Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ሳይንስና ትምህርት

ቅዱስ አባታችን፥ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል አማራጭ አዲስ የኤኮኖሚ እቅድ እንዲከወን ጥሪ አቀረቡ

ቅዱስ አባታችን፥ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል አማራጭ አዲስ የኤኮኖሚ እቅድ እንዲከወን ጥሪ አቀረቡ

22/05/2017 17:21

እ.ኤ.አ. ግንቦት 15 ቀን 1891 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ ባንድ ወጥ Rerum Novarum - አዳዲስ ነገሮች”  በሚል ርእስ ሥር ር.ሊ.ጳ. ሊዮነ 13ኛ ወቅታዊው የቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት በዝርዝር ተንትኖ በቅደም ተከተል የሚያቀርብና የሚያብራራ የደረሱት  ዓዋዲ መልእክት ዝክረ 100ኛው ዓመት ምክንያት Centesimus Annus - ምዕተ ዓመት በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ግንቦት 1  ቀን 1991 ዓ.ም. ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የደረሱት በቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ስልጣናዊት ትምህርት ሥር የሚመደብ ዓዋዲ መልእክት መሰረት ያደረገ እ.ኤ.አ. ሰኔ 5 ቀን 1993 ዓ.ም. በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎድ ዳግማዊ ፈቃድ የተቋቋመው ስለ ር.ሊ.ጳጳሳዊ የድጋፍ ተቋም ምዕተ ዓመት  ያሰናዳው የሁለት ቀናት ዓውደ ጥናት እ.ኤ.አ. ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. መጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. አገረ ቫቲካን በሚገኘው ቀለመንጦስ የጉባኤ አዳራሽ በዚህ ሰብአዊ ክብርና የጋራ ጥቅም ያማከለ ኤኮኖሚ  በሚል ርእስ ሥር  በተካሄደው ዓመታዊ ዓውደ ጉባኤ ከ 18 አገሮች የተወጣጡትን 300 ተጋባእያንን ተቀብለው በለገሱት መሪ ቃል መጠናቀቁ የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ማሶቲ አያይዘው የተካሄደው ዓውደ ጥናት ሥራና ወቅታዊው የዕደ ጥበብ እድገት ለገንቢ አማራጭና ሁሉንም አቀፍ ማንንም ሳያገል እንዲከወን ከዚህ ባሻገርም የሥራ ዕድልና ሰብአዊ ‘ግላዊ - ማኅበራዊ’ ክብር በዚህ በሥነ አኃዝ የተራቀቀ ዕደ ጥበብ በተረገጠበት ዘመን ተመስሎውን በመተንተን የሥራ ዕድል ከሰብአዊ ክብር ጋር በማቆራኘት የአቢያተ ሰብ ቅንና ተገቢ ጥያቄ የሚያስተናግድ፡ በድኽነት የተጠቁትን ኑሮ የሚያሻሽል ለጋራ ጥቅም ያነጣጠረ መሆን እንዳለበት የተካሄደው ዓውደ ጥናት እንዳሰመረበት ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ፊት ተጋባእያኑን በማቅረብ ለቅዱስነታቸው የሰላምታ መልእክት ያስደመጡት የተቋሙ ሊቀ መንበር ዶሚንጎ ሱግራንየስ ቢከል እንዳሰመሩበት አስታውቋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለተጋብእያኑ ሰላምታን በማቅረብ እንዲሁም ቀድመው ንግግር ላስደመጡት ስለ ር.ሊ.ጳጳሳዊ የድጋፍ ተቋም ምዕተ ዓመት  ሊቀ መንበር ክቡርነታቸው ዶሚንጎ ሱግራንየስ ቢከል በማመስገን ሥልጣናዊ ምዕዳናቸውን አስጀምረው፥

“መተሳሰብ መግባባት እንደ አግባብ የሚከተል አዲስ የኤኮኖሚ የንግድ ሂደትና ሥርዓት መከወን ያስፈልጋል፡ ይኽ ደግሞ እናንተ በአሁኑ ወቅት የዕደ ጥበብ እድገት ድኮችን ገዛ እራሳቸውን ለመከላከል ብቃትና አቅሙም የሌላቸውን የሚዘነጋ ሂደት(ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክት ቍጥር 16) እንደ ቅቡል እያደረገ ያለው ባህል ለማረም ለመለወጥ የሚያስችል መሆኑ በማብራራት፡ በሥነ ምርምርና የቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ሥልጣናዊ ትምህርት በማስደገፍ የምታደርጉት ጥረት የሚመሰገን ነው”

ያሉት ቅዱስ አባታችን በማስከተልም፥ ብዙ ነገሮች መሻሻል እንድሚችሉ ታምኖ ሰብአዊ ቤተሰብ ተሟይ ማንንም የማይነጥል ተቀባይነት ያለው የጋራ የልማት እቅድ ለማረጋገጥ የሚጥሩ ብዙ እንዳሉ (ከማኁ ቍጥር 13) አስታውሰው፡ ይኽ ተቋም በሁሉም የቁጠባና የንግድ ኤኮኖሚ ዘርፍ ሁሉ የቤተ ክርስትያን ማኅበራዊ ትምህት መሠረተ ሃሳብ በማስደገፍ የሚያቀርበው አማራጭ የሕንጸት እቅድ የሚደነቅ ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሶቲ ያመለክታሉ።

