2017-05-18 09:42:00

ብፁዕ አቡነ አውዛ፥ በተለያዩ ግጭቶች ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙት አመጾች ለማስወገድ ነቅቶ መሥራት አስፈላጊ ነው ሲሉ አሳሰቡ


እ.ኤ.አ. ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኒው ዮርክ በሚገኘው ዋና መቀመጫው ባለው የጉባኤ አዳራሽ በድርጅቱ የጸጥታና የደኅንነት ምክር ቤት “ሴቶች ሰላምና ደኅንነት” በሚል ርእስ ሥር በጠራው የውይይት መድረክ የተሳተፉትና ንግግር ያስደመጡት የቅድስት መንበር በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ በርናርዲቶ አውዛ፥

በተለያዩ በዓለምችን ግጭቶች በሚታይባቸው ክልሎች በሴቶች ላይ የሚፈጸመው አሰቃቂው አመጽ እንደ የእግብር እሳት ሆኖ ለሁሉም አገሮች መንግሥታትና መልካም ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ድርጊቱ ለማውገዝና ጸረ ይኽ አሰቃቂ ተግባር ተጨባጭ ምላሽ ለመስጠት የሚገፋፋ መሆን አለበት። ግጭት ባለበት ወቅት ሊፈጸም የሚችል የጎንዮሽ እክል ነው ተብሎ መግለጡ ጸረ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ነው፡ ከዚህ ጋር በማያያዝም ይኽ አገላለጥ በጠቅላላ ሰዎችን ከቦታ ቦታ የማዘዋወሩ ወቅታዊው የአዲስ ባርነት ተግባሮች፤ ሴቶች ለወሲብ ዓመጽና ለወሲብ ባርነት የመዳረጉ፤ ጽንስ የማስወረድ የሰውን ልጅ በእደ ጥበብ ውጤቶች በመጠቀም መኻን የማድረጉ ተግባር፤ የግዳጅ ጋብቻ የመሳሰሉት ጸረ የሰው ልጅ ተግባር ሁሉ የሚመለከት ነው፡ ይኽ ደግሞ የሞት ባህል በተለያየ ደረጃ እንዲኖር የሚያደርግ ኢሰብአዊ ተግባር ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ ይጠቁማሉ።

የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ አውዛ፥

ይኽ እጅግ ዘግናኝና አቢይ ገበን ተብለው የሚገለጡት ግጭቶችን ተገን በማድረግ በሴቶች ላይ የሚፈጸምመ ዘርፈ ብዙ ዓመጽ፥ ክግብረ ሸበራ በምንም ተዓምር ተነጥሎ የማይታይ ጸረ ሰብአዊ ተግባር ነው። በጠቅላላ በተለያየ መልኩ በሰቶች ላይ የሚፈጸሙት አሰቃቂ በደሎች፤ ባሸባሪያን ተጠልፈው ለግብረ ሽበራ መሣሪያ እንዲውሉ ማድረግ፤ ላመንዝራነት ሕይወት በመዳረግ የገቢ ምንጭ እንዲሆኑ ማስገደድ፤ በግጭት ለሚሳተፉ ታጣቂዎችና ተዋጊዎች ሴቶችን እንደ ገጸ በረከት ማቅረብ። ተዋጊ ኃይሎች በሚያገኙት የድል  ውጤት አንጻር ሴቶች እንደ ክፍያ መስጠት፤ ሴቶች ለአጥፍቶ የመጥፋት ድርጊት መሣሪያ የማዋሉ ጸያፍ ተግባራትን …

ሁሉ በመዘርዘር በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ዘርፈ ብዙ አመጽ እንዲቆም ለማድረግ የሚያስችል መንግሥታት ቆራጥ ፍላጎት ሊኖራቸው ይገባል፡ እነዚህ ጸያፍ ተባሮች ጨርሶ ለማስወገድ የሚያበቃ ጽናትና ተገቢ ሕግና ሥርዓት ማስተግበር አስፈላጊ ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው፥

“ለዚያ ዓመጸኛው ባህል መላ ዓለም በተለይ ደግሞ ሰብኣዊ ክብራቸው ተጥሶ በአስከፊ አመጽ የተሰቃዩትና በመሰቃየ ላይ የሚገኙት ለዚያ ጸያፍ ተግባር የሚዳረጉት ለአቅመ አዳም የደረሱና ያልደረሱ ሴቶችን ይኽ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታና የደኅንነት ምክር ቤት ተስፋ ለመስጠት ከወደቁበት ከባድ ኢሰብአዊ ተግባር ለማዳን መጠነ ሰፊ ርብርቦሽ በማድረግ ለሴቶች መብት መከበር ተግቶ ከወደቁበት ካስከፊው ችግር እንዲታደጋቸው ብቃት ይኑረው። እነዚህ ሴቶች ልጆቻችን እህቶቻችን እናቶቻችን ተስፋቸው ባክኖ እንዳይቀር ስለ እነርሱ መብትና ክብር እንጣበቅ ዘንድ ኃላፊነትና ግብረ ገባዊ ግዴታ አለበት”

በማለት ያስደመጡት ንግግር እንዳጠቃለሉ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.