2017-05-18 09:37:00

ብፁዕ አቡነ ፊዚከላ፥ ለቅዱስ አባታችን ቅዱሳን ሥፍራዎች ሁሉ ለአስፍሆተ ወንጌል ትዕድልት ናቸው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅድስት ማሪያም ዘፋጢማ ቅዱስ ሥፍራ ያካሄዱት የሰላምና የተስፋ ሐዋርያዊ ንግደት ቅዱሳት ሥፍራዎች በጠቅላላ ለአስፍሆተ ወንጌል ፍሪያማነት ተገቢ ሥፍራ መሆናቸው የሚመሰክርና የሚያረጋግጥም ጭምር መሆኑ እ.ኤ.አ. ከግንቦት 12 እስከ ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም. በፖርቱጋል ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ዘፋጢማ ስላካሄዱት ሐዋርያዊ ንግደት አስደግፈ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃል ምልልስ ያካሄዱት የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበርና በቅዱስ አባታችን ውሳኔ መሠረት የቅዱሳት ሥፍራ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የመንከባከብ ኃላፊነት የተሰጣቸው ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ አብራርተው፥ ይኽ የቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ንግደት በራሳቸው  በቅዱስነታቸው ቃል ለመግለጥ ይቻላል። አንዱ የሰላም ንግደት የሚል ነው። ምክንያቱም የቅድስተ ድንግል ማርያም ዘፋጢማ መልእክት የአንድ አቢይ ተስፋ መልእክት መሆኑ የሚያስረዳ በመሆኑ ነው።  በሰዎች መካከል ግንኙነት ተገንኝቶ የመወያየት ብቃት የመኖር ተስፋ የሚያመላክት ሲሆን፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በዚያ ቅዱስ ሥፍራ ቅዱስነታቸው እንዳሉት ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ዘፋጢማ መልእክት እንደ አንድ የብርኃን ካባ ነው በማለት ከገለጡት ሃሳብ ጋር የተጣመረ ሲሆን፡ የብርኃን ካባ ማለት የእምነት የፍቅር ጽናትና ኃይል ማለት ነው። ስለዚህ እነዚህ የአማኞች የሕይወት አግባብ መሆን የሚገባቸው አማኝነትን አፍቃሪነትን የሚያስገነዝብ ነው። ሥስተኛውና መሠረታዊ ነጥብ ደግሞ ጸሎት የሚል ነው። የቅድስተ ማርያም ዘፋጢማ ገጠመኝ ጸሎትና ጸላይነት የሚል ነው። ወደ ፋጢማ የሚኬደው ቅድስተ ማርያምን ለመጸለይ ነው፡ የማርያም ምልጃ ማእከል ያደረገ ጸሎት ለማቅረብ ነው። በዚያ ቅዱስ ሥፍራ በግልም ሆነ በጋራ የሚደገመው የመቁጸሪያ ጸሎት የጸሎት ጽሞና የማዳመጥ ጽሞና ያስተንትኖ ጽሞና ያጣመረ መሆኑ ቅዱነታቸው እዛው ተገኝተው በፈጸሙት መንፈሳዊ ተግባር አማካኝነት አስተጋብተዋል

ቅዱስነታቸው እንዳሉት ቅዱሳት ሥፍራዎች ለግብረ አስፍሆተ ወንጌል መተኪያ የሌላቸው ለአስፍሆተ ወንጌል የተገቡ ቦታዎች ናቸው፡ አስፍሆተ ወንጌል በገዛ እራስ መዘጋትን ሳይሆን ከእራስ ወጥቶ በቃልና በሕይወት ወንጌል ለሌሎች ማካፈል ማለት ነው። ከገዛ እራስ መወጣትን የሚጠይቅ እርሱም ልኡክነትን የሚያንጸባርቅ ነውይኽ ማለት ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ማለት ነው። ስለዚህ በእያንዳንዱ አማኝ ምእመን ቤተ ክርስቲያናዊነትን ጥሪ መኖር ማለት ነው። ጽሞና አድማጭ ጽሞና አስተንታኝ ጽሞና ጸላይ ገጠመኝ ለአስፍሆተ ወንጌል መንገድ ነው። ወደ ሌሎች ማለት በእያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጡር ዘንድ በኑባሬ ያለው እግዚአብሔርን የመናፈቅ ባህርይ ለይቶ መልስ የሚያሰጥ ነው።

