Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

“መጽናናት እግዚኣብሔር ለእኛ የሰጠን ስጦታ ነው፣ ይህንምም የሰጠን ሌሎችን እንድንጋለግልበት እና እንድናጽናና ነው።

ቅዱስነታቸው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት በትላንትናው ቀን ማለትም በሰኔ 5/2009 ዓ.ም. መስዋዕተ ቅዳሴን ባሳረጉበት ወቅት።

13/06/2017 09:42

“መጽናናት እግዚኣብሔር ለእኛ የሰጠን ስጦታ ነው፣ ይህንምም የሰጠን ሌሎችን እንድንጋለግልበት እና እንድናጽናና ነው። ማንም ሰው ቢሆን ራሱን በራሱ በጣም ፈጣን በሆነ መልኩ ማጽናናንት አይችልም”። ይህ ቀደም ሲል ያዳመጣችሁት ሀረግ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 5/2009 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ካሰሙት ስብከት የተወሰደ ነው።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የማጽናናት ልምድ ወይም ተመክሮ እንዲኖረን ከፈለግን በቅድሚያ የተከፈተ ሊብ ሊኖረን ያስፈልጋል በማለት ስብከታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው ፍትሃዊነት የጎደለው የተዘጋ ልብ ሳይሆን በመንፈስ ራሱን ዝቅ ያደርገ ልብ ሊኖረን ይገባል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት በእለቱ በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር በቀዳሚነት በተነበበው እና ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው በሁለተኛው መልእክቱ ላይ በተደጋጋሚ የተጠቀሰው “የመጽናንት ልምድ ሊኖረን ይገባል” በሚለው ጭብጥ ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን  ቅዱስነታቸው በዚሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተመርኩዘው መንናናት ምን ማለት እንደ ሆነ ገልጸዋል።

“መጽናናት ቅጽበታዊ የሆነ ነገር አይደለም፣ የመጽናናት ልምድ መንፈሳዊ ተመክሮ ነው፣ ምልአት ይኖረው ዘንድ ከተፈለገ አንድ ሌላ አካል መጽናናቱን ሊያመጣ ያስፈልጋል፣ ማንም ሰው ሙሉ በሆነ መንገድ ራሱን በራሱ ማጽናናት አይችልም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ራሱን በራሱ ለማጽናናት የሚሞክር ሰው በመስታወት ፊት ቁሞ ራሱን በመመልከት ራሱን በራሱ ለማሳመር እንደ ማጣር ይቆጠራል ብለዋል።

እኒዚህን የመሳሰሉ ሰዎች በወንጌል ውስጥ በብዙ ቦታ ተጠቅሰው ይገኛሉ ያሉት ቅዱስነታቸው ለምሳሌም ራሳቸው በራሳቸው ሙሉ አድርገው ይቆጥሩ የነበሩትን የሕግ ምሁራንን በአብነት መጠቀስ ያችላል ካሉ ቡኃላ በተለይም ደግሞ በወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው እና “ጌታ ሆይ እንደ ዚህ ኃጥአተኛ ሰው ስላልሆንኩኝ አመሰግናለሁ ” ብሎ የጸለየውን ሰው መጥቀስ እንደ ሚችላ ገልጸዋል።

መጽናናት ከእግዚኣብሔር የሚሰጥ ስጦታ እና እኛም ሌሎችን እንድናገለግልበት የሚሰጠን ጸጋ መሆኑን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው መጽናናት እውነተኛ ይሆን ዘንድ ሌላ አጽናኝ የሆነ አካል ያስፈልጋል ብለዋል። የመጽናናት ሁሉ ምንጭ የሆነው እግዚኣብሔር በመሆኑ የተነሳ፣ አጽናኝ የሚሆነም አካል ይህንን የጸጋ ስጦታ ከእግዚኣብሔር ተቀብሎ ሌላውን ለማጽናናት መጠቀም ይኖርበታል ያሉት ቅዱስነታቸው “ማጽናናት” የተቀበልነውን ስጦታ ሌሌሎች አግልግሎት እንደ ማዋል ይቆጠራል ብለዋል።

የተዘጋ ልብ ያላቸው ሰዎች ሁሉ “በመንፈስ የበለጸጉ ሰዎች እንደ ሆኑ ራሳቸውን በመቁጠር” የሌሎች እርዳታ የማያስፈልጋቸው “ምልአት” ያላቸው ሰዎች እንደ ሆኑ አድርገው ራሳቸውን ይቆጣራሉ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እንደ እነዚህም ዓይነት ሰዎች ራሳቸውን ጻድቅ አድርገው ስለሚቆጥሩ መጸለይ አያስፈልገኝም” የሚል መንፈስ በውስጣቸው ያሳድራሉ ብለዋል።

ከዚህም አስተሳሰባቸው የተነሳ ትህታና ምን ማለት እንደ ሆነ ስለማይገባቸው ነውጠኞች ይሆናሉ፣ ፍትህ ምን ማለት እንደ ሆነ ስለማይገባቸው ፍትህን አያደርጉም፣ ይቅርታን የማድረግ ፍላጎት በፍጹም አይታይባቸውም ምክንያቱም ይቅር የመባባል አስፈላጊነት አይታያቸውም፣ “እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ልባቸው ቆሽሹዋል፣ ጦርነት ፈጣሪዎችም ናቸው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት ልባችንን መክፈት ያስፈልጋል ካሉ ቡኃላ ልባችን የተከፈተ ወይም ደግሞ ዝግ የሆነ፣ የመጽናናት ጸጋ ይሰጠው ዘንድ የሚጠይቅ ወይም ደግሞ የማይጠይቅ መሆኑን፣ ለእኛ መጽናናት የተሰጠን ሌሎችን ለማጽናናት መሆኑን የሚገነዘብ ወይም የማይገነዘብ ልብ እንዳለን ወይም እንደ ሌለን ራሳችን ለራስችን ጥያቄን ማቅረብ ይገባል ብለው የእግዚኣብሔርን መጽናናት ለማግኘት ከፈለግን ልባችንን ብትንሹም ቢሆን መክፈት ይኖርብናል ካሉ ቡኃል ለእለት ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

13/06/2017 09:42