“ … የተሟላ ሰብአዊ እድገት ለማነቃቃት ውይይትና የሕዝቦችን መሠረታዊ ፍላጎትና አስተንፍሶ በማስተናገድ፡ ድኾችን በማዳመጥ ከዚያ በፍላጎታቸው ሳይሆን ተገደው ከተነከሩበት ከሰብአዊ በታች በሆነ የኑሮ ደረጃ የሚገኙትን ሁሉ ናጻ ለማውጣት የሚያበቃ ራእይ አስፈላጊ መሆኑ በጉባኤው የፍጻሜው ሰነድ ላይ ተሰምሮበታል። ይኽ ዓይነቱ ራእይ እግብር ላይ ለማዋል የሰው ልጅ ሃብት ሁሉ በማጠራነፍ ድኾች የኅብረተሰብ ክፍል ዋና በኅብረተሰብ ሕይወት ተወናያን የሚያደርግ ለሁሉም ሰው ልጅ ጥቅም ትኵር የሆነ አሰራር አስፈላጊ ነው። ይኽ አሰራርም ባለ ሃብቶች ሠራተኛው ማኅበረ-ሰብ አበይትና ተናንሽ ትካሎች የሚያበረታታ በዚህ መንገድም ማኅበራዊ ተገሎነት ለማስወገድ የመተባበርና የመደጋገፍ ባህል ለማቆም ይቻላል”

በዚህ ዓይነት አመለካከትና ሂደት በማኅበረሰብ በኤኮኖሚና በንግዱ ዓለም ሕይወት እንዲኖር ለማረግ እንደሚቻል ቅዱስነታቸው አብራርተው፥

“ዓውደ ጉባኤው በዚህ በአሁኑ ወቅት በመታየት ላይ ያለው ሥራ አጥነት መፍትሔ እንዲገኝለትና አዲሱ የዕደ ጥበብ አብዮት የሚያቀርበው ጥልቅ የሚባሉትን ጥያቄዎች በማስተናገድ ዕደ ጥበባዊው አብዮት ለሁም እንዲዳረስ በሁሉም ተደራሽ እንዲሆን የሚያስችል መንገድ መጠቆም ያለው አስፈላጊነት ተወያይቶበታል። የአቢያተ ሰብ ወቅታዊውና መጻኢው ጥያቄውን በማስተዋል ልክ ቤተ ሰብ ርእስ ዙሪያ የመከረው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እንዳመላከተው የሥራ ኤኮኖሚ በቤተሰብ ላይ የሚኖረው ተጽእኖና የሚፈጥረው ችግር እንዳለ ለይቶ ቤተሰብ የሚደግፍ በማኅበራዊ ሕይወት ዋነኛ ተወናያን የሚያደርገው እድል (የፍቅር ሐሴት ዓዋዲ መልእክት ቍ. 44 ተመልከት) ለመፍጠር ያስችላሉ የሚላቸው መንገዶችን በወንጌል ብርሃን በሚመራው የቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት መሰረት የሚያቀርበው ሃሳብ ቅኑ የበለጠ ነጻና ስሙር ዓለም ለመፍጠር የሚደግፍ መሆኑ አመላክቷል”

ያሉት ቅዱስ አባታችን የለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን፥ “ሥራችሁ ውጤታማ እንዲሆን እየተመኘሁ የእግዚአብሒር ቡራኬ በእናንተ ላይ በቤተሰቦቻችሁ በአገልግሎታችሁ በመላ ስለ ር.ሊ.ጳጳሳዊ የድጋፍ ተቋም ምዕተ ዓመት አባላት እንዲወርድ እማጠናለሁ” በማለት ማጠቃለቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ አስታውቋል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ይኽ ስለ ር.ሊ.ጳጳሳዊ የድጋፍ ተቋም ምዕተ ዓመት  በየዓመቱ በኤኮኖሚ ዘርፍ አቢይ አስተዋጽኦ ያደረጉትን በመምረጥ የሚሰጠው ኤኮኖሚያዊ ወማኅበራዊ የተሰየመው የ2017 ዓ.ም. ሽልማት በጀርመን ሙዩኒክ መንበረ ጥበብ የማኅበራዊ ስነ ምግባር መምህር “የዘላቂነት መሠረተ ሕግ፡ በስነ ቲዮሎጊያዊ ስነ ምግባር ጥናት ማእቅፍ” በሚል ርእስ ሥር ጥናታዊ መጽሓፍ ደራሲ በኤኮኖሚያዊ ስነ ግምባር ርእስ ሥር የተለያዩ ጽሑፉ በማቅረብ የሚታወቁ ፕሮፈሰር ማርኩስ ቮግትን እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን የሥነ ማኅበራዊ ስልጣናዊ ትምህርት ጦማሪ ፈረንሳዊ ካህን አባ ዶሚኒክ ግረኒየር፡ በ 1900 ዓመታት የቤተ ክርስቲያን ማሕበራዊ ሥልጣናዊ ትምህርት ዙሪያ የሚደነቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ኦስዋልድ ቮን ነል ብረኡንግ ዙሪያ የተለያዩ በራዲዮ የተሰራጩ የጥናት ዓምድ ያሰናዱ ጀርመናዊ ጋዜጠኛ ቡክሃርድ ሻፈርስን በሚዩኒክና ፍሪንሲንጋን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ራይንሃርድ ማርክስ በተመራው የመራጭ ዳኛ ብቁ ተብለው ለተመረጡት ሽልማቱን ከቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን እጅ መቀበላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሲቲ ገልጠዋል።   

22/05/2017 17:21