Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ሳይንስና ትምህርት

በእንግሊዝ ታስቦ ለሚውለው የሕይወት ቀን ምክንያት በማድረግ ቅዱስ አባታችን መልእክት አስተላለፉ

በእንግሊዝ ታስቦ ለሚውለው የሕይወት ቀን ምክንያት በማድረግ ቅዱስ አባታችን መልእክት አስተላለፉ - AFP

14/06/2017 16:33

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሰነ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. በእንግሊዝ በወይልስና በስኮትላንድ በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ታስቦ የሚውለው የሕይወት ቀን ምክንያት በማድረግየእመቤታችን ማርያም ጥበቃ በመማጠን ለእዚህች ለሕያዋን እናት ለሆነቸው እናት የሕይወት ምክንያት የሆነውም ሁሉ ለእርሷ አወክፋለሁ የሚል የልመና ጸሎት ያማከለ መልእክት ማስተላለፋቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ሲር የዜና አገልግሎት ካሰራጨው የዜና ምንጭ ለመረዳት እንደተቻለውም በወልደ እግዚአብሔር የሚያምኑ ሁሉ ካለ መታከት እውነትና ፍቅርን መሰረት በማረግ ስለ ሕይወት እንዲመሰክሩና መልካም ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ጋር በመሆንም የእውነትና የፍቅር ባህል ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት አቢይ አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው አደራ ብሏል።

የቅዱስ አባታችን ... ሐዋርያዊ ቡራኬ

ይኽ በታላቋ ብሪጣኒያ በሚገኘው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኤድዋርድ አዳምስ አማካኝነት ይድረስ በእንግሊዝና ወይልስና በስኮትላንድ ታስቦ ለሚውለው የሕይወት ቀን ዋና አስተባባሪ ብፁዕ አቡነ ጆን ሸሪንግቶን በሚል ባስተላለፉት መልእክት፥ ቅዱስ አባታችን በዚያ የሕይወት ቀን ለሚሳትፉት ሁሉ ከወዲሁ ጸሎታቸውን በማረጋገጥ ሐዋርያዊ ቡራኬአቸውንም እንዳስተላለፉ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።

የዛሬ 50 ዓመት በፊት ጽንስ ማስወረድ ዙሪያ የጸደቀው ሕግ

ይኽ በእንዲህ እንዳለም እፊታችን ጥቅምት 2017 ዓ.ም. በእንግሊዝ ወይልስና ስኮትላንድ ጽንስ ማስወረድ ጉዳይ የሚመለከት እ.ኤ.አ. ጥቅምት ወር 1967 ዓ.ም. የጸደቀው ሕግ ዝክረ 50ኛው ዓመት የሚታሰብ ሲሆን፡ ዘንድሮ የሚከበረው የሕይወት ቀን ከመወለዳቸው በፊት ጽንስ በማስወረድ ተግባር የተቀጩት የሚዘከሩበት ስለ እነርሱ የሚጸለይበትና በማያያዝም ጽንስ ለማስወረድ ፈተና ለሚጋለጡት ሳይጠብቁትና ሳያስቡት እርግዝና ላጋጠማቸው ሁሉ ወደ ጽንስ ማስወረድ ምርጫ እንዳያደሉ ሰብአዊ መንፈሳዊ ድጋፍ የማቅረቡ ድርጊት ዳግም የሚረጋገጥበት አጋጣሚ ነውሲል የእንግሊዝ ወይልስና ስኮትላንድ ብፁዓን ጳጳሳት የሕይወት ቀን ምክንያት በማድረግ ቀኑን በሚያስተባብረው ኮሚቴ አማካኝነት ባወጡት መግለጫ አማካኝነት ማሳወቃቸው ሲር የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።

ምጽዋት የሕይወት ባህል ለመደገፍ

የእንግሊዝ ወይልስና ስኮትላንድ ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት መልእክት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ምሕረትና አሳር በሚል ርእስ ሥር ለልዩ የምሕረት ዓመት መዝጊያ ባስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት ዘንድ፥ “የእግዚአብሔር ምሕረት የተጸጸተ ከአብ ጋር ዳግም ለመታረቅ ለሚሻ ልብ  ቅርብ ነው፡ ይኽ ምሕረት ባጠቃላይ የማይምረው የሐጢአት ዓይነት የለም፡ በተጸጸተ ልብ ወደ አብ ሲመጣ የእግዚአብሔር ምሕረት ላይ እርግጠኛነት መሆን ብቻ ነው የሚያስፈልገው” በማለት ያሰመሩበት ሃሳብ ዋቢ በማድረግ፡ የሕይወት ቀን የሕይወት ትርጉምና የሕይወት ክብር ሰብአዊ ሕይወት በማንኛውም የሕይወት ደረጃና ሁነትም ይሁን ፈጽሞ የማይሻረው ክብሩን ለማነቃቃት ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት ክብርነቱን የሚመሰከርበት ቀን መሆኑ ገልጠዋል ያለው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፥ በሕይወት ቀን ምክንያት በሚያርገው መስዋዕተ ቅዳሴ የሚሰበሰበው ምፅዋት ቤተ ክርስቲያን ስለ የሕይወት ባህል ለምታነቃቃው መርሐ ግብርና ለሥነ ሕይወት ሥነ ምግባር ተቋም እቅድ ማስፈጸሚያ እንደሚውል ከወዲሁ ማሳወቃቸው ያመለክታል።

14/06/2017 16:33