Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ሳይንስና ትምህርት

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የተፈጥሮ አደጋ ቀድሞ መከላከል ርእስ ዙሪያ በሚካሄደው ጉባኤ ምክንያት ለመክሲኮ ርእሰ ብሔር መልእክት አስተላለፉ

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የተፈጥሮ አደጋ ቀድሞ መከላከል ርእስ ዙሪያ በሚካሄደው ጉባኤ ምክንያት ለመክሲኮ ርእሰ ብሔር መልእክት አስተላለፉ - REUTERS

26/05/2017 17:01

የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን የጋራ ቤታችን በሆነው ምድረ ዓለም ላይ ለሚከሰቱት የተፈጥሮ አደጋ ጠንቋሽ ናቸው የሚባሉትን ሰው ሠራሽ ምክንያቶች ሁሉ እንዲቀንስ ለማረግና ብሎም ጨርሶ ለማጥፋት በሚል መሠረታዊ ዓላማ  ላይ ተንተንርሶ በሚሰጡት አገልግሎቶች ሁሉ የቅድስት መንበር ዘርፈ ብዙ ተባባሪነቷን የሚያረጋግጥ መልእክት ለዚያች  የተፈጥሮ አደጋ ክስተቶችን እንዲጎድል ለማረግ የሚያግዝ ሥርዓተ ክወና 2017 ዓ.ም. በሚል ርእሰ ጉዳይ የመክሲኮ መንግሥት ዓለም አቀፍ የንብረተ ዓየር ስነ ትንበያ ድርጅትና የተባበሩት መንግሥታት የተፈጥሮ አደጋ ክስተት ቅነሳ ተከታታይ ቢሮ በጋራ አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ ወዳለው እ.ኤ.አ. ግንቦት 26 ቀን 2017 የተጠናቀቀው ዓለም አቀፍ ጉባኤ አስተናጋጅ ለሆነቸው ለአገረ መክሲኮ ርእሰ ብሒር ኤንሪከ ፐኛ ኔቶ ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታውቋል።

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ባስተላለፉት መልእክት ለተፈጥሮ አደጋ ጠነቅ ናቸው የሚባሉትን ተግባሮች እንዲጎድል በማድረጉ ሂደት በተለያዩ ክልሎች የሚገኙት ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል የሚያሳትፍ ቀድሞ መጠንቀቅና ቀድሞ መከላከል ዙሪያ የሕንጸት መርሐ ግብር አስፈላጊ ነው። መሠረተ ሐሳቡም ለተፈጥሮ አደጋ መከሰት ጠንቅ የሆኑትን ተግባሮች ለማጉደል በጋራ ጥቅም ላይ የጸና ወንድማማችነት ያለው አስፈላጊነት የሚጠቁም ነው።

በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ስም ለዚህ  በመክሲኮ በካንኩ ከተማ እየተካሄደ ወዳለው ዓለም አቅፍ ዓውደ ጉባኤ ተፈጥሮን በመንከባከቡ ሂደትና የተፈጥሮ አደጋ ክስተት ለማጉደል በሚደረገው ጥርት የቅድስት መንበር ሙሉ ድጋፍና ትብብር አረጋግጣለሁ ማለታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አያይዘው፥

በቀድሞ የመከላከልና ቀድሞ የመጠንቀቁ ሂደት ከሁሉም በፊት ቀድመው የተፈጥሮ አደጋ ሊከሰት መሆኑ የሚያሳውቁ ክህለቶችና ተገቢ መሣሪያዎች አሉ። አነዚህ መሣሪያዎችም በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት በሰው ሕይወት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ትልቅ አደጋ ዝቅ ለማድረግ አጋዥ ናቸው። በመሆኑም እነዚያ በሥነ ምርምር ተደግፈው ስለ ተፈጥሮ አደጋ ለመከሰት ቀድመው የማስጠንቀቂያ ነጋሪ የሆኑት ቢሮዎች በሚገባ አገልሎት መስጠት እንዲችሉ ሙሉ ትብብርና ድጋፍ ሊያገኙ ይገባል። ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩም በክልላዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለ የተፈጥሮ አደጋና የተፈጥሮ አደጋ ክስተት ቀድሞ ለመከላከል ላይ ያተኮረ ሕንጸ ማቅረብ እጅግ አስፈላጊ ነው እንዳሉም ያመለክታሉ።

