Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ንግግሮች

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት 70ኛው ጠቅላይ ጉባኤ የለገሱት ቃል ምዕዳን

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት 70ኛው ጠቅላይ ጉባኤ የለገሱት ቃል ምዕዳን

24/05/2017 16:39

“የወጣቶች ግኑኝነት በእምነት” በሚል ዋና ርእሰ ጉዳይ ሥር የተመራው እንዲሁም እ.ኤ.አ. በኢጣሊያ ካሊያሪ ከተማ እ,ኤ,አ, ከጥቅምት 26 ቀን እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ሊካሄድ የተወሰነው የኢጣሊያ ብሔራዊ የማኅበራዊ ሳምንት የማሰናጃ ርእስ በማድረግና በማስከተልም በኢጣሊያ የቤተ ክርስቲያን ኣቢያተ ፍርድ ቤተ ክርስቲያን ሕገ መስተዳድር ወጣቶች ሥራ እንዲሁም አስፍሆተ ወንጌል የተሰኙት ነጥቦች አማክሎ የሚወያይ እ.ኤ.አ. ከግንቦት 22 ቀን እስከ ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚዘልቀው 70ኛው የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዓመታዊ ጉባኤ አገረ ቫቲካን በሚገኘው በሲኖዶስ የጉባኤ አዳራሽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በለገሱት ቃለ ምዕዳን በይፋ የተጀመረ ሲሆን። ጉባኤው የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር ሆነው ላገለገሉት የተልእኮ ዘመናቸው ላጠናቀቁት የጀኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካዲናል አንጀሎ ባኛስኮን የሚተካ አካል ለመምረጥ ሦስት ስሞችን በመጠቆም ለቅዱስ አባታችን ማቅረቡም ሲገለጥ ይኸው ቅዱስነታቸው ምክር ቤቱን የሚመራ አዲሱ ሊቀ መንበር እንደሰየሙ ዛሬ ጧት ከቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል የተሰራጨውን ዜና የጠቆሙ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጓራሺ አያይዘው ይኸው ዛሬ እ.ኤ.አ. ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በጳጳሳዊ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ተጋባእያኑ ብፁዓን ጳጳሳት በሁባሬ መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው አስታውቋል።

እ.ኤ.አ. ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ባለው አጥሪየም (ደጀ ሰላም) በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ ከኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አለሳንድሮ ጓራሺ ይጠቁማሉ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ለጉባኤው ባስደመጡት ንግግር፥

“በቅድሚያ የፁዓን ጳጳሳቱን ምክር ቤት ላለፉት 10 ዓመታት በሊቀ መንበርነት ለመሩት ካለ መታከት ሁሉንም በመታገስ እኔንም ጨምሮ ያሉት ቅዱስ አባታችን ለእኔ ያሳዩት ትእግስት ቀላል አይደለም እና እርስዎን ብፁዕነትዎን ካርዲናል ባኛስኮ በጣም አመሰግናለሁ”

ክፍት ንጽጽር

“ማንኛውም አካል ይሁን  የጉባኤ መሪም ውይይት እንዳይኖር ሃሳብ እንዳይቀርብ የሚያግድ ከሆነ ለሐሜትና ስም ለማጥፋት ተግበር በር ይከፍታል። ይኽ ደግሞ እጅግ በጣም አደገኛ ነው፡ ስለዚህ በመካከላችን ክፍት ግልጽ ውይይት መኖር አለበት። የምስማማበት የማልስማማበ ማንኛውም ዓይነት አስተያይት መቀበል መቻል አለብን። በነጻነት ሃሳብክን በመግለጥ ሂደት ውይይት ማረጋገጥ ወሳኝ ነው።

