2017-05-31 17:17:00

ተስፋ ወደ ፊት እንድንጓዝ ያደርገናል


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች የጠቅላላ አስተምህሮ እንደ ምያደርጉ ይታወቃል። የዚህ መረዕ ግብር አንዱ አካል በሆነው በግንቦት 23/2009 ዓ.ም. ያሰትላለፉት አስተምህሮ ከዚህ ቀደም የክርስትያን ተስፋ በሚል አርእስ ጀምረውት የነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻፈው መልእክቱ በምዕራፍ 15፡13-14 ላይ ያተኮረ እንደ ነበረም ተገልጹዋል።

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያስተላለፉት የጠቅላላ አስተምህሮን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛችዋለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

 መንፈስ ቅዱስ የሚወርድበትን የጴንጤቆስጤ በዓል እየተጠባበቅን ባለንበት በአሁኑ ወቅት የክርስትያን ተስፋ በሚል አርዕስት ጀምረነው የነበረው አስተምህሮ በዛሬው እለት በመንፈስ ቅዱስ እና አዳኛ በሆነው ተግባሩ ላይ ያተኮረ ይሆናል። ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች የጻፈውን መልእክቱንተስፋችን በመንፈስ ቅዱስ ኅይል እያደገ እንዲሄድ፣ የተስፋችን አምላክ በእርሱ በመታመናችሁ ደስታንና ሰላምን በሙላት ይስጣችሁ”(1513) በሚል ጸሎት ደምድሞታል። መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንችል ዘንድ ተስፋ ማድረግ እንደ መልእቅ ሆኖ ያገለግላል፣ በሕይወት ውስጥ ማዕበል በምያጋጥምበት ወቅት ሁሉ ይህንን ማዕበል በመቋቋም ደኅንነታችንን ወደ ሚረጋገጥበት ወደ ዘላለም ሕይወት በቀጣይነት መቅዘፍ እንድንችል ያረዳናል። የእግዚኣብሔር መንፈስ ከእኛ መንፈስ ጋር ሆኖ የእግዚኣብሔር ልጆች መሆናችንን ይመሰክራል። በዚህ ተስፋ በመሞላት ካርዲናል ኒውማን እንደ ሚሉትበጳራቅሊጦስ አማሳል የሚመጣው አጽናኝ ተሟጋቻችን፣ ረዳታችን እና መጽናናትን ለሌሎች የምያመጣነው። መንፈስ ቅዱስ ነው ለፍጥረታት ሁሉ ተስፋን የሚያጎናጽፈው፣ በተጨማሪም እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ እና የምንኖርበት ዓለማችንን እንድናከብር የምያስተምረን መንፈስ ቅዱስ ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም እና ሐዋሪያት  በአንድ ቤት ውስጥ ተሰብስበው በመጸለይ ላይ በነበሩበት ወቅት እንዳገኛቸው ሁሉ እኛንም በዚሁ በሚመጣው በጴራቅሊቶስ ቀን ተሰብስ በመጸልይ ላይ እንዳለን እንዲያገኘን እመኛለሁኝ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.