የአካባቢ ሕዝቦች በተለይ ደግሞ ድኻው የኅብረተሰብ ክልፍ ማለትም ገዛ እራሳቸው የመከላከል ብቃቱም ሆነ አቅሙም የሌላቸውን በሕንጸት መርሐ ግብር በሚገባ ተሳታፊ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ሕንጸቱ ሰብአዊና መንፈሳዊ ጉዳይ ያካተተ መሆን አለበት። ሌላው በተለያዩ አካባቢዎች የሚከስተው የተፈጥሮ አደጋ ጥሎት የሚያልፈው የሥነ ልቦና ጫና እንዲቀረፍ ያስችላል ተብሎ የሚቀርበው ድጋፍና ትብብር ለማቅረብ ያንድ ሕዝብ ባህልና ሃይማኖት ቀድሞ ማወቅና መገንዘብ አስፈላጊ ነው እንዳሉ ዲኒኒ ይጠቁማሉ።

ሆኖም ብፁዕነታቸው እነዚህ ለቀድሞ መጠንቀቅ ሂደት መሠረተ ሃሳብ ናቸው በማለት ለዘረዘሩዋቸው ነጥቦች እግብር ላይ ለማዋል ያስተሳሰብና የሕይወት ስልት አጢኖ ማደስ ያለው አስፈላጊነት ገልጠው። የእደ ጥበብ ምንጣቄ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ የመጻኢ እድል ግምት መሰጠት ለመላ ሰው ልጅ የጋራው ጥቅም ማተኰር ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚያ ‘ይሴባህ’ በሚል ርእስ ሥር በደረሱት የጋራ ቤታችን ላይ ባማከለው ዓዋዲ መእክታቸው ዘንድ የሚከሰቱ አደጋዎች ተፈጥሮአውያን ክስተት ብቻ ሳይሆን ያንን ከማኅበራዊ ጉዳይ የሚመነጩ እንዳሉም ያመለክታሉ። ይክ የመክሲኮው  የ 2017 ዓ.ም. ሥርዓተ ክወና የዚያ የ 2015 ዓ.ም.  የፓሪስ ጉባኤ የወጠነው ተግባራዊ መርሓ ግብር ማለትም እ.ኤ.አ. ከ 2015 ዓ.ም. እስከ 2030 ዓ.ም. ባለው የዓመታት ገደብ ውስጥ የተፈጥሮ አደጋዎች  እንዲጎድል ለማድረግ ገቢራዊ መሆን ይገባቸዋል በማለት ያስቀመጣቸው ሦስት ነጥቦች በማስታወስ፡ ሰብአዊ ተግባርና እንቅስቃሴ ከዚያ የተፈጥሮ አደጋ ክስተት ማጉደል ያስልቻል ከሚባለው ተግባር ጋር ጥምረት እንዲኖረው ማድረግ የሚለው እቅድ የተሟላ ሰብአዊ እድገት ከሚለው ሃሳብ ጋር መሟላት ይኖርበታል ስለዚህ ይኽ አንዱ ኣብይ ተግዳሮት ነው። ድኽነት ማኅበራዊ አግላይነትን መዋጋት ከሚከሰቱት የተፍጥሮ የአካባቢ አየር ለውጥ ጋር ሊጋጠም የሚችል ስልት ማሻሻል ማላዘብና በሥራ ላይ ማዋል ያለው አስፈላጊነት አብራርተው ያስተላለፉት መልእክት ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አስታወቁ።

26/05/2017 17:01