ያሉት ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን በመቀጠል፡“እነዚህ በመነጻጸር ግልጽ በመሆነ ሃሳብ በማቅረብ ሥልት የሚመሩት የጉባኤ ቀናት ክፍት ትህትና የተሞላው ቅን ንጽጽር እንዲታይበት እመኛለሁ፡ ጠንካራ ንጽጽር ሊያስፈራችሁ አይገባም ለዚያ ለብዙኅነት ለኅብረ ሃሳብ ክፍት የሚያደግ ዕጣ ዕድልን በወንድማዊ ፍቅር ለሚያስታርቅ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ክፍት መሆን ነው”።

ከመዘጋት መጠንቀቅ

“ሲኖዶሳዊነት ያንን ውሳኔዎቻችንን የሚያነቃቃው ለእሳቢያችንና ለታታሪነታችን ሁሉ እስትንፋስና እርምጃ ነው ስለዚህ ላለን ሱታፌ መግለጫ ነው። በዚህ አድማስ ብቻ ነው የምናቀርበው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እውነተኛና ለወቅታዊት ቤት ክርስቲያን ብቃት የሚኖረው። በዚህ መንገድ ብቻ ነው የወቅቱን ውስብስቡን ሁኔታ ያለፉት ክንዋኔዎቻችን የተረጋገጡት ውሳኔዎችን ሁሉ እውቅና በመስጠት ግልጽነት ባለው ውይይትና ምክክር ለመጋፈጥ የምንችለው።

ጉዟችን በገዛ እራስ መዘጋት እምቢተኝነት የተሞላው በታማኝነት እየዛልን ለዚያ በቤተ ክርስቲያን ለታቀበው እምነት ምስክርነት አሳማኝነቱ ላይ እክል ፈጥረን ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ለእምነት አሳማኝነት  እንቅፋት ሆኖ መገኘት በእምነት ምክንያት ከሚፈጸመው ስደትና መከራ እጅግ አስጊና የከፋ አደጋ ነው”

ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ፥ ለወጣት ትውልድ ትኩረት መስጠት

ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ንግግራቸውን በመቀጠል ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ወደ ጉባኤ የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ያስደመጡት የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር በመሆን ለአስር ዓመት ያገለገሉት የተልእኮ ዘመናቸው ያጠናቀቁት ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ በንግግራቸው ለወጣቶች አቢይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል በማለት ያሰመሩበትን ሃሳብ ጠቀስ በማድረግ፥

“የወጣት ትውልድ የሕይወት ሁኔታ፣ ብቃታቸውና አምቁ ኃይላቸው ሁሉ ግምት በመስጠት የነገ ሕይወታቸውን ለመገንባት ያላቸው ትልቅ ምኞት እኛ ለምንሰጠው ሕንጸት መጠይቅና በሕንጸት ዙሪያ ላለብን የጥሪ ኃላፊነትና ለምንሰጠው ምስርነት እንፈትሽ ዘንድ አቢይ ጥያቄ ነው። ስለዚህ ከወጣት ትውልድ ጋር መገናኘት በሕይወታችን የእግዚአብሔር ቀዳሚነት ዳግም ለማረጋገጥ በዚህ ሂደትም በዚያ ከእውነት ከሚመነጨው ነጻነት አማካኝነት እንድናስብና እንድንተገብር ያግዘናል”

የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አዲስ ሊቀ መንበር

ቀደም ተብሎ እንደተገለጠው ሁሉ፡ ምክር ቤቱ ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ የሚተካ አዲስ ሊቀ መንበር ለመምረጥ ያለው የሦስት እጩ ተመራጮች ስም የማቅረብ መብት በመጠቀም ለቅዱስነታቸው ሦስት ስሞችን ማስተላለፉ ሲገለጥ፡ ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ አስደምጠዉት በነበረው ንግግር ቅዱስ አባታችን ለሚመርጡት የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር ከወዲሁ ለሚሰጣቸው ኃላፊነት ሙሉ አውቅና ለመስጠትም ታዛዥ መሆናቸውና ያላቸውን መልካም ፈቃድ ከወዲሁ ማረጋገጣቸው ልኡክ ጋዜጠኛ ጓራሺ ያመለክታሉ።

24/05/2017 16:39