2017-05-24 16:28:00

ኢየሱስ የተስፋችን ሐኪም ነው


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እን የሀገር ጎብኝዎች የጠቅላላ አስተምህሮ  እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የዚህ አስተምህሮ አንዱ ክፍል በሆነው በዛሬው እለት ማለትም በግንቦት 16/2009 ዓ.ም. ያስተላለፉት አስተምህሮ ትኩረቱን የክርስትያን ተስፋ በሚል አርእስት ከዚህ ቀደም ስያደርጉት የነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ ተገልጹዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በዛሬው እለት አስተምህሮዋቸው ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በሉቃስ ወንጌል 24፡28-32 ላይ የተጠቀሰው ኢየሱስ ተስቅሎ ከሞተ ቡኃላ ከሙታን ዳግም አይነሳም በማለት ተስፋ ቆርጠው ወደ ሀገራቸው ወደ ኤማሁስ በመመልስ ላይ የነበሩ ሁለት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ታሪክ ላይ ያተኮረ እንደ ነበረም ተገልጹዋል።

እነዚህ ሁለት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ወደ ሚሄዱበት መንደር በቀረቡ ጊዜ ኢየሱስ መንደሩን አልፎ የሚሄድ መሰለ በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን እነርሱ “ቀኑ መሽቱዋል፣ ፀሐይም መጥለቋ ነው፣ ሰለዚህ ከእኛ ጋር እዚህ እደር” ብለው በጠየቁት ጊዜ ሐሳባቸውን ተቀብሎ ከእነርሱ ጋር ለማደር እንደ ገባም ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ከእነርሱ ጋር ራት ለመብላት በተቀመጠበት ወቅት፣ እንጀራውን ወስዶ ባረከ፣ ቆርሶም ሰጣቸው፣ ከዚያም ቡኃላ ዐይኖቻቸው ተከፈቱ፣ እርሱንም አወቁት፣ ነገር ግን እርሱ ከዐይናቸው ተሰወረ በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እነርሱም እርስ በእርሳቸው “በመንግድ ላይ ሳለን ሲነግረን እና ቅዱሳን መጽሐፍትን እየጠቀሰ ሲያስረዳን ልባችን እንደ እሳት ሲቃጠል አልነበረምን? ብለው እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች  በማስከተል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደርጉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ጠቅላላ ይዞዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

ውድ ወንሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የክርስትያን ተስፋ በሚል አርዕስት ጀምረነው የነበረውን አስተምህሮ በመቀጠል፣ በዛሬ እለት ደግሞ ከሙታን የተነሳውን ጌታን እና ተስፋ ቆርጠው ወደ ኤማሁስ በምሄድ ላይ የነበሩትን ሁለት ደቀ መዛሙርት ታሪክ ላይ እናተኩራለን። ከእነርሱ ጋር አብሮ መጓዝ በጀመረበት ወቅት በመስቀል ላይ የተከናወነው ነገር ተስፋቸውን እንዴ እንዳጨለመው በሚወያዩበት ወቅት ኢየሱስ ማንነቱን ሳያሳውቅ ያድምጣቸው ነበር። ኢየሱስ በመሲው ስቃይ እና ሞት ምክንያት በቅዱሳን መጽሐፍት ውስጥ ስለ እርሱ ተጽፈው የሚገኙት ነገሮች ሁሉ ፍጻሜ ማግኘታቸውን ቀስ በቀስ በማብራራት የሁለቱን ደቀ መዛሙርቱ ልብ በታላቅ ተስፋ እንዲሞላ አድርጎ ነበር። አብሮዋቸው በማዕድ ተቀምጦ እንጀራውን በቆረሰበት ወቅት ከእነርሱ ጋር የነበረው በመንገድ ላይ ሲጓዝ የነበረው ከሙታን የተነሳው ጌታ መሆኑን አወቁ። ከዚያን ቡኃላ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው መልኩሙን ዜና አበሰሩ። የኤማሁስ ታሪክ ኢየሱስ ከእኛ በሽተኞች ጋር አብሮ በመጓዝ ቀስ በቀስ በእግዚኣብሔር ቃል ኪዳን እንድንታመን ልባችንን የሚከፍት “የተስፋ ሃኪም” መሆኑን ያስረዳናል። በተጨማሪም ቅዱስ ቁራብን በጣም አስፈላጊ ነገር መሆኑን እና ልክ ኢየሱስ እንጀራውን እንደ ቆረሰው፣ ሕይወታችንንም በመቁረስ ለሌሎች እንድንሰጥ ያስተምረናል። እንደ እነዚህ የኤማሁስ ደቀ መዛሙርት እኛም ሌሎችን እንድንገናኝ፣ ሐዘናቸውን፣ የልባቸውን ደስታ፣ የሕይወት ቃልን እንድናበስር እና በማይነጥፈው እና በማንኛውም የሕይወት ደረጃ አብሮን የሚጓዘውን በእግዚኣብሔር ፍቅር ተስፋ ማድረግ እንዲችሉ እንድንመሰክር ተልከናል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.