Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

“ቅድስት ስላሤ የህብረት፣ የመልካምነት እና የውበት ነጸብራቅ”

ር. ሊ. ጳ.ፍራንቸስኮ በሰኔ 4/2009 ዓ.ም. በቅዱ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት። - AFP

13/06/2017 09:34

በሰኔ 4/2009 ዓ.ም. የቅድስት ስላሤ አመታዊ ክብረ በዓለ በመላው ክርስቲያኖች ዘንድ በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። በዚሁ እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ይህንን በዓል ለመክበር ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አስተንትኖ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በእለቱም ያደረጉት አስተንትኖ “የእግዚኣብሔር ህልውና ምስጢር” በሚል ጭብጥ ዙሪያ ያጠነጠነ እንደነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት  በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

 

በእለቱ በላቲን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር መሰረት በበሁለተኛነት በተነበበው እና ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው 2ኛው መልእክቱ 13:11-13 በተወሰደው “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚኣብሔር ፍቅር እና የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችሁም ጋር ይሁን” የሚለውን ጥቅስ በመጥቀስ አስተንትኖዋቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው ይህም ጥቅስ ጳዎሎስ በእግዚኣብሔር ፍቅር ላይ የነበረው የግል ተመክሮ ነጸብራቅ ነው ብለዋል።

ሐዋሪያው ጳውሎስ በወቅቱ ለነበሩ የክርስቲያን ማኅበረሰብ ምንም እንኳን ሰው በመሆናቸው የተነሳ ውስን ቢሆኑም “የቅድስት ስላሤ ህብረት፣ መልካምነት እና ውበት ነጸብራቅ” ይሆኑ ዘንድ አሳስቡዋቸው ነበር በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ይህ ሊተገበር የሚችለው እኛ ምሕረትን ማድረግ በሕይወታችን ስንለማመድ እና የእግዚኣብሔር ምሕረት ሲታከልበት ብቻ ነው ብለዋል።

ይህም የአይሁድ ሕዝብ ከባርነት በወጡበት ወቅት የነበራቸው ተመክሮ ነው በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አይሁዳዊያን የእግዚኣብሔርን ትዕዛዛት በጣሱበት ወቅት እግዚኣብሔር ለሙሴ በደመና ውስጥ በመገለጽ አይሁዳዊያን ጥሰውት የነበረውን ትዕዛዝ በድጋሚ ለማደስ ተግልጦ ነበር ካሉ ቡኃላ የራሱንም ስም ትክክለኛ ትጉም “ጌታ መሓሪ እና ታላቅ አምላክ ነው፣ ለቁጣ የዘገየ ምሕረቱ እና ታማኝነቱ የበዛ” በማለት ግልጾ ነበር ብለዋል።

ይህ የእግዚኣብሔር ስም ትርጓሜ “እግዚኣብሔር ከእኛ ሩቅ እናዳልሆነ እና ራሱን በራሱ ዝግ ያደረገ አለምሆኑን የሚያሳይ እንደ ሆነ ገልጸው ነገር ግን በተቃራኒው እራሱን ከሌሎች ጋር የሚያገናኝ ሕይወት፣ ለሁሉም ክፍት የሆነ፣ የሰዎችን እምነት ማጉደል በፍቅሩ የዋጄ” መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

በብሉይ ኪዳን የተገለጸው የእግዚኣብሔር ስም ትርጉዋሜ በቀጣይነትም በአዲስ ኪዳን ምልአት ማግኘቱን በመግለጽ አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም በኢየሱስ ቃላት እና የማዳን ታልእኮ ፍጻሜን እንዳገኘ ጨምረው ገልጸዋል። “ኢየሱስ የእግዚኣብሔርን የፊት ገጽታን በመግለጽ እግዚኣብሔር በሦስት አካላት የተዋቀረ አንድ አካል መሆኑን፣ እግዚኣብሔር ሙሉ እና ፍቅር መሆኑን፣ በእነዚህ ሦስት አካላት መካከል ያለው ግንኙነት የሚፈጥር፣ የሚያድን እና ሁሉንም የሚያነጻ፣ አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ይህም ዛሬ በተነበበልን የወንጌል ቃል ውስጥ የተጠቀሰው የኢየሱስ እና የኒኮዲሞስ ትይንት ጭብጥ ሐሳብ ነው በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምንም እንኳን ኒቆዲሞስ በወቅቱ በነበረው ማኅበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ስፍራ የሚሰጠው ሰው የነበረ ቢሆንም በሕይወቱ ውስጥ እግዚኣብሔርን ከመመኘት እን ከመፈለግ ግን ታክቶ አያውቅም ነበር ብለዋል።

ነገር ግን ከኢየሱስ ጋር ይነጋገር በነበረበት ወቅት እግዚኣብሔር በአንጻሩ እርሱን እየፈለገው እንደ ነበረ መረዳት ችሎ ነበር በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔር ይጠባበቀው እንደነበረ እና እንደ ሚወደውም መረዳት ችሎ ነበር ብለዋል። በእዚህ የወንጌል ክፍል ውስጥ “እግዚኣብሔር ዓለምን እጅግ ስለ ወደደ አንድ ልጁን ሰጠ፣ ስለዚህ በልጁ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት ይኖረዋል እንጂ አይጠፋም” የሚለውን የኢየሱስን በጣም አስፈላጊ የሆነ ቃል እናገኛለን ያሉት ቅዱስነታቸው ይህ የዘላለም ሕይወት “የማይለካውን እና ታላቅ የሆነውን ኢየሱስ በመስቀል ላይ እንዲሞት የፈቀደውን የእግዚኣብሔርን ፍቅር የሚገልጸ ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በአስተንትኖዋቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት “ወደ ቅድስት ስላሴ ሕብርት ውስጥ በጥልቀት መግባት እንችል ዘንድ፣ ይህንንም ሕይወታችንን በፍቅር በመኖርና በሕይወታችን መመስከር እንድንችል የህልውናችን አንዱ አካል አድርገን መኖርም እንድችል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያ እንድትረዳን መማጸን ያስፈልጋል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተንትኖ አጠናቀዋል።

 

13/06/2017 09:34