Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ወጣቶች

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ በጽናት ወደፊት መጓዝ

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ በጽናት ወደፊት መጓዝ - AFP

12/06/2017 15:49

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ሰርጆ ማታረላ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት በርእሰ ብሔር ሕንፃ ይፋዊ ጉብኝት ማካሄዳቸውና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከርእሰ ብሔር ማታረላ ጋር በመሆን ከኢጣሊያ በርዕደ መሬት ከተጠቃው ክልል በተወጣጡ 300 ሕፃናትና ወጣቶች አቀባበል እንዳደረጉላቸውም የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጓራሺ አስታውቋል።

የአቀባበሉ ሥነ ስርዓት መንግሥታዊ ብቻ ሳይሆን የሕፃናቱ እዛው መገኘት በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ግኑኝነት ከፍተኛ ቅርርብና ጥልቅ ወዳጅነት የተካነ መሆኑ ትልቅ የማረጋጫ አብነት ነው ያሉት ልኡክ ጋዜጠኛ ጓራሺ አያይዘው፥ ቅዱስ አባታችን በዚሁ ጉብኝታቸው በቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፕየትሮ ፓሮሊን በሮማ ሰበካ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ በኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ መንበር የፐሩጃ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካዲናል ጉዋልቲየሮ ባሰቲ ተሸኝተው በዚህ በኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ሕንፃ ባካሄዱት ጉብኝት እነዚያ ከኢጣሊያ በርዕርእደ መሬት ከተጠቃው ክልል የተወጣጡ ሕፃናት መገኘት በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ግንኙነቱ እጅግ ሰአዊነት የጎላበት እንደሆነም የሚያወሳ መሆኑ ገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ባስደመጡት ንግግር፥ ለ 300 ታዳጊ ወጣቶች እዛው ተገኝተው ላስደሙት ጥዑም መዝሙር አመስግነው፡ በማንኛውም የሕይወት ጉዞ በጽናት በርትታችሁ ተጓዙ ፡ እዎ በሕይወት ጉዞ እክሎች ከባድ ፈተናዎችና ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ፡ ብዙ ሰቃይ ደርሶባችኋል ሆኖም  ልክ የተራራማ ክልል ሰዎች፥ “ተራራን የመውጣት ጥበብ አለ መውደቅ ሳይሆን ከወደቁ በኋላ መነሳት ላይ ነው፡ ወድቆ በመነሳት ላይ ነው። ዘወትር መነሳት፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ” በማለት የመንፈስ ጽናታቸውን በማድነቅ ወጣቱ የተጋፈጡት የክልላቸው ርዕደ መሬት ባስከተለባቸው አበይት ችግሮች ምንም’ኳ ታሪካቸው ሰብአዊነታቸውን ሁሉ የነካ ቢሆንም ቅሉ በተካዥ ሕይወት ጫና ሥር ሳይቀሩ ወደ ፊት መጓዝ እንደሚገባ ለሁሉም ህያው ምስክር መሆናቸው ቅዱስነታቸው የገለጡ ሲሆን፡ ታዳጊ ወጣቶቹም “ወዳጅነት” የተሰየመው መዝሙር በማስደመጥ ለቅዱነታቸው ከርዕደ መሬት ከተጠቃው ክልል ከሚገኙ ወጣቶች የተላከላቸው ደብዳቤዎች ማስረከባቸውንም ጓራሺ ይጠቁማሉ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከርእሰ ብሔር ማታረላ ጋር ባካሄዱት ግንኙነት በፍረሰኞች አዳራሽ ባስደመጡት ንግግር፥ ደጋግመው ያሰመሩበት ሃሳብ ቢኖር፥ ሥራ የሰው ልጅ ክብር መሆኑና ሥራን ማእከል ያደረገ ፖለቲካ ለወጣቱ ትውልድ ተስፋ መስጠት ያለው አስፈላጊነት በስፋት ማብራራታቸውና የኢጣሊያ የኤኮኦሚ ሚኒ. ፒየሮ ካርሎ ፓዶኣን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ቅዱስነታቸው ያሰመሩበትን ሃሳብ አስደግፈው በእውነቱ ወጣት ትውልድ እያጋጠመው ያለው ሥራ አጥነት የተለያየ ምክንያት ያለው ችግር ነው ሆኖም መንግሥት ይኸንን ችግር ለመቅረፍ ወጣቱ ትውልድ በሥራ ዓለም የማሳተፍ ዕድል ከፍ ለማድረግ ወቅታዊው የሥራ ዓለም የሚጠይቀው ቅድመ ዝግጅት ወጣቱ ትውልድ ተክኖ ተገቢ ሥልጠና አግኝቶ ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ ያስፈጋል ካሉ በኋላ፡ ብቃት ያለው በሚገባ የተዘጋጀ ወጣትም ብዙ ነው ስለዚህ ለብቃት ማሠልጠን ብቻ ሳይሆን የዓለም ኤኮኖሚ የቤተ ክርስቲያን የሥነ ማሕበራዊ ትምህርት እንደሚያመለክተው በትርፍ ላይ ያጠነጠነ ኤኮኖሚ ሳይሆን ፍትሕ ላይ የጸና የኤኮኖሚ ሂደት ማረጋገጥ ወሳኝ ነው ሲሉ በመቀጠልም የኢጣሊያ የጤና ጥበቃ ሚኒ. በአትሪቸ ሎረንዚኒ በበኵላቸውም፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያስደመጡት ንግግር የላቀው እሴት የተኖረበትና አንድን ሕዝብ አንድ ሆኖ በመኖር ጥሪው ከሚያጋጥም ችግር ማዶ ውህደቱን አቅቦ ለመኖር እንዲችል የሚደግፍ መንግሥት ያስፈልጋል። መንግሥት ብቻ ሳይሆን በዚህ ድጋፍ በጠቅላላ የመንግሥት ተቋሞች መንግሥግታዊ ያልሆኑት ተቋሞች ጭምር አቢይ ሚና ሊኖራቸው ይገባል ካሉ በኋላ፡ የቅዱነታቸው መልእኽት የላቀ ፖለቲካ መቃን ያደረገ የአንድ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ራእይ የሚያንጸባርቅ በጠቅላላ ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን የነካ ነው ብሏል።

12/06/2017 15:49