Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

“በጣም ከባድ በሆነ ሐዘን እና ትካዜ ውስጥ በምንገባበት ወቅቶች ሁሉ ጌታ ትዕግስት ማድረግ እንድንችል ይረዳን ዘንድ እንጸልይ።

ቅዱስነታቸው በሰኔ 2/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት።

09/06/2017 14:57

“በጣም ከባድ ሐዘን እና ትካዜ ውስጥ በምንገባበት፣ ሰዎች በሚሰድቡን እና በሚያንጓጥጡን ወቅቶች ሁሉ በእብሪተኛ ስሜት ውስጥ ሳንገባ የጸሎትን መንገድ በመያዝ እግዚኣብሔር ትዕግስቱን እና ተስፋውን እንዲሰጠን መለመን ይገባናል”። ይህንን ቀደ ሲል የሰማችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በሰኔ 2/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ካሰሙት ስብከት የተወሰደ ነው።

“የመኳኳያ ግብዕቶችን ተጠቅሞ በሚገኘው ውበት” በፍጹም መታለል የለብንም በማለት ስብከታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው በማንኛውም መንገድ እብሪትን አስወግደን  “የእግዚኣብሔር ደስታ” እንዲገባ ልባችንን መክፈት እግዚኣብሔር ስለሰጠን ደኅንንነት ልናመሰግነው ይገባል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በዛሬው ቀን በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት የመስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት በእለቱ በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በቀዳሚነት በተነበበው እና ከመጽሐፈ ጦቢት በተወሰደው ምንባብ ላይ ትኩረቱን ያደርገ ስብከት እንደ ሆነም ለመረዳት ተችሉዋል።

“ጦቢያ በጣም የተንከራተተ ሰው ነበር፣ ስደትም ደርሶበት ነበር፣ በሚስቱም ሳይቀር ተስድቦ ነበር” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን የጦቢያ ሚስት ክፉ የምትባል ሴት አለምሆኑዋን ገልጸው “ነገር ግን እርሱ ዐይነ ስውር በመሆኑ የተነሳ የቤታቸውን ሙሉ ተግባር በማከናወን ቤቱን የምታስተዳድር እርሱ ነበረች” ካሉ ቡኃላ ሳራም ራሷ ምንም እንኳን የሚገባትን ያህል ሥራ እያከናወንች ብትገኝም ከስድብ አላመለጠችም፣ ሁሉም ነገር ጨለማ ሆኖባቸው ነበር፣ በዚህም ምክንያት መሞት መርጣ እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

“እኛ ሁላችን በጣም መጥፎ የሚባሉ ወቅቶችን በሕይወታችን አስልፈናል፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በጣም ከበድ የሚባሉ ወቅቶች በሕይወታችን ውስጥ ተከስተው አልፈዋል ነገር ግን ሕይወታችን ጨለማ እና ሐዘን ውስጥ  በምትገባበት ወቅቶች ሁሉ ምን እንደ ሚከሰት እንውቃለን” በማለት ስብከታቸውን የቅጠሉት ቅዱስነታቸው የጦቢያ ሚስት የነበረችው ሳራ ሕይወቱዋ መከራ ውስጥ በገባበት ወቅት የራሷን ሕይወት ለማጥፋት አስባ ነበር ነገር ግን “እኔ ራሴን ካተፋው ቤተሰቦቼ በጣም ይጎዳሉ” ብላ አስባ እንደ ነበረ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው በመጨርሻም አንድ ጊዜ ቆም ብላ ጸሎት ማድረግ መጀመሩዋን ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

እኛም በሕይወታችን ዘመን ክፉ የሚባሉ ነገሮች በሚገጥሙን ውቅቶች ሁሉ ልንከተለው የሚገባው ባሕሪ ይህ ሊሆን ይገባል ያሉት ቅዱስነታቸው የምንድንበት እና ከጭንቀታችን መላቀቅ የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ጸሎት ነው ብለዋል።

በመቀጠልም መከራዎች ውስጥ በምንገባባቸው ወቅቶች ሁሉ ከፍተኛ የሆነ ትዕግስት ያስፈልገናል ያሉት ቅዱስነታቸው ጦቢያ እና ሚስቱ ሳራ ምንም እንኳን ከፍተኝ የሆነ ጭንቀት እና ሐዘን ውስጥ የነበሩ ሰዎች ቢሆንም ቅሉ ታጋሾች ግን ነበሩ ያሉት ቅዱስነታቸው እነዚህ የመከራ እና የሐዘን ወቅቶች ያልፉ ዘንድ  በእግዚኣብሔር ላይ ተስፋ በማድረግ ይገባል ብለዋል።

መቼም ጊዜ ቢሆን ይነስም ይብዛም፣ ሕይወታችን ጨለማ የሚባሉ ወቅቶች ውስጥ በሚገባበት ወቅት መጸለይ፣ መታገስ እና ተስፋ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ቅዱስነታቸው  እነዚህን ነገሮች መቼም ቢሆን መርሳት የለብንም ብለዋል።

በጦቢያ እና በሳራ ሕይወት ውስጥ ጥሩ የሚባሉ ወቅቶችም ተከስተው እንደ ነበረ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው “ከእዚህ ሁሉ ሐዘን እና መከራዎች ቡኃላ ጌታ ወደ እነርሱ በመቅረብ ሲያድናቸው እናያለን ብለዋል”። በሕይወት ውስጥ ጥሩ የሚባሉ እና እውነተኛ ነገሮች ይከሰታሉ” ያሉት ቅዱስነታቸው እንደ እዚህ ያለ ሁኔታ ውስጥ ሕይወታችን በሚሆንበት ወቅቶች ሁሉ እግዚኣብሔርን እያመሰገንን ይበልጡኑ አመስጋኞች እንድንሆን ልባችንን ያስፈው ዘንድ ልንለምነው እና ልናመሰግነው ይገባል ብለዋል።

በዚህ በመገባደ ላይ በሚገኘው ሳምንት ይህንን የጦቢያን መጽሐፍ በምናነብበት ወቅት መከራ እና ሐዘን ውስጥ በምንገባባቸው ወቅቶች ሁሉ ትክክለኛውን ውሳኔ ማድረግ እንድንችል ይረዳን ዘንድ እና ክፉን ከደጉ በመለየት ወደ ፊት መልካም ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ በሚል ተስፋ ተሞልተን መጓዝ የምንችልበትን ጸጋ ይሰጠን ዘንድ ልንለምነው ይገባል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

09/06/2017 14:57