2017-06-12 15:52:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፥ እያንዳንዱ ሰው በዚህ በምንኖርበት ዓለም የራሱ የሆነ ሚና አለው


እ.ኤ.አ. በ2001 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው መጋቢት 13 ቀን በ 2013 ዓ.ም. ከመመረጣቸው በፊት ገና የብዌኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት እያሉ የግልና የመንግሥት በሚል ስያሜ ሳነጣጠሉ አለ ምንም የሃይማኖት ልዩነት የሁሉም ትምህርት ቤቶች አሳግርት እርሱም አውታረ መረባዊ ግኑኝነት እንዲኖራቸው በማድረግ ወጣቱ ትውልድ ለጋራ ጥቅም አገልግሎት እንዲታነጽና የእያንዳንዱ ሰው ልጅ እድገት የሁሉም እድገት የሁሉም እንድገት ደግሞ የእያንዳንዱ እድገት መሆን እንዳለበትና ሁሉም ተያይዞ ማንም በተገሎ ሕይወት መኖር ሳይጠቃ በመደጋገፍ አብሮ እንዲጓዝ ለማረግ አልመው ያቋቋሙት ብሔራዊ የነበረው ይኸው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡ በኋላም ጳጳሳዊ መብት ያለው ዓለም አቀፋዊ ማኅበር ለመሆን የበቃው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ማንም እንደ ጥራጊ የማይታይበት በከተሞቻንና በኅልውና ጥጋ ጥግ ተነጥሎ የሚኖር የኅብረሰብ አባል መኖር የለበትም፡ ማንም ገለልተኛና ባይተዋር የማይሆንበት ዕድገት የጨበጠ ማኅበረሰብ ሁሉንም አባላቱን ያካተተ ሁሉም ዜጋ እንደ ጥሪው ኣንዲሳተፍ የሚሰጡት ትምህርት ዓላማው በማስፋፋት ላይ የሚገኝ ሲሆን። እ.ኤ.አ. ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም.  የዚህ ጳጳሳዊ መብት ያለው ዓለም አቀፍ የአቢያተ ትምህርት የግኑኝነት መረብ ማኅበር በሮማ አዲስ የመጀመሪያው የሆነው ዋና መቀመጫው የሚገኝበት ቢሮ በይፋ ቅዱስነታቸው መርቀው ለመክፈት ባስደመጡት ቃለ ምዕዳን፥ በዓለማችን እየሰፋ በመሄድ ላይ ያለው አግላይ ባህል በመቃወምና በመኰነን ሁሉም ለሁሉም አንድም ለብቻው የማይተውበት አንዱ ስለ ሌላው የወንድማዊ ተጠያቂነትና ያሳቢነት መንፈስ እንዲሰማው የሚያደግ የአብሮነት ባህል እንዲስፋፋ ይኽ ጳጳሳዊ ማኅበር በሚሰጠው አገልግሎት ቀዳሚ ሚና ሊጭወት እንደሚገባው ማሳሰባቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጃንካርሎ ላ ቨላ አስታወቁ።

ይኽ የዛሬ 20 ዓመት በፊት በቡዌኖስ አይረስ አንድ በማለት የጀመረው የግኑኝነት ባህል ማስፋፋት ዓላምው በማድረግ አገልግሎት እየሰጠ ያለው ማኅበር ዛሬ ዓለም አቀፋዊ ተጨባጭነት ያለው ሆኖ ይኸው በሚገባ እያገለገለና በ 190 አገሮች የተስፋፋ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሙያ ማሰልጠኛ ማእከሎችና በተለያዩ ሃይማኖቶች ሥር የሚታቀፉትን፡ የመንግሥትና የግል በጠቅላላ 450 ሺሕ ትምህርት ቤቶች የሚያቅፍ ለመሆን መብቃቱና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይኸንን ማኅበር ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም. ጳጳሳዊ መብት ያለው ዓለም አቀፍ ማኅበር እንዲሆ መወሰናቸውና ይኸው በአገረ ቫቲካን በቅዱስ ካሊስቶ ሕንጻ ውስY ዋና ቢሮውን እ.ኤ.አ. ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በይፋ ለማስመረቅ እንደበቃም ያስታወሱት ልኡክ ጋዜጠኛ ላ ቨላ አያዘው  የዚህ ዓለም አቀፋዊ ተቋም መሥሪያ ቤት ለማስመረቅ በተካሄደው ስነ ሥርዓት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተለያዩ አገሮች ከሚገኙት የተቋሙ ቅንርጫፍ ሁሉ የድረ መልእክት ከደረሳቸው በኋላ በመቀጠል ባስደመጡት ቃለ ምዕዳን፥ እሳቸው ይኸንን ተቋም ለማቋቋም ያነቃቃቸው ሃሳብና ዓላማው መለስ ብለው በመቃኘት በተለይ ደግሞ አስተንፍሶ የሆኑዋቸውን እሴቶች በማብራራት፥

ነጣይነት ይቀር፥ ሌላውን የሚያገል ለብቻው የሚተው አግላይ ባህል እንቢ እንበል። የሚያሳትፍ ሌላውን የሚያዋህድ ባህል እናስፋፋ፡ ማንም ሰው አይ የሚባል አይደለም። ሁሉም ክብር አለው። ክብር ያለውና የሌለው የሚባል ሰው የለም ሁሉም ክቡር ነው። አንድ ትንሽ ጠጠር ቢሆንም የራሱ ጥቅምና አገልግሎት አለው። ስለዚህ ይኽ ዓለም አቀፍ ተቋም ተገላይነት እንዲወገድ ውህንደት በማነቃቃት የአብሮነት ባህል የሚያስፋፋ የሚል መሆኑ መቼም ቢሆን እንዳይዘነጋ አደራ እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ላ ቨላ አያይዘው፥

የዓለማዊነት ትስስር አሉታዊ ገጽታ፥ የእያንዳንዱ ጥልቅ መለያ በመሰረዝ ሁሉም አንድ ዓይነት መለያ እንዲያጠልቅ የሚያደርግ ዓለማዊነት ትስስር ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ዓለማዊነት ትስስር ኅብረአዊነት ሥር መሆን አለበት። ይኽ ደግሞ ግንዛቤን ያሰፋል እንጂ አያጠብም። እውነተኛው ዓለማዊ ትስስር ኅብረአዊነትን የሚያከብር ነው፡ ስለዚህ ኅብረአዊነትን የሚቀበልና የሚያስተናግድ ኅብረተሰብ ብቻ ነው ማደግ የሚችለው። እያንዳንዱ ሰው የገዛ እራሱ ሚና ለይቶ በማወቅ በኅብረተሰብ ውስጥ ተገቢ ስፍራውን በመቀዳጀት ለገዛ ርእሱ በጅቶ ለኅብረተሰብ የሚበጅ ለጋራ ጥቅም የሚያገለግል መሆን አለበት ካሉ በኋላ የተቋሙን ቅርንጫፎችን ላስተናገዱት አገሮች ሁሉ በዚህ አጋጣሚም አመስነው የተቋሙ አባላት እየሰጡት ላለው አገልግሎትም አመስግነው፥ አደራ ምንም ሳይንጠል ሳይገለል ለመኖር የሚያስችለው እድል እንዳይነፈገው ተግታችሁ አገልግሉ። ለትብብራችሁ አመስግናችኋለሁ በማለት የለገሱት ቃለ ምዕዳን ማጠቃለላቸው አስታውቋል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.