Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ቤተ ክርስትያን \ ቤተ ክርስትያን በአለም

ለበዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ ካቶሊካዊ የተሃድሶ በመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ጉባኤ በሮማ ማሲሞ አደባባይ

ለበዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ ካቶሊካዊ የተሃድሶ በመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ጉባኤ በሮማ ማሲሞ አደባባይ - RV

31/05/2017 17:03

ካቶሊካዊ የመፈስ ቅዱስ ተሃድሶ እንቅስቃሴ 50ኛው ዓመተ ምሥረታ ምክንያት ዓለም አቀፍ ካቶሊካዊ የመንፈስ ቅዱስ ተሃድሶ እንቅስቃሴና ካቶሊካዊ ወንድማማችነት ያሰናዳው እ.ኤ.አ. ከግንቦት 31 ቀን እስከ ሰነ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. የተለያዩ ሮማ በሚገኙት አበይት ባዚሊካዎች የተለያዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮች እንደሚከናወንና በበዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተገኝተው ቃለ ምዕዳን የሚለግሱበት ከሰላሳ ሺሕ በላይ ተሳታፊ ይገኛል ተብሎ ከወዲሁ ግምት የተሰጠበት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መልካም ፈቃድ ምክንያትም የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ያሳተፈ የውህደት ጸሎት እርሱም የተለያዩ የጴንጠቆስጣውያን ወንጌላውያን አቢያተ ክርስቲያንና የሌሎች ሃይማኖቶች የበላይ መንፈሳውያን መሪዎች የካቶሊካዊ በመንፈስ ቅዱስ ተሓድሶ እንቅስቃሴ መሪዎች በዋናው የጉባኤው የመሃል መድረክ የሚገኙበት የጋራ ጸሎት እንደሚያርግ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸቺሊያ ሰፒያ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

ይኽ ከ 130 አገሮች የተወጣጡ 600 ካህናት እንዲሁም ወደ 50 የሚገመቱ ብፁዓን ጳጳሳትና ብፁዓን ካርዲናሎች፡ ምእመና በጠቅላላ ከሳላሳ ሺሕ በላይ ተጋባእያን የሚያሳትፍ ይሆናል ተብሎ በሚነገርለት ለበዓለም ጴንጠቆስጠ ዋዜማ የተሰናዳው መንፈሳዊ መርሐ ግብር ካቶሊካዊ የተሃድሶ በመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ዝክረ 50ኛው ዓመተ ምሥረታው ጭምር የሚያካትት ሲሆን፡ ይኽ ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ እ.ኤ.አ. በ1967 ዓ.ም. የካቲት ወር ላይ በፒትስቡርግ ጥቂት የመንበረ ጥበብ ተማሪዎች በቤተ ክርስቲያንና በዓለም ላይ መንፈስ ቅዱስ እንዲወርድ ያለው አስፈላጊነት በመገንዘብ በጋራ ባካሄዱት አብሮ ለመንፈስ ቅዱስ የመጸለይ የልመና ጸሎት ያነቃቃው መሆኑ ያስታወሱት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሰፒያ አያይዘው፥ በዚህ በአሁኑ ወቅት የእሴቶች ቀውስና መጻረር በስፋት በሚታይበ ዓለም ይኽ የካቶሊክ እንቅስቃሴ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ግፊት መሠረት ጸጋው እጅግ በዝቶ ብዙ ጥሪ የሚወለድበት በበለጠ ወንጌል የሚያስፋፋ የድኾች የተናቁት እሩቅ ያሉት የተገለሉት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው ወንጌል መሆናቸው በማበሰር ላይ እንደሚገኝ የተሃድሶ በመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ዓለም አቀፍ ወንድማማችነት ሊቀ መንበር ሚከለ ሞርጋን ማሳወቃቸው ገልጠዋል።

ሞርጋን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ አንድ አዲስ ነገር ሲነቃቃ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተገቢ ስፍራው ማግኘት ይኖርበታል። ይክ እንቅስቃሴ ተገቢው ሥፍራ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊያገኝ መቻሉንም ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ይመስገን፡ እንቅስቃሴው በገዛ እራሱ ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በኋላ በመጡት ሁነቶች ውስጥ የተቀበለው የተሃድሶ ጸጋ በሚገባ ሊያገናኘውና ሊተገብረው  በሚገባ ሊያስተውለውና ሊገነዘበው እንደሚያስፈልግም በማመን ለቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርትና ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ታዛዥ በመሆን ህዳሴው ለማስፋፋት ችለዋል። ይኽ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው። እንቅስቃሴው የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ መሆን ማለት ነው፡ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለሚነቃቃው የቤተ ክርስቲያን የኅዳሴ ሂደቶችን በመደገፍ በመታዘዝ ያገለግላል፡ የጴንጠቆስጠ ባህል ያስፋፋል ምክንያቱን እያንዳንዱን ነገርና ጉዳይ ትልቅ የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ነውና ብሏል።

በዚህ በሮማ ማሲሞ አደባባይ በሚካሄደው የበዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ ስነ ሥርዓት በመቀጠልም ለነገታው በበዓለም ጰራቅሊጦስ ቅዱስ አባታችን እኩለ ቀን በሚያሳርጉት ጸሎተ ንግስተ ሰማይ እንደሚሳተፉ ገልጠዋል። በዚህ አጋጣሚም እነዚህ በጰራቅሊጦስ በዓለ ዋዜማ የሚሳተፉት እ.ኤ.አ. ግንቦት 31 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በለገሱት የዕለተ ረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መሳተፋቸው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የኢጣሊያ ብሔራዊ የተሃድሶ በመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር ሳልቫቶረ ማርቲነዝ አያይዘው፡ በዋዜማው ስነ ሥርዓት የቅዱስ አባታችን የቅርብ ጓደኛ መጋቤ ጆቫኒ ትራኤቲኖ የፕሮተስታንት አቢያተ ክርስቲያን መጋቢያን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የበላይ መንፍሳዊ መሪዎች እንደሚሳተፉ አረጋግጠው፥ በበዓለ ዋዜማው ስነ ሥርዓት ሁሉም አቢያተ ክርስቲያንና የተለያዩ ሃይማኖት የበላይ መንፈሳውያን መሪዎች በማሳተፍ በማሲሞ አደባባይ እንዲካሄድ የሚለው ሃሳብ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የመነጨ ነው፡ እንዲሁም ተያይዞ ካቶሊካዊ የተሃድሶ በመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ዝክረ 50ኛው ዓመት ይከበራል ሆኖም የእንቅስቃሴው በዓል ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ ነው የሚከበረው ይኽ የአንድነት የውህደት የዕርቅ የሐሴትና የዕርቅ ምክንያት የሆነውን መንፈስ ቅዱስ የሚከበርበት ዕለት መሆኑ አብራርተዋል።

አስፍሆተ ወንጌል የሚመራው መንፍስ ቅዱስ ነው። የመንፈስ ቅዱስ ዋና ተወናያንነት ለአግሮሞትና ለአድናቆት ምክንያት ነው። ስለዚህ የካቶሊካዊ ተሃድሶ በመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ኃላፊነት ምንኛ አቢይና ጥልቅ መሆኑ ከዚህ ለመረዳቱ አያዳግትም በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።

31/05/2017 17:03