Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

በጳውሎስ ሕይወት ውስጥ ጎልተው ታይተው የነበሩት ስብከት፣ ስደት እና ጸሎት ለዛሬ ክርስትያኖች አብነት ሊሆኑ ይገባል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በግንቦት 24/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት።

02/06/2017 15:14

በቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ሕይወት ውስጥ ጎልተው ታይተው የነበሩት ስብከት፣ ስደት እና ጸሎት በዛሬው ዘመን ለሚገኙ ክርስትያኖች አብነት ሊሆኑ ይገባል። ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 24/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ካሰሙት ስብከት የተወሰደ ነው።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት በላቲን ስርዐተ-አምልኮ አቆጣጠር በእለቱ በቀዳሚነት በተነበበው እና ከሐዋሪያት ሥራ 22 ላይ የተጠቀሰው የጳውሎስ በአይሁድ ሸንጎ ፊት መቅረቡን በምያወሳው ታሪክ ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተመርኩዘው ሐዋሪያው ጳውሎስ ቆራጥ የሆነ እርምጃ የሚወስድ ሰው ነበር ካሉ ቡኃላ የእርሱን ሕይወት መገምገም በጣም ከባድ ነው፣ ምክንያቱ እርሱ ብዙን ጊዜ በጉዞ ላይ የነበረ እና አንድ አንድ ጊዜ ብቻ ተቀምጦ የሚጽፍ ሰው በመሆኑ የተነሳ ነው ብለዋል።

ሐዋሪያው ጳውሎስ ከፍተኛ የሆነ የመስበክ ፍላጎት ስለነበረው ሁል ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለዓለም በማብሰር ሥራ ላይ ተጠምዶ ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም ከፍተኛ የሆን የመስበክ ፍላጎቱ በሐዋሪያዊ ሕይወቱ ውስጥ ጎልቶ ወደ ታየው እና በሐይማኖት መሪዎች አነሳሽነት ወደ ደረሰበት ከፍተኛ ስደት ውስጥ ይከተዋል ብለዋል። ነገር ግን አሉ ቅዱስነታቸው ነገር ግን ሐዋሪያው ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ በመመራት በሰዱቃዊያን እና በፈሪሳዊያን መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ልዩነት መመልከት ችሎ እንደ ነበረ የገልጹት ቅዱስነታቸው ገሚሱ ከሙታን መነሳት እንዳለ የሚያምኑ፣ ገሚሱ ደግሞ ይህንን የሚቃወሙ ፈሪሳዊያን እና ሰዱቃዊያን ነበሩ እነዚህም በወቅቱ ታይተው የነበሩ ልዩነቶች እንደ ነበሩም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ሐዋሪያው ጳውሎስ በአይሁድ ሸንጎ ፊት በቀረበበር ወቅት “ሕዝቡ፣ ከፊሎቹ ሰዱቃውያን፣ ከፊሎቹ ፈሪሳውያን መሆናቸውን ስላወቀ፣ “ወንድሞቼ ሆይ፤ እኔ ከፈሪሳዊ የተወለድሁ ፈሪሳዊ ነኝ፣ ለፍርድ የቀረብሁትም የሙታንን ትንሣኤ ተስፋ በማድረጌ ነው” ሲል በሸንጎው ፊት ጮኸ ተናግሮ እንደ ነበረ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንንም በተናገረ ጊዜ፣ በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን መካከል ጠብ ተነሣ፤ ሸንጎውም ለሁለት ተከፈለ ብለዋል። ሰዱቃውያን የሙታን ትንሣኤ የለም፤ መላእክትም መናፍስትም የሉም የሚሉ ሲሆኑ፣ ፈሪሳውያን ግን በእነዚህ ሁሉ መኖር የሚያምኑ ነበሩ፣ እነዚህ የሸንጎ አባላት የሆኑ የሕግ አስከባሪዎች በእመነታቸው የተነሳ ክፍፍልን ፈጥረው ነበር ካሉ ቡኃላ በዚህም ምክንያት እምነታቸውን እስከ ማጣት ደርሰው ነበር ምክንያቱም ሕግጋቶቻቸውን እና ሀይማኖታዊ አስተምህሮዋቸ ሁሉ ምናባዊ መሰረት የነበረው በመሆኑ የተነሳ ነው በማለት ቅዱስነታቸው አስረድተዋል።

ጸሎት ሦስተኛው የሐዋሪያው ጳውሎስ ሕይወት መገለጫ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ከጌታ ጋር የነበረው ጥብቅ ግልኙነት ያሳያል ብለዋል። በጣም አድካሚ በሆነው የወንጌል ስብከት ውስጥ በመሳተፍ እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ወንጌልን የሰበከ እና በዚህም ሰበብ ከፍተኛ የሆነ መከራና ስደት ገጥሞት የነበረ ቢሆንም እንኳን ጳውሎስ ወደ ደማስቆ በመሄድ ላይ በነበረበት ወቅት ከተገለጠለት ከሙታን ከተነሳው ጌታ ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት ነበረው ብለዋል።

ይህ ሁሉ የሐዋርያው ጳውሎስ ብርታት የመነጨው የጸሎት ሰው በመሆኑ የተነሳ እና በቀጣይነትም በጸሎት ከኢየሱስ ጋር የተገናኘ እና  ለመገናኘት የሚሻ ሰው በመሆኑ የተነሳ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እኛም በሐዋሪያው ጳውሎስ ሕይወት ውስጥ የነበሩ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ፣ ስደትን መቋቋም እና በጸሎት ከኢየሱስ ጋር መገናኘት የሚሉት ጸጋዎች በሕይወታችን ውስጥ እንዲኖሩ ምኞቴ እና ጸሎቴም ነው ካሉ ቡኃል ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

02/06/2017 15:14