስና ባህል በማነቃቃት ነው እንዳሉ ዶኒኒ ያመለክታሉ።

በተያያዘ መልኩም ማኅበራዊ አስተያየቶች በጸረ ሙስና ባህል ንቃት እንዲኖራቸው ምን መደረገ አለበት ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠትና ሙስና የሚያነቃቃው ምክንያት ሁሉ ፈትሾ መንስኤው በመለየት ይኸንን የሕዝቦችና የአገሮች በተለይ ደግሞ የድኾች አገሮች በኤኮኖሚ በሰብአዊና በማኅበራዊ እድገት ወደ ፊት እንዳይሉ የሚቀይደውን በመንግስትና በሕዝብ በሰዎች መካከልም ሊኖር የሚገባውን ጤናማውን ግኑኝነት የሚያወክ ተግባር ለማስወገድ የሁሉም ጥረት ለማነቃቃት ነው ካሉ በኋላ አያይዘውም ባጠቃላይ ጉባኤው የጋራ ጥቅም ዋስትና እንዲያገኝ የጋራ ጥቅም በመዋስ የእያንዳንዱ ዜጋ መብትና ክብር ለማረጋገጥ ጸረ ሙስና የሆነ አመለካከትና ባህል ለማስፋፋት የሚያግዝ መንገድ ለይቶ የሚጠቁም ዓውደ ጉባኤ ነው እንዳሉ ዶኒኒ ገልጠዋል።

በዓውደ ጉባኤው ንግግር ባማስደምጥ የተሳተፉት የኢጣሊያ የጸረ ሙስና ባለ ሥልጣን ተቋም ሊቀ መንበር ራፋኤለ ካንቶነ፥ ከጉባኤው ፍጻሜ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ይኽ ዓለም አቀፍ ዓውደ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙስና ዙሪያ የመከረ ልዩና ዓይነተኛ ጉባኤ ነው። ሙስና የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በማጠናከር የእስራት ዓመታት በማራዘም ሳይሆን ባህላዊ ትግል በማስፋፋትና ግብረ ገባዊ ሕሊና በማጎልበት ነው ለማስወገድ የሚቻለው። ስለዚህም ነው ቤተ ክርስቲያንና ቅዱስ አባታችን የዚህ ዓይነቱ ዓውደ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲካሄድ ያነቃቁትጉባኤው ለመላ ዓለም አገሮች ሙስና የሕዝቦች አብሮነትን ከማናጋት አልፎ እጅግ ለስቃይ የሚዳርገውም ድኻው የሕብረተሰብ ክፍል ነው ምክንያቱም ብሩህ መጻኢን የሚነጥቅ ነውናየዚህ ዓይነቱ ዓለም አቀፋዊ ዓውደ ጉባኤ ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግና ከወዲሁ ወጣቱ ትውልድ በጸረ ሙስና ባህል ታንጾ እንዲያድግ የዚህ ማኅበራዊነትን ሰብአዊነትን የጋራ ጥቅምን ጭምር የሚጎዳው ሙስና ቀድሞ ለመከላከል የሚያግዘው ስነ ልቦናዊ ግብረ ገባዊ ባህላዊ ንቃት እንዲጎልብት ሁሉም አገሮች ይኸንን በማስተዋል ሙስናን በመዋጋቱ ጥረት ነቅተው እንዲገኙ ለማድረግ ነው ብሏል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.