2017-06-15 10:18:00

የክርስቲያን ምስክርነት ለዓለም ጨው እና ብርሃን መሆን ማለት ነው እንጂ ሰው ሠራሽ የደኅንነት ዋስትና ማረጋገጫ አይደለም።


የክርስቲያን ምስክርነት ለዓለም ጨው እና ብርሃን መሆን ማለት ነው እንጂ ሰው ሠራሽ የደኅንነት ዋስትና ማረጋገጫ አይደለም።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሰኔ 5/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “በሕይወታቸው እግዚአብሔርን እያከበርን ለሌሎች ጨው እና ብርሃን መሆን ያስፈልጋል” ማለታቸው ተገልጹዋል። በዚህ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍርንቸስኮ አማክሪ የሆኑት ዘጠኝ ካርዲናሎች መስዋዕተ ቅዳሴውን ታድመው እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት በእለቱ በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር መሰረት ከማቴዎስ ወንጌል 5:13-16 ላይ በተነበበው የወንጌል ቃል ላይ ያተኮረ እንደ ነበረም የተገለጸ ሲሆን በዚሁ የወንጌል ቃል ላይ ተመስርተው ክርስቲያኖች “ሰው ሠራሽ የደኅንነት ዋስትናን ማረጋገጥ” አቁመው በመንፈስ ቅዱስ ላይ ያላቸው መተማመን ማሳደግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

“አዎንታ፣ ጨው እና ብርሃን” የሚሉት ሦስት ቃላት በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሱ ቁልፍ የሆኑ ቃላት ናቸው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ወንጌልን የማብሰር ሂደት ውሳኝ የሆነ ሂደት ነው እሺ ወይም እንቢ በማለት የምናወላውልበት ሰው ሰራሽ የሆነ የደኅንነት ማረጋገጫ ግን አይደለም ብለዋል።

ክርስቲያናዊ ምስክርነት እንድንሰጥ የሚረዳን መንፈስ ቅድሱ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እነዚህ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ውስጥ የተጠቀሱት ሦስቱ ቃላት የወንጌልን ኃይል የሚያመላክቱ ቃላት ናቸው ካሉ ቡኃላ ምስክርነት እንድንሰጥ እና እግዚኣብሔርን እንድናከብር የረዱናል ብለዋል።

በዚህ “አዎንታ” በሚለው ቃል አማካይነት ሁሉንም የእግዚኣብሔር ቃል ኪዳን በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ እናገኛለን ያሉት ቅዱስነታቸው “ኢየሱስ ቃል የገባውን ሁሉ ሙሉ በሙሉ ፈጽሙዋል፣ ለዚህም ነው እርሱ ምልአት ነው የምንለው” ብለዋል።

በኢየሱስ ዘንድ “እንቢዬው” የሚል ቃል በፍጹም የለም ሁልጊዜም ቢሆን ለእግዚኣብሔር ክብር “እሺ” የሚል ቃል ብቻ ነበር ከኢየሱስ የወጣው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እኛም ይህንን የኢየሱስን እሺታ መከተል ይኖርብናል ምክንያቱም በቅባ ቅዱስ አማክይነት የእርሱ ማህትም በሆነው በመንፈስ ቅዱስ በመታተማችን የተነስ ነው ብለዋል። መንፈስ ቅዱስ ነው ነገሮችን “በእሺታ” እንድቀበል የሚረዳን ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም እሺታ ወደ ምልአት ይመራናል፣ ይህም ተመሳሳይ መንፈስ ብርሃን እና ጨው እንድንሆን ይረዳናል፣ በአጠቃላይ መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያናዊ ምስክርነትን እንድንሰጥ ኃይል ይሰጠናል ካሉ ቡኃል ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.