ቅዱስነታቸው የቅዱሳት ሥፍራ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጉዳይ የሚከታተል ኃላፊነት ለዚህ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሲሰጡ ባስተላለፉት መእክት ላይ እንዳመለከቱት፥ ቅዱሳት ሥፍራዎች ለግብረ አስፍሆተ ወንጌል መተኪያ የሌላቸው ሥፍራ ናቸው በማለት ይገልጣሉ።

የሕዝብ ሃይማኖተኛነት ሰጋጅነት አምላኪነት መንፈሳዊነት የሚገለጥበት ሥፍራ ነው። የሚገለጠውም በመንፈሳዊ ነጋዲነት ተግባር ነው። በመሆኑም ይኸንን የሕዝብ በቅዱስ ሥፍራ መገኘት ለትምህርተ ክርስቶ የሚያነቃቃ መሆን አለበት፡ ቅዱሳት ሥፍራዎች ባላቸው ውስጣዊ ሕይወትና ብቃት ማኅበረ ክርስቲያን ወንጌላዊነት በሙላት እንዲኖር አወንታዊ ተጽእኖ ናቸው። ለእውነተኛው እምነት ግፊት ናቸው። አወንታዊ ተጽእኖ ያሳድርብኻል ስለዚህ ቅዱሳት ስፍራዎች ለአስፍሆተ ወንጌል በተገቢ ጊዜ እንድትገኝ የሚያነቃቃ ምቹ ሥፍራዎች ናቸው።

የሰው ልጅ ወደ ቅዱሳት ሥፍራዎች የሚከውነው መንፈሳዊ ንግደት ያንን በሰው ልጅ ውስጥ በኑባሬ ያለው የሕይወት ትርጉም የመሻት ግፊት የሚገልጥ ነው። ምጥቁን የመፈለግ ከየት መጣሁ ወዴት ነው ያቀናሁት ፍጻሜ ምንድር ነው ለሚሉት በሰው ልጅ ውስጥ በኑባሬ ለሚነሱት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የሰው ልጅ ወደ ገዛ እራስ ውስጥና ከገዛ እራስ ውጭ ይነግዳል። ስለዚህ መንፈሳዊ ንግደት ጥልቅ ቲዮሎጊያዊ ትርጉም ያለው የእምነት ክፍል ነው በብሉይና በአዲስ ኪዳን ውስጥ በተለያየ መልኩ ተመልክቶም ይገኛል። በቅዱስ የምኅረ ዓመት ወቅት ወደ ጓዳሉፐ ማያማዊ ቅዱስ ስፍራ 22 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ምእመን መፈሳዊ ንግደት መፈጸሙ ይነገራል። አማኞችም ይሆኑ ኢአማኒያንም ጭምር ወደ ቅዱሳት ሥፍራ ሲጎርፉ ታያለህ፡ አማኙ ስለ ሚያምን ብቻ ሳይሆን ምጥቁን በመፈለግ ጎዳና ያለ መርካት እንዳለና ብታገኘውም መገኘቱ ለገዛ እራሱ ዘወትር ፈልገኝ የሚል መሆኑ የሚያረጋግጥ ሲሆን ኢአማንያኑ ደግሞ በውስጥ በኑባሬ ያለው የላቀውም ምጥቁን የመፈለግ ባህርይ ስለ ሚገፋፋው ይኸንን በተለያየ መንገድ እየገለጠ ሳያወቁት ወደ ሚያመልኩት አምላክ እንደሚያቀኑ የሚያረግጥ ነው። ስለዚህ ይኽንን ሁሉ እግምት ውስጥ በማስገባት ቅዱሳት ሥፍራዎች በቃልና በሕይወት በጥልቅ ክርስቲያናዊ ብስለት ቲዮሎጊያዊና መጽሓፍ ቅዱሳዊ ብስለት (እወቅት) የተካነ አስፍሆተ ወንጌል የተገቡ ሥፋዎች ናቸው የሚባሉት፡ ቅዱሳት ሥፍራዎች የእምነት መግለጫና መንፈሳዊ ሰብኣዊ ተመክሮ በጥልቀት የሚኖርባቸው ሥፍራዎች በመሆናቸውም ከዚህ ጋር በሚመጣጠን መንፈስ ሊኖሩ የገባቸዋል

በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.