2017-05-31 17:12:00

የመላ ላቲን አመሪካና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ኅብረት ዝክረ አስረኛው ዓመት የአፓረሲዳ ጉባኤ


በብራዚል አፓረሲዳ ሰበካ ተካሂዶ የነበረው የመላ ላቲን አመሪካና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ኅብረት ይፋዊ ጠቅላይ ጉባኤ በዚያኑ ወቅት የቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ ካርዲናል ኾርገ ማሪዮ ቦርጎሊያ እ.ኤ.አ. ከ 2013 ዓ.ም. መጋቢት 13 ቀን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ  ሆነው ከመመረጣቸው በፊት የተሳተፉበት ተካሂዶ የነበረው ጠቅላይ ይፋዊ ጉብኤ ያወጣው የፍጻሜ ሰነድ የቅዱስነታቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው ሕያው ምንጭ ነው ሊባል ይችላል። ይኸንን ጉዳይ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት በአፓረሲዳ ጉባኤ የተሳተፉት የላቲን አመሪካ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ድርገት ምክትል ሊቀ መንበር ፕሮፈሰር ጉዝማን ካሪኵየር አስታውቋል።

ያ የአፓረሲዳ ጉባኤ በእውነቱ ጥልቅ ወንድማዊነትና ጉባእያዊነት የተገለጸበት ሁነት ነበር፡  መንፈስ ቅዱስ የተባረከ ይሁን በመላ ላቲን አመሪካና ካሪቢያን የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን  ውጥረቶችን ዝንፈቶችን በማሸነፍ ጥልቅ ሱታፊያዊነት በማረጋገጥ አንዲት ቤተ ክርስቲያን መሆንዋ ልዩና ጥልቅ ግንዛቤ የጎላበትም ነበር፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ጉባእያዊነት እጅግ የጎላበት ነበር ስለዚሁ ጉዳይም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከካቶሊካዊ ሥልጣኔ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎችን ለይቶ መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠውን ጸጋ መቀበል በማለት ያሰመሩበት ሃሳብ የጎላበት ነበር

ካሉ በኋላ አያይዘውም የአፓረሲዳ ጉባኤም የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑ ይኸው እግዚአብሔር አሳቢነቱ ብፁዕ ካርዲናል በርጎሊያ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲሆኑ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን መመረጣቸው አቢይ ተጨባጭ ምስክር ነው ብሏል።

በዚያ በአፓረሲዳ ጉባኤ መዝጊያ በመሳተፍ መሥዋዕተ ቅዳሴ በተጋባእያን ብፁዓን ጳጳሳትና ብፁዓን ካርዲናሎች ታጅበው ባሳረጉት በዚያኑ ወቅት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በነበሩት በቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛና በዚያኑ ወቅት ብፁዕ ካርዲናል ቦርጎሊዮ መካከል የተመሰከረው ጥልቅ ውኅህደትና ስምምነት ያስተዋወቀም እንደነበርም አብራርተው በነዲክቶስ 16ኛ መስዋዕተ ቅዳሴውን አሳርገው አስደምጠዉት በነበረው ስብከት፥

የአፓረሲዳ ጉባኤ የተወያየባቸውን ነጥቦች ጠቃቅሰው በላቲን አመሪካ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተክለ ሰብነት ያስተዋወቀ ጉባኤ በማለት ገልጠዉታል። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወንጌላዊ ሐሴት በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ሐዋርያው ምዕዳን ያንን የአፓረሲዳ ጉባኤ የፍጻሜ ሰነድና በብፁዕ ጳውሎስ ስድተኛ ብስራተ ወንጌል በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን በጥልቀት የሚያጣምር ነው፡ ይኽ ሲባል ደግሞ የራሱ የሆነ አዲስነት የለውም ማለት ሳይሆን ኵላዊነት ባህርይ ያጎላና ከክርስቶስ ጋር መገናኘት የሐሴት ምንጭ መሆኑ አስረግጦ የሚመሰክር ነው

በማለት አብራርተዋል።

የአፓረሲዳ ጉባኤ ሕዝበ እግዚአብሔር የክርስቶስ ደቀ መዝሙርና ልኡካነ ወንጌል መሆኑ የሚገልጥ የላቲን አመሪካና ካሪቢያን ተጨባጭ ሁኔታ ቀርቦ በእምነት ክርስትናና በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ሥር የሚያነብ ነው፡ ይኽ ሃሳብ ደግሞ የአፓረሲዳ ጉባኤ ያወጣው የፍጻሜ ሰነድ ተንታኝ ቁልፍ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.